ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 19, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ብአዴን ከአቶ ሌንጮ ለታ የተቀባይነት ጠብታ ይለምን።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የ80ሺህ ህዝብ ሰቆቃን ማነው አማጩ?  „እኔም ባሪያህ ከትንሽነቴ ጀምሬ እግዛብሄርን እፈራ ነበር“ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፲፰ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  19.02.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። የሚቀድመውን ማወቅ እንዴት ያለ ብልህነት መሰላችሁ ውዶቼ? ግን እንደምን አላችሁልኝ። እኔ እህታችሁ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። እኔ የሰኔ16ቱም ግብታዊ የድጋፍ እና የምስጋና ሰልፍ፤ የወርሃ ሀምሌ የሰሜን አሜሪካ የጠ/ሚር ጉዞም፤ መጨረሻ ላይ የብአዴን ጉዞን አክሎ ምቾት ያልሰጠኝ ዕጣ ነፍስ ነበርኩኝ። በሰኔ 16ቱ በቅጡ የተደራጀ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን አቅሙ ከታዬ ጠላት እንደ አሸን እንደሚያፈራበት የታለመ ነበር።  አደጋውንም አሳምሬ ገልጫለሁኝ ወዮለሽ አዲስ አባባ ብዬም ። ስልፉ የአዲስ አባባ የመከራ አምራች ስለመሆኑ አስረግጬ ገልጫለሁኝ። አማካሪም፤ አዳምጫም አልነበረም ያው የገበረ ተገብሮ ቀረ። እንደ ሰማዕቷ ሽብሬ ደሰለኝ ወላጆች ሁሉ አካሉን ያጣም አካሉን አጥቶ ቀረ።  የመሸበትም መሽቶበት ቀረ። የዳመነበት ዳምኖበትም ቀረ። ·        ዝበት እና እርቀት። የሀምሌው የጠ/ሚር እና የሚያርቧቸው ነፍሶች የስሜን አሜሪካ ጉዞ በሚመለከት ከዛ በፊት የስሜን አሜሪካ እስፖርት ፌስቲባል ለመገኘት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ባሳዩት መልካም ፈቃድ ላይ የነበረው ሳንክ፤ የነበረው የጦፈ ውግዘት የነበራችሁበት ነው።  እኔም ያን ጊዜ የሚጠቅማቸው እንደሆን ይሳካ፤ የማይጠቅማቸው ከሆነ ግን በጥበቡ አማኑኤል የፈቀደውን ይፈጽመው፤ ግን ተቀናቃኞ...