ልጥፎች

ከሜይ 9, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ወንዝ፤ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዝ (ቄንጠኛ ዝንጥ ያለ ወግ።)

ምስል
ወ ንዝ፤ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ወንዝ፤ የገባሪ ገባሪ ገባሪ ወንዝ።   „የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት። የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፪   ከሥርጉተ©ሥላሴ   Sergute©Selassie   09.05.2019   ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። አ ልኳችሁ ዛሬ ቪንቲ በስጭት ብላ፤ ወጅብ ስትለቅብን ነበር የዋለችው። እናላችሁ እኔ እህታችሁ፤ ምኔ ሞኝ?! ዋናውን ሰቅሰቅ ጠበቅ አድርጌ ከርችሜ ቁጭ።   ግን እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁን አዱኛዎቼ ። እናንተን አያሳጣኝ ፈጣሪዬ። አሜን!   ቄንጠኛውን ወግ በድምጥ ከፈለጋችሁ ቅኖቹ . .. https://www.youtube.com/watch?v=mc-brGzchX4&feature=youtu.be አ ንድ አገር አንድ መንግሥት ያስፈልገዋል። ያ መንግሥት ግን የውጭጭ ያልሆነ፤ የእጣ እጣ ያልሆነ፤ የአድርሽኝ ያልሆነ ወይንም የሽሙጥ ያልሆነ ወይንም የደርሶ መልስ ያልሆነ ወይንም ባጣ ቆዬኝ ያልሆነ፤ በራሱ ውስጥ የሰከነ። የጸና፣ ለህግ ተገዢ፤ ሚዛናዊ እና ተጠያቂነትን የሚቀበል።   ዘ መኑ የዬሀገሩ መንግሥታት አብዛኙቹ የፖለቲካ ድርጅት አላቸው። በህሊና በሠለጠኑት በውድድር፤ በፉክክር፤ በፍቅር፤ በመቻቻል በምርጫ ተወዳድሮ ያሸነፈ በትረ መንግሥቱን ይይዛል።   እ ንደኛ ያልሆነ ማለት ነው። ያው በዚህ ስሌት ሲኬድ እኛ በዚህ ዘርፍ ደረጃችን እንቁላል ነው። ፍላጎቱን እንጂ መሆኑን ስላልሰጠን። በቃ ማለት ብቻ፤ ማለት አሁንም ማለት፤ ትናንትም ማለት፤ ዛሬም ማለት፤ ነገም ማለት፤ ተዚያ ወዲያም ማለት … የማለት ስንቅ፤ የማለት ጥሪት፤ በማለት ተባዝተን የ ተቀናነስን ።