ልጥፎች

ከዲሴምበር 18, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጥማት።

ምስል
ጥማት!! „እግዚአብሄርም እንዲህ ይላል፤ --- በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፤ በመድሃኒቴም ቀን ረድቼህ አለሁ፤ እጠብቅሃ አለሁም፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፤ የተጋዙትንም ውጪ በጨለማም የተቀመጡትን ተገለጡ  ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለህዝቡ  ሰጥቼአለሁ።“ ትንቢተ ኢሳያስ ፵፰ ከቁጥር ፰ እስከ ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                       የለማ የዴሞክራሲ ጀግንነት እንዲህ ነው በአፍሪካ ፊደል ያሰቆጠረው ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? አጀንዳችን ባለቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አብሮ ደመር በመቀመጥ ሳይሆን በ27 ዓመት ውስጥ በጠፉን፤ በሾሎኩን ወደፊትም መጥፋቱም ሆነ መሽሎኩን ለመገደብ ወሳኙን ግንዱ ላይ ማተኮር የተገባ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ግንዱ ደግሞ አዲሱ ትውልድ ነው።  ከ7 እስከ 18 ዓመት ያለው። ያን ነው አንጸን ነፍስ ባለው የዜግነት ትሩፋት አንጸን መገንባት ያለብን። ያ ነው የዛሬው የቤት ሥራችን ሊሆን የሚገባው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ።  እንደ ሥርጉተ ሥላሴ እኛም ማስቲካ የሆን ይመስለኛል።  ያለቀ አሮጌ ቆርቆሮ ለምን አፈሰስክ፤ ስለምን የወዬበው ግድግዳህ ወረዛ፤ ስለምንስ መቆም የተሰነው ምርጊትህ ፍርክርክ ብሎ ህልምህ እንዲህ እና እንዲያ ሆነ እያለን የምናባክነው ጊዜ የተገባ አይመስለኝም። ይልቁኑ በቆሰለው፤ በተጎዳው፤ በደማው የማግስት ድልድይ ላይ እያንዳንዳችን ልናደርግ ስለሚገባው ብናተኮር እና ብንሥራ መልካም ይመስለኛል። አሁንም ቅድምም ያን ገዳይ፤ ያን ተስፋን ቀሚ፤ ያን መኖርን ነጣቂ ዘመን እያነሳን ከምንጥል እና በዛ ከምንገሸገሽ