ልጥፎች

ከኖቬምበር 21, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የጣይቱ መንፈስ ያብባል ገና!

ምስል
ዬሥነ መኖር  ህብርነት  የህሊና ሉዕቅነት፤ ዕውቀት ዕውቅነት። „ዖጽ በሚባል አገር ሥሙ ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበር። ያም ሰው ፍጹምና ቅን እግዚአብሄርን የሚፈራ ክክፋትም የራቀ ነበር።“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ  21.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·       ክብሩ የሆነ ሰላምታዬ። እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ባለመቻል አላገኛኋችሁም። ግን ደህና ናችሁን? ስለሆነም ትናንት ተዘጋግቶ የዋለውን ሁለመና ስከፋፍተው አዳዲስ ዜና አገኘሁኝ። ይህ ዜና እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ መንፈሰኑ አገለብጬ ሆድ ዕቃውን ዘረጋግፌ ተመለከትኩት። በቅድሚያ ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የከተሞች ቀን በጎንደር ሲከበር ያሉትን ትንሽ ላቅርብ። ·       በር። „ ዋናው ዕይታችን ህዝብ መሆን አለበት።   እንደዚህ የሚያምር መንገድ፤ እንዲሁም የሚያምር ሥነ - ህንጻ   ሰው ከሌለበት ሰው መሆን አይችልም።   ዲፍኒሽኑን በርከት ያሉ ሰዎች በቋሚነት ቤት ያደረጉበት ነው እንጂ፤ ከተማ በ ጣም የሚያማሩ ህንጻ ያለበት እና ሰፋፊ መንገድ ያለበት አይደለም። ከተማ ይህ ነገር ያምራል፤ ሰው ኬለበት ግን ወና ነው። በጠራራ ጸሐይ እዚህ ውስጥ መሄድ ያስፈራል።   አንድ ሰው ብቻውን በቀን ብርሃን መሄድ አይችልም። ሰው ከሌለ ውበት መሆኑ ቀርቶ የፍርሃት ምንጭ መሆን ይችላል። ፍርሃት ደግሞ ያለው ጨለማ ውስጥ ነው። በብርሃን ውስጥ...