የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መኮነን ሜጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ኢትዮኤርትራን በሚመለከት ያነሱት ሃሳብ በሳል ዕይታ ነው።
የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መኮነን ሜጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ያነሱት ሃሳብ በሳል ዕይታ ነው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ማህበረ ቅንነት እንዴት አደራችሁልኝ? እምዬ ኢትዮጵያስ? አባ ቅንዬ አማራስ እንዴት ናችሁ። ከሪፖርተር ያገኜሁት የህወሃት መራሹ የኢህአዴጉ መኮነን ሜ/ጄ አበበ ተ/ ኃይማኖት ብሄራዊ፤ አህጉራዊ፤ ግሎባል ሁኔታወችን ያገናዘበ #በሳል ዕይታ በሚመለከት በዝምታ ባጅቼ፦ ግን እኔ አስቀድሜ የፃፍኩበት ቢሆንም፤ ሃሳቤን፦ ዕይታዬን የሚያጠናክርልኝ ስለሆነ ለሪፈረንስ ይረዳ ዘንድ ሙሉው መንፈስ ከሥር ይገኛል የሪፖርተር ዘገባ። ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት በሳል ዕይታን፤ አስቀድመው ማዬት የሚችሉ ሊቃናት ያስፈልጓታል። ሰሚ ከተገኜ። እኔ በፌድራሉ እና በህወሃት ጦርነትም ጉዳቱን ከመዘገብ ውጪ ምንም አቅም አላዋጣሁም። ለአማራ ታጋዮችም አታበረታቱ፦ ትርፍ የለውም ብዬ ሞግቻለሁኝ። የሆነ ሆኖ ከዬትኛውም ዞግ ይሁን መንፈሱ ጤናማ፤ መጪውን ዕድል የሚወስኑ ጉዳዮችን በአሰተውሎት የሚያነብ፤ የሚተረጉም እንዲህ #የሚያመሳጥር አቅም ያለው ዕይታ #ሊደመጥ ይገባል። ለጤነኛ ኃሳብ ድንበር እና ወሰን አበጅቶ ዕቀባ ማድረግ ብልህነት አይደለም። ከቀደመው አሳቤ እማክልበት እኔ ስፈራ የነበረው የኔቶ እና የራሽያ ፍጥጫን ነበር። ሦስተኛ ዓለም ጦርነትን አማጭ ይሆናል ብዬ ስሰጋ የነበርኩት። አሁን ተመስገን ነው። ፍጥጫው ቢኖርም ውጥረቱን ሊያመጣጥን ወይንም ሊመክት የሚችል አቅም አለ። #ትራንፒዝም ። በሌላ በኩል ይህ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ መነሻው ወደብ፤ የባህር በር የይገባኛል ጉዳይ ይምሰል እንጂ፦ በውስጡ ብዙ የታመቁ፤ #የታመሉም ፍላጎቶች አሉበት። ይህን የአቶ ሽመልስ አብዲሳን ...