ወይ ባህርዳር እንደ ውጪ ወራሪ ጠላት ..?
ወይ ባህርዳር እንደ ውጪ ጠላት የመርዝ ጭስ መሞከሪያ?
ከሥርጉተ - ሥላሴ 18.06.2018 (ከገዳማዊቷ - ሲዊዘርላንድ)
"በሥጋው ቁርበት ላይ ቁስል ቢሆንና ቢሽር በቁስሉም ሥፍራ ነጭ እባጭ ወይም
ቀላ ያለ ቋቁቻ ቢወጣ በካህኑ ዘንድ ይታያል"
(ኦሪት ዘሌዋውያን ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፰– ፲፱።)
ማዘን ለማለት እንደ ሰውነት ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ነው። በዓለም ዓቀፍ ፍርድ ቤት የሚያስጠይቅ መከራ ነው ባህርዳር ላይ የተፈጸመው። አንድ ወጣት ሙሁር የዩነቨርሲቲ ሙሁር ሲናገር በታቀደ ሁኔታ ከተማ ላይ ሊተገበር የማይገባው የጥቃት ዓይነትን ነው የባህርዳር ሰማዕታት ያስተናገዱት።
ወደ ኋዋላ በምልስት ለምን ሆነ ለሚለው ምክንያታዊ የሆነ ነገር አለው። በአንድ ከይሲ ዕሳቤ ሰርጎ ገብቶ ያስፈጸመው ተልዕኮ መሆኑ ከመቀድሙ ለማገናዘብ እኔ በግሌ ተረድቻለሁኝ። ሚዲያ ላይም ጥንቃቄ የለም። የትኛው እሳቤ ህዝብን ለበለጠ ጥቃት ይዳርጋል የሚለው ማንዘርዘሪያ የለውም። የሰው ልጅ ህይወት ከሸቀጠም ባነሰ ደረጃ የተገመተበት ዘመን ነው በግራው ፖለቲካ ፍልስፍና፤ ጊዚያዊ እንጂ ዘላቂ ሁኔታዎች አይጠኑም። በማስተዋል ሊመረመሩ የሚገባቸው ነገሮች ጎልተው ይወጣሉ በቃ የፈረደባት የ ኢትዮጵያ እናት ብርንዶ ታቀርባለች። ወሸኔነቱ በማመላላጥ ከጎንደር የአማራ ተጋድሎ ጋር ተዛብቶ ቀረበ፤ ያ ቀደመ ዕልቂቱ ተከተለ ያው በመሞኮሪያው ህዝብ ላይ። ስለሆነም ይህ የተቋጠረ የበቀል እርምጃ ገፊ ገረጭራጫ ሃይል ነበረው። እነሱ ነፍሳቸውን አያውቁትም ይህን መሰል ዱብ እዳ ይመጣል ብለው። በዚህ ከይሲ እና በቅጡ በታቀደ ከራስ ቃር አቀራርቦ በተሰጠ ትንተና ገፊ ሃይል ጫና ፈጻሚውን ከመጨረሻው የሰው ልጅ የባህሪ ደረጃ አልፎ ወደ እንሰሳነት አስቀይሯታል ማለት ነው። በዚህ ሂደት ህፃናት አሉ። ይህን እዬሰሙ የሚያድጉ። ታዳጊ ወጣቶች አሉ ይህን እያዩ ያደጉ፤ በዚህ ውስጥ የቂም ውርስን አሸንፎ እንዴት ተብሎ የምህረት ዬይቅርታ መንፈስ መውለድ እንደሚቻል ከባድ የሆነ የመንፈሰም፤ የህሊናም፤ የሰብዕናም ፈተና ነው።
- በዳዩ እንዳኮረፈ ኮፈፍ እንዳለም ነው።
አሁን ባለው ሁኔታ ቀጥታ በዳዩ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሳፍንት እና አጋዢያቸው ብአዴን ውስጥ የተሰገሰገው የትግራይ ትግርኝ ጋንታ ፍንክች አላለም። ለይቅርታም ምንም ዓይነት በጎ ዝንባሌ አያሳይም። እንዲያውም ተበደልን ባዮች ናቸው። የተበደሉት ይቅርታ አድርጉ፤ ንፁህ ልብ ይኑራችሁ ብሎ ደፍሮ ለመናገር እንኳን በዳዮ በድያለሁኝ ይቅርታ ይደረግልኝ ብሎ ራሱን ዝቅ አድርጎ ሲመጣ ነበር። ነገር ግን አሁን የሚታዬው የተበደሉት እንዲተዉት ብቻ ነው ያለው ጫና። ይህ ደግሞ ለጊዜው ሊለዝብ ቢችልም ቁስሉን ሊያሽር ግን አቅም ያንሰዋል። ሰው የሚዬው የሦስት ዓመት አድርጎ ነው። አይደለም አማራ በስልት የማስወገድ ዘመቻ 43 ዓመቱ ነው። አሁን እነ ጥላሁን ግዛውን የአማራ ቴሌቪዥን ሲያቀነቅን በሬ ካራጁ ጋር ስለመሆኑ ሊያገናዛብቱ የቅንጣቢ ያህል አቅም የላቸውም። ለነገሩ እንኳን ሞታችን አዋጃችሁ ብሎ አይደለም የባህርዳሩን አውሮፕላን ማረፊያ ግንቦት 20 ተብሎ የተሰዬመው? ግፍ እኮ ነው። የገዳይህን ሃውልት ክልልህ ነው፤ ቀይህ ነው፤ መናህሪያህ ይህ ብቻ ነው በተባለ ቦታ ሃውልት ማቆም? ህሊና ቢስነት ነው።
ወደ ቀደመው ስመለስ እነሱስ ይተውት ጥቃቱ ሳይቆም ከቀረ ማገርሸቱ እንዴት ይቀራል? አሁንም እኮ ድብደባ በዬእስር ቤቱ አለ፤ በጠላት እጅ በወደቁት እንደ መተከል፤ ራያ፤ ወልቃይት ጠገዴ ያሉ አካባቢያዎች እጥፍ ድርብ ንብርብር የሆነ ፍዳ እና ሰቆቃ ላይ ናቸው - በጠላት እጅ ውስጥ ነው ወድቀው ያሉት። አንድም እስረኛ እስከ አሁን ድረስ በባዶ ስድስት የሰው ማረጃ ቦታ አልተፈታም። በየዕለቱም በወልቃይት በጠገዴ በራያ እዬታፈኑ የሚወሰዱት ባሊህ ባይ የላቸውም። እኔ እንደማስበው የአነ ዶር አንባቸው መኮነን ሆነ የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቅናዊ ከወጣቶች ጋር የሚያደርጉት የሃሳብ ሙግት እና የስምምነት ሂደት ቀጣይ ሊሆን የሚችለው በትግራይ መሳፍንቶች ዘንድ ያለው የጨርስው ዓዋጅ ሲቆም ብቻ ነው። ይህን ማስቆም ሳይቻል ዛሬ ያለውን የአማራ የጦፈ ሰላማዊ የቁጣ እንፍላሎት አስቆማለሁ ማለት ውሎ ሲያድር ሌላ መከራ ይዞ ሊያመጣ ይችላል። የእኔ ስጋት ይሄ ነው። አባ ዝምታ ጫናው ልክ የለውም።
እንዲያውም እኔ ከጠበቅኩት በለይ የአማራ ማህበረሰብ እጅግ ማህበራዊ ጨዋነቱ ጎልቶ እዬታዬኝ ነው። በዚህ መሰል በደል እኮ እንኳንስ 27 ዓመት 27 ቀንም በሰላም ቀዩ ውሎ ማደር እጅግ ከባድ ነው። ይህም ሆኖ አሁንም እነ ተራሮች ተራራው ላይ ገዢ መሬታቸውን ይዘው እንደ ተቀመጡ ነው። ይህ የሚጎዳው ውሎ ሲያድር የትግራይን ህዝብ ነው። መተላለቅን ሊያመጣ ይችላል። ምክንያቱም ሚዛኑን የጠበቀ ሁኔታ አይታይም። እዬተገደልክም፤ እዬታሰርክም፤ እዬተደበደብክም ባድማህን ተቀምተህም በቃ አማራነትህን እርሳው ከሆነ የሚያስኬድ አይሆንም።
ሌላው አኮ በለማ በለመለመ ቦታውም ሆኖ ያ አልበቃው ብሎ ሌላ ነገር አማረው ከድህንት ወላል በታች ከኢትዮጵያ ¼ ህዝብ የሚኖረው አማራ መሬት ሆኖ፤ በዛ ላይ ማን ይተካን ሲሉ ዶር አንባቸው መኮነን አዳምጫለሁኝ፤ ነፍስ ያላቸውማ ተገደሉ፤ ታሰሩ፤ ተሸለቱ፤ ተሰደዱ አሁን እኮ በሦስተኛ ደረጃ ያለው ትውልድ በተለይም ወያኔ ሃርነት ትግራይ ከመጣ የተወለዱት እኮ ናቸው ዳይናሚክ የሆነ ጥያቄ እያቀረቡ ያሉት … በራሱ ዘመን የተፈጠሩት …. እሱ ከመጣም እጅግ ዘግይተው የተወለዱት … የትም ይደግ የትም ይወለድ አማራ አማራ ነው።
ቢሸፍቱ የተወለደው ደርባባ ወጣት „ቢሸፍቱ የተወለድኩ ኢትዮጵያዊ አማራ“ ብሎ ነው የጀመረው። ሥነ- ልቦናው በተዓምር በፈጣሪ መንፈስ ቅዱስ የተቆራኘ ነው። ይህ አባባል እኮ ድንቅ ነው። „ቢሸፍቱ የተወለድኩ ኢትዮጵያዊ አማራ“ መሪ አላለም „ቢሸፍቱ ስለተወለድኩኝ ኦሮሞ ደም አለኝ በተጨማሪነት“ ነው ያለው እንጂ „ቢሸፍቱ የተወለድኩ ኢትዮጵያዊ ….“ ብሎ አልጀመረውም። ድፍረት ከዬት ይመጣል። አማራ ግን ሲወልድ ጡት አጠብቶ የሚያሳድገው ልጁን ኢትዮጵያዊ ነህ፤ ነሽ ብሎ ነው። ከዚህም የላቀ ነው በፈጣሪ አምሳል የተፈጠርክ "ሰው ነህ" ብሎ ነው የሚያሳድገው። ልዩነቱ እጅግ የሰፋ ነው። ስለዚህም ነው በእኛ እና በኢትዮጵያዊነት መካከል ፍቺ ለመፈጸም አደጋ ሆኖ ሲያስገድለን፤ ሲያስገልለን፤ ሲያስገርፈን፤ ሲያስፈጅን የኖረው ሚስጢሩ ይሄው ነው። አሁንም ትርምሱ ይሄው ነው። ኢትዮጵያዊነት መንበር ላይ ከፍ ብላ ስትታይ ሚስጢሩ ያስገኘው ክብር እና ሞገስ ቃጠሎ አስነሳ፤ ምቀኝነት ፈጠረ፤ ስለዚህም መንፈሱን ለመገደብ በሽፋን መጪ ተባለ … ጉራማይሌ ….
- ግን ይቻላልን?
እዬተገለልክም፤ እዬተገፋህም፤ እዬተረገጥህም እንሱ ይቅርታ አድርጉልኝ ባይሉም ምህረት አድርግላቸው አያስኬድም። ትግራይ ድንጋይ ተሸክማ ከአማራ እግር እስር ወድቃ ይቅርታ መጠዬቅ ይኖርበታል። ቀድሞ ነገር ለትግራይ ህዝብ ከከንባታውም፤ ከጋንቤላውም፤ ከሲዳማውም ከዬትኛውም ብሄር ብሄረሰብ ይልቅ አፋርን እና አማራ ይቀርባታል። ከአፋርም አማራ በወሰንተኝነት ይቀርባትል ለእትጌ ትግራይ። ከሌላው ቢቀር የእነ ፈላስፋው ዘረያዕቆብን እን የቅዱስ ያሬድን ስንት የትግራይ መንፈሳዊ ሊቀ - ሊቃውንታት አቮን ሽክፍ ክውን አድርጎ ለዘመናት አደራ ያወጣ፤ ጉሮሮም ያረጠበ፤ የያዘን አማራን ዛሬ ይህን ሁሉ መከራ ማድረስ አልበቃ ብሎ አሁን ደግሞ አራጦ ይዞ፤ ተኮፍሶ ማን ደፍሮኝ ብሎ መቀመጥ ጊዜው እያለቀበት ነው ለትግራይ ህዝብ።
እኔ ለጥጋበኞች እግር ለእግር ለተተኩት የወያኔ ማንፌስቶ መርዝ ጠጥተው መርዝን የሙጥኝ ላሉት አዳዲስ ምላጮች ሳይሆን ገና በሃሳብ ደረጃ ላልተጸነሱት ትንቢታዊ ህፃናት ይጨንቀኛል። እነሱ ለአማራ በሃሳብ ደረጃ ላልተጸነሱት ሳይቀሩ እንዳይፈጠሩ፤ ቀይ እንዳይኖራቸው፤ የዘር ማምከኛ ይሰጣሉ። እኔ ደግሞ ገና ለሚፈጠሩት የትግራይ ህፃናት ህልውና ቀጣይነት ያሰጋኛል። የኢትዮጵያ እናቶችም ያሳዝኑኛል።
ሰው መሆን ብቻ በሚጠይቀው በነገ በአማራ እና በትግራይ መሃከል ሊቀጥል፤ ሊኖር ስለሚገባው ግንኙነት ይጨንቀኛል፤ ይጠበኛል ከ50 ዓመት በኋዋላ እኛ ሳንንኖር መጪው መከራ ጉማም ይሆንብኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ኤርትራ እና ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች ሰላማዊ ግንኙነት ይጠበባል። እኔ ደግሞ ይሄ ቤት ሳይጸዳ የግቢ ያህል ነው ሚሰማኝ። መጀመሪያ ቤታችን ቅርብ ያለውን ችግር እንፍታ።
እነ ኦቦ ለማ መግርሳ እና እነ ዶር አብይ አህመድ፤ እነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና አነ ዶር አንባቸው መኮነን በጋራ በበሰለ የተመክሮ ሁኔታ፤ በላቀ ብቃት እና ጥበብ የኦሮሞ እና የአማራን ጤናማ ግንኙነት ከነበረው ዘመን ተሻጋሪ የእትብት ትስስር በላይ እጅግ ዘመናዊ አድርገውታል። የሚታዩ ገጭ ገው እኮ ሰው ሰራሽ አርቲፊሻል ናቸው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚፈብርካቸው። የቀደምቱ የኦሮሞ የፖለቲካ ሊሂቅ ኢልት ላይ እንደ ተጠለጠሉ አንሳፈው እንሱ ግን መሰሩትን አሳማሩት። አሁን የአማራ አክቲቢስቶች ጥቃቶችን ሲዘግቡ እንኳን አጅግ በተመሰጠ ጥንቃቄ በተሞላው ሁኔታ ነው። ስለምን? ተግባሩ ነው።
ኦህዴድ የሠራው በሳል የፖለቲካ አካሄድ በራሱ ህሊና ገዝ አቅም ስላለው ነው። ኦህዴድ ግራ ዘመም አይደለም። ኦህዴድ ሰብዕዊነት እና ተፈጥሯዊነትን መርሁ ያደረገ ታላቅ ብሄራዊ ፕሮስተሪካ አብዮት ያካሄድ የድንቆች ድንቅ የድንቅነሽ ባለውለታ ጉልላት ነው። ለኢትዮጵያዊነትም መድህን ነው። ኦህዴድ ፓን አፍሪካኒስትም ነው። ጥረቱ ከሥነ - ልቦና የተነሳ ስለሆነ ልበ ገብ፤ መስኖ ገብ፤ ህሊና ገብ ዝልቅ ገብ ነው። ስለዚህም ነው ሥርጉተ ሥላሴ በጥዋቱ ለማውያን የሆነችው። የሎሬቱ የተስፋ አብዮት ታቦት አዳማ ላይ ሃሌን ቀድሶ፤ ሰላምን ወርቦ፤ ፍቅርን አጨጌ! ልላዊነትንም አሰከነ። አፍሪካዊነትም አጎለለ!
ባህርዳርም ላይ የተናገሩት የፍቅር ትንግርት፤ ኦሮምያም ላይ በክብሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የህይወት ታሪክ ሙሉ ዘገባ ላይ ስለ አማራ አክቲቢስቱ ግን ብሄራዊ ጀግና የሃይማኖት አባቱ ክቡር ኡስታዝ ራያ „ጎንደር ማንአለው?“ ሲሉ ጎንደርን ለእርድ ያስቀረበውም፤ ያሳረደውንም የ43 ዓመቱን ሴራ ከነሸንኮፉ ማህበራዊ መሰረቱን ነው የነቀሉት።
ከ10 ሺህ በላይ የሚገመት ህዝብ መቱ ላይ „አማራን እንዳትነኩ ብትነኩ ዋ“ ሲል ያ የሥነ ልቦና ልቅና ከሜዳ የታፈስ አልነበረም። ከውስጥ በተለወጠ ከ አንጀት ተሁኖ በተሰራ የደም እና የሥጋ ንጹህ ጋብቻ የተፈጸመ የህሊና ጋብቻ ውጤት ነው። ለዚህ ነው ሥርጉተ ሥላሴ እኔ ለማውያን ነን ብላ የወጣቸው። ወደፊትም ቢሆን ለ አማራ አምጡ ድገሙ ቢባል እንደ ድርጅት ኦህዴድ ከብአዴን በላይ፤ እንደ ስብዕና ደግሞ እንደ ኦቦ ለማ መግርሳ፤ እንደ ዶር አብይ አህመድ እንደ ኡስታዝ ራያ ያለ ብቁ አጋር የውስጥ ትንፋሽ ማግኘት አይችልም። ይህ በዘመናት የታሪክ መፈራረቅ እንኳንቢሆን በፍጹም ሁኔታ ወደር የለሽ የ ዕንባ ታምር አዲስ ግኝት ነው። ልክ ጎጃም ለጎንደር ህዝብ ራሱን የደም ግብረኛ ፈቅዶ እንዳደረገው ሁሉ ማለት ነው።
ይህን ነው ያጣው የትግራይ ሥርዕዎ መንግስት መሳፍንት። ከሊቅ እስከ ደቂቅ አሁንም ይታመሳሉ፤ ይተራመሳሉ። ስለነገ አያስቡም፤ ለማሰብም የፖለቲካ አቅማቸው አይፍቅዳላቸውም። ስለምን? አቅል አልሰራላቸወም? አንድ የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር አፍሪካ ቀንድን አንድ አገር ለማድረግ በሚባትልበት በዚህ አዲስ ዘመን ትግራይ እራሷን ኮፍሳ፤ አማራን ለዛውም ጉሮሮዋን ጠላቴ ብላ አንቃ፤ ፈጅታ፤ ገፍትራ፤ አገር አልባ አድርጋ ለማክሰም ሌት እና ቀን ትባዝናለች። ወያኔ ሃርነት ትግራይ የትግራይ እንጂ የሌላ አይደለም። ሊሆንም አይችልም። የትግራይ መሬት ያበቀለው እፉኝት ነው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የመርዝ ድርጀት። ጥጋቡ እኮ ልኩን አልፎ ዓለም አቀፉን የስፖርት ድርጅት ፊፋን ሁሉ ተዳፍሯል። ከዚህ በላይ ማን አህሎኝነት፤ ከዚህ በላይ መታበይ ምን ሊመጣ … ይህን ልክ የሚያስይዘው የእዮር አደባባይ ብቻ ነው። አንድ ግራጫ ጸጉር የለም። ካለ እኒያ ቅዱስ አባት አቶ ገ/ መድህን አርያ በስተቀር።
- ምን ይሁን?
አማራ በጀመረው መልክ ውስጡን፤ መንፈሱን፤ ህሊናውን እያደራጀ ያቀረቡትን እያቀረበ፤ ካቀረቡት ጋር ማህበራዊ ግንኙነቱን፤ ፖለቲካዊ ግንኙነቱን፤ ጋብቻዊ ትስስሩን እያጠበቀ ብረት መዝጊያ የሆነ አቅሙን መገንባት ግድ ይለዋል። አማራነቱን አጥብቆ መያዝ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ትውልዱን ከጥቃት የሚታደገው ዘመን እራሱ፤ ግፍ ራሱ፤ በደል ራሱ የሰጠው ታላቅ የህይወቱ መሃንዲስ ነው - አማራነት።
እርግጥ ነው ቂምን፤ በቀልን፤ ጥላቻን፤ ፉክክርን፤ ራስን አሳብጦ ማዬትን፤ ሌላውን መገፋትን፤ ሌላውን መጫንን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አለመጥቀሙን አይቷል። ስለዚህ ከእነዚህ እኩይ ክፉ ባህሪያት ጋር ሳይነካካ ከፈጠሪው/ ከአላህ ጋር በመሆን ቀጣዩን ጊዜ ካቀረቡት - ከወደዱት - ከተረደቱ - ካከበሩት መንፈሶች አብሶ ከኦህዴድ ንጡህ መንፈስ ጋር የጠበቀ የሰለጠነ ትስስሩን አጎልብቶ፤ ነገን በጸና አስተማማኝ መሰረት ላይ ለመገንባት በራሱ ውስጥ በቅሎ መጽደቅ ይኖርበታል።
የዚህ ጉባኤ ዕድምታ ሰፊ ነው። የዛሬው ጹሑፌ ባህርዳር ላይ የተቀበረው የጥላቻ ፈንጅ ምንጩ ኢ-ሰባዊነት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ወንጀሉ የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት መሸከም የማይችለው ስለሆነ በዓለም አደባባይ የፍትህ ችሎት ሊታይም የሚገባው ስለመሆኑ ለማጠዬቅ ነው።
ይህም ሆኖ ጨቋኙ የ ኢሰባእዊ የኢ - ተፈጥሯዊ ድርጅት ማንፌስቶ ልኩን አውቆ በልኩ ለመራመድ ከወሰነ እና ከቆረጠ መጠለያ ጃንጥላዎችን ከሥር ለመንቀል ከፈቀደ፤ ከግራ ዘመመ የማረተ አይዲዎሎጂው ቆርጦ መፋታት ከቻለ ቢያንስ ነገን ማትረፍ ይችላል አቤቶ ወያኔ።
ማንኛውም ጥረት ለስኬት እና ለውጤት የሚበቃው ጊዜ፤ ሁኔታ፤ ቦታ፤ ዓለምአቀፍ ገዥ አመክንዮዎች በጥንቃቄ መያዝ ሲችሉ ነው። ሁሉም በዚያ ሲዖላዊ ድርጅት ማንፌስቶም ሆን በግርፎቹ ዕሳቤዎች ዙሪያ ፊቱን አዙሯል። እንጥፍጣፊም አትኩሮትም አክብሮትም የለም። አሁን ስለባድመ እነሱ ብቻ ነው የሚያቀነቅኑት ለሌላው አጀንዳው ሊሆን አልተቻለውም። ከዚህ የከፋ ቢመጣስ ምን እንሆናለን ብቻችን ተንጠልጥለን ቆጥ ላይ ሰፍረን ብሎ ማሰብ ይበጃል።
ሌላው ቀርቶ አሉ የሚባሉት የህግ ሊሂቁ ዶር ያዕቆብ ራሱ በዋናው ጭብጥ ላይ ለመወያዬት አቅም አንሷቸው ነው ያዬሆዋቸው እስክደነግጥ ድረስ። ልክ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ንግግር መጽሐፍ መሆን ነበረበት ብለው ከተከራከሩት የተሸላ ሃሳብ አላዬሁም። እነሱስ የልምድ የተመክሮ ማነስ እና ፖለቲከኝነታቸው የተነሳበት መሰረቱ አምክንዮው ለዚህ አቅም ፍለቅት ስለሚችግረው ነው ስለነበር።
አንድ የሹመት ንግግር ፖሊሲ አይደለም። እርግጥ ነው የፖሊሲ ሃሳብ ሊይዝ ይችላል። ግን ጠቋሚ እና አቅጣጫ አምልካች ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። ሃሳቡ በህግ ማስደገፍ ወይ ደግሞ በአፈጻጻም መመሪያ ብቻ የሚወሰንም ሊሆን ይችላል። ለዛ ሃሳብ በአጭር በረጅም ጊዜ መርሃ ግብር ያስፈልጋዋል። ልክ እንደዛ የባድምን ጉዳይ እልባት የሰጠውን ውሳኔ ዝርዝር አፈጻጻም ሆኖ ማዬት ናፍቋቸዋል፤ ማቄን ጨርቄን ያለ ሙግት ነበር የገጠሙት። ታላቁን የህግ አፍሪካዊ ባለሙያ ዶር ያ ዕቆብ ኃ/ ማርያም። ያን የወሳኔ ሃሳብ የአፈጻጻም ሂደቱን፤ የኮሚቴ አወቃቀሩን፤ በጀቱን መዘርዘር ነበረበት አይነት ነበር ሙግታቸው። እጅግ ነው ያዘንኩት። የሚያስገምት ሆኖ ነው ያዬሁት። ተመስገን ያልኩት ተሎ ሳተናው ብራና ላይ እንዲነሳ ቢደረግም እኔ ግን ቀድሜ ሰርቸዋለሁኝ፤ ቀሪ ሙሁራንም እኔ ያነሳሁዋቸውን እያንዳንዱ ነጥብ ነው አጽህኖት የሰጡት። የ እኔ የብዕር ጠብታ ተፈርቶ ድራሹ ቢጠፋም የ ኢትዮ ውይይቱ ግን ዩቱብ ላይ ማንሳት አልተቻለም። ከ እኔ ሃሳብ ጋር ከ አንድ እንቁላል የተሠራ ነው የሆነው። ከዶር ያዕቆብ ኃ/ ማርያም ሃሳብ በስተቀር። ወሳኔ ውሳኔ እንጂ የ ዝርዝር አፈጻጻም ሰነድ አይደለም።
ሄሮድስ መለስ ዜናዊ እና የጫካ ባልደረቦቻቸው አንጠልጥለው ሲያነኩሩት የቆዩትን ለዛውም በዓለም አቀፍ ህግ መሠረት ያስያዙትን፤ ያሙረቀረቁትን ነው መልክ እንዲይዝ የተደረገው። አንጡራ የሰው ሃብት የወደመበት፤ አሁንም ሃብት አላግባብ እየባከነበት ያለ ጉዳይ ነው። ወሳኔ ነው መኖርን የሚተረጉመው። የሆነ ሆኖ ልብ ቋት ... ህግ መሆን ሲገባው ዝርያ ከሆነ ቀጣዩም አስፈሪ ነው ... ለዚህ ለዛውም ዛሬ ግብር ይቅረብልኝ ማለት የሰው ጅልነት ነው ... ሁልጊዜ ሰርግ ስሌለ ... ለሞቱ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ የበደነ ራዕይ ጋር ለመቆም? እእ!
[የግድ ሊታይ የሚገባ] በአማራ ቲቪ የህወሓትና ብአዴን ገመና ሜዳላይ ተሰጣ ~ አማራው አምርሯል
„አማራነት ይከበር“
የአማራ ማገዶነት በአስቸኳይ ይቁም!
ከምህረት እንጂ ከቂም በቀል የሚያተርፍ ሰብዕና የለም!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ