ልጥፎች

በሴት የፖለቲካ ሊሂቃን የነበረው ተስፋዬ ወደ መቃብር እያሰኘው ነው።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  በሴት የፖለቲካ ሊሂቃን የነበረው ተስፋዬ ወደ  መቃብር እያሰኘው ነው። „የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤  እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ክብርን ያጠፋል።“  መጽሐፈ መክብብ ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.05.2019 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                                                         እውን ይህ ጽናት በምን ሁኔታ ተጠለፈ?                                                     ድምጽ አልባዋ የአማራ እናትም ልጇ                                                      ከቁም ነገር ደርሶ ማዬት ህልሟ ነበር።                                                     "ቃል የእምነት ዕዳ" መሆኑ አክትሞ                                                      የዘመን መጫኛ ሆነ ለዛውም ለሚዛን?                                                     የአማራ እናትም ኢትዮጵያዊት ናት! የመከራ ማጫ! ·        እ ፍታ። ህም! የት መጠጊያ ማግኘት እንደሚቻል አይታወቅም። ውሉ የጠፋበት ዘመን እንደዚህ ገጥሞ አያውቅም። በድምጽ ውስጤ እንዲህም ገልጨዋለሁኝ፡፤ https://www.youtube.com/watch?v=js60nj_SwHo&feature=youtu.be የእናትነት መክሊት ግማዱ በአብይወለማ ሌጋሲ። ( ከሥርጉተ ሥላሴ

"የድምጻችን ይሰማ" ስኬት ተመክሮ ዕድምታ በሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ።

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ  "የድምጻችን ይሰማ" ስኬት ተመክሮ            ዕድምታ በሥርጉተ ሥላሴ           ዕይታ።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“   ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ 07.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዚሻ። ·        መግቢያ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ፧ የቀድሞው ፕ/ ዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አላልሽም። ለምን የሚል ጥያቄ ቀርቦብኛል። ከቶ እንደ እኔ ስለ ግለሰቦች መልካም ነገር የሚመሰክር ጸሐፊ አለን? ማንም እኮ ስሌለው አድንቆ፤ አክብሮ፤ ተበራታልኝ ብሎ አይጽፍም። እኔ ግን ሲሞላ እና ሲጎድል የተፈጠርኩኝ አይደለሁም። እውነት ነው በምልበት ሁሉ እተጋለሁኝ። ለዛውም የማይደፈረውን ሁሉ ነው የምደፍረው። ሰተት ብዬም ነው ፈተና ውስጥ ራሴን እምማግደው። መጠለያ ጥግ ሳይኖረኝ። ስለሆነም እሳቸውን በሚመለከት ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁኝ። ቅሬታዬንም አክብሮቴንም። ኦዴፓ እንኳን ስላደረገላቸው መልካም ነገር አድንቄ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ህልፈታቸውን ሳዳምጥም በድንጋጤ ተውጬ እንዲያውም አንድ ቀን ካደርኩኝ፤ ከተረጋጋሁኝ በኋዋላ ጽፌለሁኝ። አንጀቴ ስስ ስለሆነ አገር ቤት ስለ አንድም ሰው በህይወት አለመኖር ተነግሮኝ አያውቅም። እንደ ጹሁፎቼ እና እንደ ሙግቶቼ ጠንካራ አይደለሁም። ከምትጥብቁት በላይ አዛኝ እና ሩህሩህ ነኝ። ሌላው ደግሞ የማልችላቸው ጊዜያትም ሊኖሩ ይችላሉ። የጤናም ጉዳይ አለ፤ ድካም አለ። እንዲሁም በአመዛኙ ደግሞ እኔ ብዙ አትኩሮት ባጡ፤ ከእይታ ውጭ በሆኑ፤ የትርጉም ዝብት ባለባቸው፤ ባለቤት ባጡ ጉዳዮች ላይ ነው እምተጋው። ያው ድካሜ ግን አመድ አፋሽ ነው።