የኢትዮጵያ ህይወት።
ጥሩ ሰው ሰፊ ስብዕና። ከሥርጉተ ሥላሴ 18.06.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ) ዳዊትም፣--- ሥራውን ሁሉ ምሳሌ አውቅ ዘንድ ይህ ሁሉ በእግዚአብሄር እጅ ተጽፎ መጣልኝ አለ። (መጽሐፈ ዜና መዋእለ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፲፱) የታደለ ማህጸን። የታደለ አብራክ። የታደለ እትብት። የታደለች መሬት። ኢትዮጵያ ብርሃን ወጣላት። ኢትዮጵያ ፈጣሪ አምላክ በቃሽ አላት። በቃ ራስ እግሩ ቅንነት። ራስ እግሩ ፍቅር። ራስ እግሩ መሆን። ራስ እግሩ ቁም ነገር። እራስ እግሩ ምህረት። ራስ እግሩ ማቀራረብ። ራስ እግሩ ማግስታዊነት። ራስ እግሩ ሰዋዊነት። ራስ እግሩ ተፈጥሯዊነት። እንዲህ ዓይነት የተባረከ የተቀደስ ብቁ መንፈስ የሰጠን አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን! ይህ ማለት ግን በሁሉም ሃሳብ ተሰማምቻለሁ ማለት አይደለም። የልዩነት ሃሳብ ያለው እንኳን ቢሆን በፍቅር አስማምቶ፤ አዋዶ ህሊና በጎ እንዲያስብ፤ ህሊና መልካምነትን እንዲያመርት፤ ህሊና ንጹህ የታጠበ እንዲሆን፤ የሚመክር - የጎበጠን ለማቃናት የሚያግዝ ግን ኮስታራ፤ ግን ወንዳ ወንድ፤ ግን ሃሞት ያለው፤ ግን የቆረጠ እናቱን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን አንድ ለማድረግ የሩቅ ህልመኛ። የአፍሪካ ህዝብ ደስ ብሎት፤ ስቆ አድሮ መዋል እንዲችል እጅ ለእጅ ለማያያዝ የሚተጋ ጥሩ ሰው ሰፊ ልቦና፤ መጠነ ሰፊ ራዕይ ያለው። ሰፊ ሆድ፤ ሰፊ ስብዕና ያለው። ኧረ ከዓይን ያውጣህ መዳህኒተ ዓለም አባቴ የሚያሰኝ። የሰው ልጅ የማይመች ሃሳብም ቢሆን ደስ ብሎት ለመቀበል የሚያስችል...