የጣይቱ መንፈስ ያብባል ገና!

ዬሥነ መኖር 
ህብርነት 
የህሊና ሉዕቅነት፤
ዕውቀት ዕውቅነት።

„ዖጽ በሚባል አገር ሥሙ ኢዮብ የሚባል
አንድ ሰው ነበር። ያም ሰው ፍጹምና ቅን
እግዚአብሄርን የሚፈራ ክክፋትም የራቀ ነበር።“
መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 21.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

·      ክብሩ የሆነ ሰላምታዬ።

እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ባለመቻል አላገኛኋችሁም። ግን ደህና ናችሁን?

ስለሆነም ትናንት ተዘጋግቶ የዋለውን ሁለመና ስከፋፍተው አዳዲስ ዜና አገኘሁኝ። ይህ ዜና እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ መንፈሰኑ አገለብጬ ሆድ ዕቃውን ዘረጋግፌ ተመለከትኩት። በቅድሚያ ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ የከተሞች ቀን በጎንደር ሲከበር ያሉትን ትንሽ ላቅርብ።


·      በር።

ዋናው ዕይታችን ህዝብ መሆን አለበት። እንደዚህ የሚያምር መንገድ፤ እንዲሁም የሚያምር ሥነ - ህንጻ ሰው ከሌለበት ሰው መሆን አይችልም። ዲፍኒሽኑን በርከት ያሉ ሰዎች በቋሚነት ቤት ያደረጉበት ነው እንጂ፤ ከተማ ጣም የሚያማሩ ህንጻ ያለበት እና ሰፋፊ መንገድ ያለበት አይደለም። ከተማ ይህ ነገር ያምራል፤ ሰው ኬለበት ግን ወና ነው። በጠራራ ጸሐይ እዚህ ውስጥ መሄድ ያስፈራል። አንድ ሰው ብቻውን በቀን ብርሃን መሄድ አይችልም። ሰው ከሌለ ውበት መሆኑ ቀርቶ የፍርሃት ምንጭ መሆን ይችላል። ፍርሃት ደግሞ ያለው ጨለማ ውስጥ ነው። በብርሃን ውስጥ ፍርሃት የሚወጣው ብርሃን መሆን ሲሳነው ነው ማለት ነው። ስለዚህ ዕይታችን ሰው ላይ መሆን አለበት።

 

በ2009 የከተሞች ስብበሳባ በጎንደር ከተማ ዶር አብይ አህመድ /አሜኑ/ ከተናገሩ የወሰድኩት ነው። እኔ ደግሞ በ2009 መጨረሻ ሥማቸው በውል በፖለቲካው መስክ ጎልተው ሳይወጣ „ከመለሳውያን ወደ ለማውያን“ በሚል የኢሳቱ ጋዜጠኛ በዓይኔ ስለመጣብኝ አቶ ማሰረሻ አለሙ ሃሳቡን ለመሞገት በአብይ ኬኛ 6ኛውን ክፍል ሳጠናቅቅ በዚህ ሃሳብ ሞግቼው ነበር። የዕለቱም መነሻዬ የኢትዮ አፍሪካን መናህሪያ "የሰው መኖር በራሱ ጠሐይ ነው" የሚሉትን የጠ/ሚር አብይ አህመድ ፍልስፍና ከመስከረሙ የኦነግውያን በዬዘመናቱ ከሚነሳው ለውጥ አገር ተዛማጅ ከሆነው የተለምዶ የማሰናከል ግርግር ጋር አዛምጄ በሰሞናቱ አዲስ የአዲስ አበባ የተስፋ መንደርነት ጋር አገናኝቼ እምለው ይኖረኛል - ዛሬ።

 

„በብርሃን ውስጥ ፍርሃት የሚመጣው ብርሃን መሆን ሲሳነው ነው።“ ይህን ተጻረው ነው 5 የኦነግውያን መንፈስ ራህብተኞች ፍርሃትን በጠራራ ጠሐይ ያወጁብን። ቀኗም የደም ግርዶሽ እንድትለብስ የተደረገው። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነውም፤ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ“ የሚለውን ዘመን ተሻጋሪ የተስፋ በር አንባርም ቆፈን አላብሰውታል። ቆፈኑ አሁንም ድርስ ገና አለቀቀም።


ትንሽ ዘና ያለ መንፈስ ያዬሁት የሰሞናቱ የፍቅር ሩጫ ቀን እና የታላቁ ሩጫ ሁለት ሰንበቶች ወጣቶቼ ፈታ ያለ ገጽ አሳይተዋል። ከመስከረም ደመመን ወዲህ እንደ ማለት። ተመስገን! ያን የሰኔ 16 ፍስሃቸውን፤ ተስፋቸውን፤ ሐሴታቸውን የመስከረም የታቀደ ግርግር ነጥቋቸው ክው ኩምሽሽ ድርቅ ብለው ነበርና አዲስ አበቤዎች።

 

እኔ ዲኮር ሳይሆን ውስጥን አስተውሎ የማዬት ፈቃድ ነው ያለኝ። የ27 ዓመቱ የስጋት ዘመን በምንም ሁኔታ አቅም እንዲኖረው አልፈቅድም። ኦነግውያን ደግሞ አይደክማቸውም ለውጥ መጣ በተባለ ቁጥር ያው የታቆረ ሃሳባቸውን ይዘው ብቅ በማለት የቅኖችን የውሃ ልክ ያናጋሉ። የቅኖችን የመሠረት ድንጋይ ይነቅላሉ፤ ያስነቅላሉ። የተፈጠሩበት ይኸው ነውና። እነሱም አያረጁም ዘመኑም አያረጅባቸውም። የሚገረመው ነገር ይኸው ነው የ66ቶች ዛሬም አሉ እንዳሉ ሙጭጭ ብለው ከፍቅር ወንበር ጋር።

 

ከላይ በመግቢያው ላይ የለጠፍኩት አገላለጽ ዶር አብይ አህመድ „ሰው ጸሐይ“ ነው ያሉትን ታላቅ ፍልስፍና ለማጠዬቅ ነው። የሰው ልጅ መንፈስ በማስበርገግ የሚታወቁት ጸረ ኢትዮጵያ ድርጅቶች ደግሞ በዬዘመኑ የጸላዬ ሰናይ ስብክታቸውን እያደቡ መቼም አይታክቱም ይዘው ከች ይላሉ ወፍ ቀናኝ ባሉበት ጊዜ ሁሉ፤ ተጥለልው ይሁን ተጠግተው። 


ለአሁኑ ዘመን ደግሞ ማርከሻው ከእዛው ከመዲናዋ አለላቸው። በላቀ መንፈስ አፍሪካዊነትን አጉልቶ ለማበልጸግ ታጥቆ የተነሳ። ከተማ የከተሜ ፍልስፍናን ያነገበ ነው። ገጠር ደግሞ የገጠርን ፍልስፍና ያነገበ ነው። አመሰረራታቸውም እንደ ተፈጥሯቸው ነው። ሁለቱ የራሳቸው ማንነት የአፈጣጠር ሥነ አመክንዮ አላቸው። ሁለቱ ሲደመሩ አገር ይሆናሉ ከተሜው እና ገጠሬው። ይኸ ነው ተፋልሶ ሲነገር የሚደመጠው በኦነጋውያኑ ዘንድ።

 

·      መንፈስ ማስኪያጃ።


 https://www.youtube.com/watch?v=Pqr8Ha_Prk8

Abiy ahmed speech at Gonder part 2

https://sergute.blogspot.com/2018/05/05.html

 

አብይ የኢትዮጵያ ፍላጎት! ማጠቃለያ
Ethiopia: / አብይ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያልተጠበቀ ንግግር አደረጉ
|Dr Abiy Ahmed
Published on Nov 20, 2018

·      ቃል እና የሙሴው ፍልስፍናው።

 „ሃሳብ መሆኑ የሚታወቀው በቃል ሲገለጽ ነው። ቃል ካልወጣ በአእምሮ ውስጥ ብቻውን ቢብሰለሰል ሃሳብ ሊሆን አይችልም፤ ቢሆንም ለባለቤቱ ብቻ ነው የሚሆነው። ቃል ጉልበት አለው። ይተክላል፣ ይነቅላል። ትውልድ ይፈጥራል፤ ትውልድ ያጠፋል። ፍቅር ይዘራል ጥላቻን ይዘራል። በቃል ውስጥ ብዙ መማር ብቻ ሳይሆን፤ ሐገርንም መሥራት ይቻላል።“ 

„ኢትዮጵያ የፈረሰችውም የተሠራቸውም በቃል ስለሆነ። ሁለቱንም ነገር ለመለማመድ እንደዚህ ዓይነት ፓብሊክ ስፒች ሰዎች ሃሳባቸውን ኦርጋናይዝድ አድርገው ለብዙሃን ሸር የሚያደርጉበት መድረክ ማግኘት ለእኛ ትልቅ ዕድል ነው።“

ተመስገን የሚያሰኘው አሁን ይኽ ቅን መንፈስ አይለም ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ ታላቅ መኩሪያ እና ተስፋ እዬሆነ ነው። በትረ ሥልጣኑ መንበሩ ላይ እጬጌነቱን ብአዴን ስለሳከለት ወይንም ስለ አሟሻለት። 

ለአፍሪካ ሴቶችም ሆነ ወጣቶችም አንባሳደር ነው። በቃል ውስጥ ኢትዮጵያ እንዳትነቀል ኢትዮጵያን በጥርሳቸው ከያዙት ጋር ፍልሚያ ላይ ነው አሜኑ። ያሸንፋልም። ስለምን? ኢትዮጵያዊነት አፍቅሮ አክብሮ የወደቀ ዘመንም የወደቀ መንፈስም የለም እና። ኢትዮጵያዊነት ጠላቶችን አፍርሶ ለመኖር የተፈጠረ ሚስጢር ነው። ሁሉ አለቀ እና ኢትዮጵያም አፍሪካም ካለ መዲና ለማስቀረት ነበር አራተኛው ጦርነት መስከረም ላይ በ አደባባይ ይፋ ሆኖ የተከፈተው። ግን እንሆ ከሸፈ። ተመስገን።  

·      ምኞቴ የእኔ ቢሰተካካል።
እርእሱ መሰጠኝ አልትሜት ፋክት ዩቱብ ሲለጥፍ የተጠቀመበት። እንዲህም ይላል ..
Ethiopia: / አብይ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያልተጠበቀ ንግግር አደረጉ

ሌላ ቦታ ደግሞ ይህንኑ ንግግር ወስዶ /ሚር አብይ አህመድ ለዶር ደብረጽዮን /ሚኬኤል መልስ ሰጡ ይላል።

በቅድሚያ ዩቱብ ላላቸው ወገኖቼ በትህትና ላሳስባቸው እምሻው እውነቱን ሃቁን ብቻ መግለጹ ይበጃል። እጅግ የሚገርሙ እርእሶች ነው የሚሰጠው። ባለቤቱ ሲለጥፍ ካደረገው ሌላው የቀዳው የሚሰጠው ሥም የሚገርም ነው። እርእሱ ስለተጋነነም ስለኮሰሰም ነፍስ ላላቸው አድማጮች፤ ምራቁን ለዋጠ ፖለቲከኛ ለውጥ የለውም። ምክንያቱም ውስጡ እንጂ ቅርፊቱ ምንም ስላልሆነ።

ተግባር እና የፖለቲካ ሊሂቅነት ስለተኖረበት ዛሬ ማንም ምንም በብልጥነት አባጭሎ የመንፈስ ጌታ የሚሆንበት ዘመን አክትሟል፤ ባልተፈጠሩበት ለመኖር ለወሰኑት አክሮባቲስቶች አቅል የለም።
እርግጥ ነው ዕለታዊ ድጋፍ ሊኖር ይችላል። ያ ግን ጎርፍ፤ የሳሙና አረፋ ወይንም ጤዛ ነው። ምክንያቱም መሰረታዊ አቅም ስለሆነ ቋሚ እና ዘላቂ ደጋፊ ሊያስገኝም ሊያስነሳም የሚቻለው። አቅሙ ከሌለ አክሮባቲስትነቱ የውርንጫ ድካም ስለሚያደርግም። አሁን እኔ የዕለተ ሰኞ የተስፋ ጠባቂ ሆኛለሁኝ።

ምክንያቱም ዕለተ ሰኞ ከጠ/ሚር ጽ/ቤት መልካም የምሥራቾች ያልተሰሙ እሸት የተስፋ ሃሳቦች ስለሚደመጥበት።  አዲሳዊነት በዬማዕለቱ የራሱን መጸሐፍ እዬጻፈ ነው - በምድሪቱ  በኢትዮጵያ። ተመስገን። በቀደመው ጊዜ በበ10/15 ዓመትም አንድም አዲስ ሀሳብ ተደምጦ አያውቅም ነበር። አሁን እኮ ዋጠን ብንል እንችላለን። ዕለቱ በ እሸታዊ ሃሳብ የታሰሰ ነው። የከበረ ነው። የተዋደደ ነው። 

በአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሏዊ አብዮት ቆሞ የሚጠብቅ አምክንዮ ዓለም አስተናግዳ እንደማታውቅ ጽፌ ነበር። ሳተናው/ ኢትዮ ሪጅስተር ላይ ይገኛል። ማህበራዊ ንቃተ ህሊና ዘመኑን የፈቀደ ሲሆን ነው ተደማጭ መሆን የሚችለው፤ ታዲያ የቀሰማ ካልሆነ ብቻ። ምክንያቱም አንቴናችን ቀጥ አድርግን እምንከታተል ስላለን። አዳልጦ መኖር አክትሟል። የተሻለ ሃሳብ እኮ እንደ ፆም ውሃ ሆኖ ባጅቶበትን አሁን ደግሞ እሸታዊ ዕሳቤ ዕለታዊ ስንቅና ትጥቃችን ሆኗል። ተመስገን!
·      የጥዋቱ ባለጉዳይ ወግ።

ስለ አዲስ አባባ እሸት ተስፋ አልትሜት ፋክት ዩቱብ ላይ ያገኘሁትን ንግግር ሆድ ዕቃውን ዘረጋግፌ ለማዬት ይረዳኝ ዘንድ የማለዳ ኩትኩቴ አድርጌ 7 ጊዜ ለ70 ዲቂቃ ይህል አዳመጥኩት። እንዚህን መሰል ቋሚ የተስፋ ማህደር ፕሮጀክቶች አዲስዬ ላይ መታቀዳቸው መንግሥት በማሳወቁ እረገድ አዲስ አባባ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች አደባዊ አድማጭነትን አስተውያለሁኝ።

ይህን መሰረታዊ አብቃይ መንፈስ ግን ማዘግዬት የተገባ አልነበረም ባይ ነኝ። ይህን ስል ተስፋ ከእጅ እስኪገባ ስለመሆኑ ባለመረዳት ሳይሆን፤ የኗሪው የእኔነት መንፈስን ማነጽ ከመጋቢት 24 ቀን ወዲያ ታቅዶ የተከወነ አወያይ መድረክ ስላላዩሁ ነው።

ሰው መጀመሪያ የእኔ የሚለው እራፊ መሬት የሚቆምበት ይሻል። አሁን የእኔ መኖሪያ ቤት የእኔ ነው፤ ሲዊዞችም የእኔን ያህል በቤቴ ውስጥ ያለኝን ያህል መብት ነው ያላቸው። እኩል። አዲስ አበባ ላይ ግን መጣንብህ ነው በዬዘመኑ … በኦነግውያን መንፈሱ የተፈናቀለ ህዝብ ነው ያለው። ይህ ዕውነት መደፈር አለበት።

የአዲስ አበባን እድገት ለእኔ ሁለተኛ ደረጃ ነው የምሰጠው። የሰው ልጅ ቀዳሚው ሰው መሆኑ ዕወቅና ማግኘት አለበት። እድገት መልካም ነው ይህ ለእኔ ቁሳዊ ነው። ቁሳዊው ጉዳይ መንፈስን ይቀልባል ቢባል ሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ መጥታ ተቀብራ ባልቀረች ነበር። 

እጅግ የማይታሰቡ ዕድሎችን ጉልት አድርጋ ነው ሲዊዝ ስደተኛ ካንፕ እንድትገባ ያስወሰናት። ረዳት አውሮፕላን አብራሪ የሖንስ ተስፋዬም ከፓይለትነት ወደ ግብርና ያመጣው የመንፈስ ልዕናን አላስደፈርም ከማለት ነው። የብዙ ወጣቶች ራዕይ ነው ፓይለትነት መሆኑ ይታወቃል። ጀግናውና እና ብለሁ አስተዋዩ ረ/ አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ያን የልጅነት ምኞቱን ያወረረድበት ሁነት ነጻነትን በማስቀደም ነው። ባርነትን ለማያውቅ ህዝብ የመንፈሱ ነፃነት ቀዳሚው አውራው በኽረ ልዕልናው መሪ ማህንዲሱ የኑሮም ማህንዲሱ ነው።  

በቁሳዊ ሁኔታ የሚገኙ ተረፈ መንፈሳዊ ዕሳቤዎች ቢኖሩም መቀመጫ የሌለው ስለ ዴሞክራሲ እና ስለ ዛሬ ሦስት አራት አምስት አስር ዓመት ያስባል ለማለት የሚከብዱ ነገሮች ይኖራሉ። ስለምን“ ሰው የሃሳብ ውጤት ስለሆነ። እግዚአብሄር ሰውን ሲፈጥር አስቦ ነው። በፕላኔታችን ያሉ ነገሮች ሁሉ ከሰው ጀምሮ የሃሳብ ውጤቶች ናቸው እና። ሃሳብ ደግሞ የመኖርን ነጻነት ይጠይቃል። ሰው እንዲያሰብ ነፃነት ሊኖረው ይገባል። 

ስለዚህ አዲስ አባባን በሚመለከት የእኛነት ሃሳብ አለ። ያ ሃሳብ ትናንትም ዛሬም ወደፊትም የሚኖር ነው። ያን ሃሳብ ለማፈናቀል ለማፍረስ የተነሳ ሃሳብ ደግሞ አለ የኦነግውያን። ገና ያልሰከነ ዕድሜ ልኩን የጫጫ እና የማያድግ ባለህበት እርገጥ የሆነ። ጮርቃና ከታቱም ፈቅ ብሎ የማያውቅ

"ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል" ይላሉ ጎንደሬዎች፤ ከአሜሪካ ወደ አገር ቤት የሄዱ ቤተሰቦች ነበሩኝ። እና አዲስ አባባን እንደ ትራንዚት አድርገው በቀጥታ ነው ወደ ጎንደር የበረሩት። አላደሩም አዲስ አበባ። ስለምን? ሃሳባቸው ስለተናደ፤ ሃሳባቸው ፈተና ስለገጠመው፤ ህልማቸው እንዲሰቃይ ስለተፈረደበት። እዛ ቢውሉ ቢያድሩ ሆቴሎች፤ ታክሲ ነጂዎች፤ ሱቆች፤ ፈርማሲዎች ይጠቃሙ ነበር።

ሥርጉተም ኢትዮጵያ ለመሄድ ብትፈልግ የምታደረገው ይህንኑ ነው። ይህን እሷ ስታደርግ ለእህቶቿ ልጆች ግን እያሰበች እያለቀሰችም ነው። እህቷ ልጆቿን ወልድ አሳድጋ ለቁምነገር የባቃቻቸው አዲስዬ ላይ ነው። ልጆች የእህቴ ልጆች በእናታቸውም በአባታቸውም ጎንደሬዎች ናቸው። ልጆቹ ጎንደርን እራሱ አያውቁቱም። አሁን ሁለቱ አሜሪካን ነው የሚኖሩት። ኢትዮጵያ ቢሄዱ አንዱ ወንድማቸው እና ወላጅ አባታቸው ቤት ሠርቶ ወደ ሚኖርበት አዲስ አባባ ነው። እነሱ ብሄር አልቦሽ ናቸው። አሁን የኦነግውያን አስፈሪ መንፈስ የት ላይ ተቀመጥ ይባል ነው ችግሩ።

እኔ መጸሐፍቶቼን ሳሳትም 6ኛው መጻህፌ ላይ የአርሲ ባህላዊ ልብስ የለበስኩት ፎቶ የጀርባ ሽፋን ነው። 6ኛው መጸሐፌ የተስፋ በር ይባላል። የተስፋ በር ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ያሳድጋሉ የሚል በዲዛይን የተጻፈ መጸሐፍ ነው። እናቴም ከላኩላት መጸህፍት እጅግ የምትወደው ፎቶ ይህን ነው። አልፎ አልፎ ከጹሑፎቼ ጋርም አውጣዋለሁ ይህን ፎቶዬን አሁን ከመስከረሙ የኦነግውያን ግርግር በኋዋላ ግን መንፈሴ አልፈቀደም።

እኔ የእኔ ስል እነሱ የእኛ አይደለሽም እያሉ እንዴት ከባህል ጋር መዋህድ ይቻላል የሚል የህሊና ሙግት ላይ ነኝ። ለዛውም ሥርጉተ በኦሮሞ ሊሂቃን አቀንቃኝነት በይፋ የተከሰሰች፤ በብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ራዲዮ እና ድህረ ገጽ የተከሰሰች፤ የተነገላታች፤ የተገለለች፤ የተሳደደች፤ ፍዳዋን የከፈለች በዘመነ ኦሮሞ ዘመንም እዬተገፋች ያለች ሴት ስትሆን መንፈሱ እራፊ ማረፊያ ያጣል።

የዶር ለማ መገርሳ እና የዶር አብይ አህመድ አዲስ አባባን በሚመለከት ያላቸውን አቋም ለመፈተሽ ጊዜ ወስጄ የምከታታለው ጉዳይ ነው። ምክንያቱም እነሱን መሪዎቼ ብዬ የወጣሁት የዛሬ ዓመት ስለሆነ የእነሱ አቋም አሉታዊ ከሆነ ሁለመናዬን ያቆስለዋል ያከስለዋልም ያፈርሰዋልም።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሲመጡ ወደፊት የብላቴ ሎሬት ጸጋዬን ኢትዮ አፍረኪኒዝምን ተጻረው ኦነግውያን ይሆናሉ የሚል ግምት አልነበረኝም። እስከ የኦሮሞ ወጣቶችን ብቻ ሰብስበው አዲስ አበባ ላይ እስኪያወያዩ ድረስ። አሁን እኔ ከሳቸው እምጠብቀው ፋይዳ አይኖረኝም። አዳምጫቸውም አላውቅም። በበቃኝ ትቸዋለሁኝ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች በዬዘመኑ የዘመኑ እሳት እራት ናቸው። ነበልባሉ ነዶ በጭንቅላታቸው ላይ አመድ የሆነ ነው። አሁን ያ እንዲደገም ፈጽሞ አልፈቅድም። ነገ የወጣቶች ነው። በእነሱ ማህል ልዩነት መስማትም፤ ማድመጥም፤ ማዬትም አልሻም። ብላቴው ሎሬቱ ታቦቱም በጽረ አርያም መንፈሱ ይህን ይጸዬፋዋል።

አሁን ባደመጥኩት በዚህ በዶር አብይ ንግግር ትንሽ መንፈሴ የተሻለ እረፍት አግኝቷል ብዬ አስላለሁኝ። ጥሩ ንግግር ነው። እኔ የቁስ ሰው ስላለሆንኩኝ ለመንፈስ የሚሆን ስንቅ አቀብለዋል ብዬ አስባለሁኝ። ለዚህም ነው ድህነቴን ወድጄው ሲዊዝ የምኖረው። 

አዲስ አባባ በእኔ ዕምነት የኗሪዎቿ ናት። አዲስ አባባ እንደ ሌሎች ሜትሮፖሎ ከተሞች የራሷ ማንነት ያላት፤ ሁለመና እና ሁለገብ የሁሉም ከተማ ናት። አዲስ አባባ መላ አፍሪካ፤ መላ የሰው ዘር መዲናችን የሚሏት ሉላዊ ከተማ ናት። አዲስ አባባ ነፃነቷ በማናቸውም ሁኔታ ሊከበርላት ይገባል። 

አዲስ አባባ ልክ እንደ ሲዎዞች በርን፤ ልክ እንደ አሜሪካኖች ዋሽንግተን ዲሲ፤ ልክ እንደ እንግሊዞች ለንደን፤ ልክ እንደ ፈንሳዮች ፓሪስ፤ ልክ እንደ ጀርመኖች በርሊን፤ ልክ እንደ ዴኖች ኮፐን ሃገን፤ ልክ እንደ ሲዎዶኖች ስኮትሆልም እርዕስ መዲና ብቻ ሳትሆን እናት ናትሰብሳቢ፤ አዛኝ፤ አጽናኝ እና አቃፊ፤ እንዲሁም መግቢያ መናህሪያ አናትም ከተማ ናት። መንፈሷን ለመሸርሸር፤ ለመሸራረፍ የሚከድበት መንፈስ ግን ዓለም ዐቀፍ ህግጋትንም የሚጣረር ነው። አዲስዬም ዲሞክራሲ ራህበተኛ ናት። 

ልማቷ፤ ዕድገቷ፤ ብልጽግናዋ ሉላዊ ነው። ሉላዊነቷ ደግሞ የዛሬ ሳይሆን የቀደመ የኖረ የነበረ ነው። ታዋቂ ገናና ከተማ ናት። በአንድ ከተማ የተለያዩ ማህበረሰቦች ይኖራሉ። አሁን እኔ ያደግኩበት ከተማ ጎንደር አንባጅኔ የኤርትራውያን መኖሪያ ነው። 

አንባጅኔ አንድ የመኖሪያ ቦታ ነው ልክ እንደ ደብረ ምቅማቅ፤ ልክ እንደ አብይዝጊን፤ ልክ እንደ እንኮዬ መስክ፤ ልክ እንደ አደባባይ እዬሱስ፤ ልክ እንደ ጨዋሰፈር፤ ልክ እንደ ጡረታ ሰፈር፤ ልክ እንደ ቆብ አስጥል፤ ልክ እንደ ፊት እና አጣጣሚ ሚኬኤል፤ ልክ እንደ ቀሃ እዬሱስ፤ ልክ እንደ አዲስ ዓለም፤ ልክ እንደ ቸቸላ፤ ልክ እንደ ቀሃ እዬሱስ፤ ልክ እንደ ቁስቋም ወዘተ እና አባጃኔ ያሉ ኤርትራውያን ጎንደር ላይ አባጅኔ የሚኖሩ ኤርትራውያን ጎንደር ኤርትራውያን ናት ሊባል ነውን? ጎንደር ሥሟ ተቀይሮ አንባጅኔ ሊባል ነውን። ያው ኤርትራም  ዬኢትዮጵያ አካል ስለነበረች ማለቴ ነው። የዛሬውን ሰው ሰራሽ የዳቦ ቆረሳ ነገር ርስት ብናደርገው ማለት ነው።

እንዲያውም ለእኔ አዲስ አባባ ከሚለው ፍጽምና ድንግልና በላይ ታላቅ ብሩህ የተስፋ የራዕይ የመልካም ምኞት መግለጫ ሥምም የለም። አበባም አበባ ነው አዲስም አዲስ ነው። አዲስ አባባ አዎንታዊ የተስፋም ዜና ነው። አዲስ አበባን የአንድ ሠፈር ሥያሜ ልኳም ደረጃዋም ሊሆን ከቶም አይችልም። 

አዲስ አባባ የአንድ ብሄር ይሁን የአንድ ብሄረሰብ መናህሪያ አድርጎ ማሰቡ ራሱ አንጎልን ይፈትሻል። ሰው መሆንን ይፈትናል። ስለምን አዲስ አበባ የሉላዊ ዓለም ክፍለ አካልነቷ ጉልላት ስለሆነ። አዲስ አበባን የሠፈር ሥም ፈጽሞ አይመጥናትም። ሥልጣኔዋም ዕድገቷም መንበር ነውና። አዲስ አበባ የሁሉም ናት። ማንም ሰጪ፤ ማንም ነሺም የለም። ማንም ምርጥ ዜጋ ማንም ተርታ ዜጋም የለም። የዜግነት እርቦ እና ሲሦም የለም። 

በመክፍቻቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ አዲስዬን ጉላ ወደድ አድርገው ስላቀረቧት እጅግ አድርጌ አመሰግናችዋለሁኝ። ሰንበት ላይም የአፍሪካ ህብረት 11ኛው አስቸኳይ የመሪዎችን ጉባኤ ሲጠናቀቅም ነዋሪዎቿን በፍቅር አክብረው „በአችን“ አመስግነዋል። በዚህ አካሄድ ከሳቸው የምፈልገውን የመንፈስ ሙና አግኝቻለሁ።

ቀሪ የቤት ሥራ ግን ይቀራቸዋል ዶር አብይ አህመድን ማለቴ ነው። ዶር መራራ ጉዲና ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዲስ አበባን በሚመለከት ከ5 ኦሮሞ ድርጅቶች ጋር በመሆን ኦፌንኳውያን አቋሟቸውን ጊዜ ሰጠን ብለው አሳውቀውናል፤ አሁን ሸብልል አድርገው „እንደ አጋጣሚ ሆኖ አዲስ አባባ በኦሮምያ ክልል ስለምትገኝ“ ብለውናል። በሽዋ ክ/አገር እኮ ነው አዲስ አባባ የምትገኘው። ሽዋ ደግሞ የኦሮሞ ብቻ አይደለም የጉራጌው፤  የኦሮሞው እና የአማራው ነው።

እርግጥ ነው አሁን ዘመን አመጣሹ ባንዳዊ ውርስ እና ቅርስ ክልል የወያኔ ሃርትንት ትግራይ እና ኦነግ ጋብቻቸውን የፈጸሙት ጣሊያን የሰጣቸውን የሽንሸና የትውስት መንፈስ በማስተናገድ ነው። ስለሆነም ነው ጌታቸው ጣሊያን የሰራላቸውን ሞዴል ነው የተከተሉት። የሚገርመው ይመኩበታልም። አንዲት በነጻነት የኖረች የአፍሪካ ርዕሰ የነጻነት አንባ፤ የጥቁሮች የነፃነት ፈርጥ  አሁንም የጣሊያን መንፈስ ውርስ ቅርስ አድርጎ መቀበል በራሱ ተጨማሪ ቅኝ ተገዥነትን ባርነት መፍቀድ ነው። ክልል የሚባል ኖሮ አያውቅም ከጣሊያን ከተረከቡት የባንዳ መንፈስ ውጪ ባለሟሎች በስተቀር።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደረግ የአዲስ አባባ ማደግ እና መበልጸግ  የዓይን ሳቢነት እና ማራኪነት ያጓጓው የወያኔ ሃርነት ትግራይም ይህን ዕውን ለማድረግ 27 ዓመት ጥሯል። የአዲስ አባባን ዓወደ ምስል ለመቀዬር ግን አልተቻለውም። ወደፊትም ኦነግውያን ያን ቢሞክሩት ይወድቃሉ። ለነገሩ እነሱ ከመወደቅ ውጪ አልፈው አያውቁም። የአሁኑ ጦርነትም መወደቅን ለመቀበል አለመፈቅድ ነው። ሌላው እራሱን ሸጉጦ ካኖረበት ሳጥን ውስጥ ለመውጣት የሃሳብ አቅም ማነስ ነው። በትርጉም ሲቃና አጓጉል የሥልጣኔ ጠቃጠቆ ይባል። 
·      የቤት ሥራ ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ቢችሉ መልካሙ መንገድ።

ከመንፈስ መነሳት። መንፈስ ንደት ተፈጥሮበታል። መንፈስ ተቀናቃኝ አረም ተፈታትኖታል መዲናዋ ላይ። ስለዚህ በቀጣይም ጠ/ሚር አብይ አህመድ የአዲስ አበባ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ባለቤት ስሌላቸው ባለቤታቸው ሆነው ሰብስበው ማወያዬት ይጠበቅባቸዋል፤ ነዋሪዎችንም በዬቦታው እንዳደረጉት እንዲሁ፤ በተጨማሪም የአዲስ አበባን ሊሂቃንን በሚመለከት ባሊህ ያልተባለ በቴሌቮዥን ሞደሬተሮች ብቻ ነው ተሸብልሎ የሚገኘው። ይህ የታሪክ ግድፈትም ጉድፍም ነው።

መቼም ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለአዲስ አበባ ወጣቶች ባለቤታቸው ናቸው ብለው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደማይተረቡኝ ተስፋ አደርጋለሁኝ። ኢንጂነሩ ተጠሪነታቸውም ለኦዴፓ ነው። አዲስ አበባን እዬመሩ የኦዴፓ የማዕከላዊ ምክር ቤት አባል ነው የሆኑት። ሎጅኩ አያስኬድም።

አዲስ አበባን በመንፈስ ተጠማኝ እና ጥገኛ ያደረገ እጅግ አውራጅ እርምጃ ነው። መዲናነቷን የሳተ ያሳነሰም ውሳኔ ነው። ተጠሪነቷ ለ አዳማ። ይገርማል እስከ ወዲኛው? አዲስ አባባ በራሷ ጉባኤ፤ ምክር ቤት እንጂ በጥምር የበላይነት ልትተዳደር ከቶውንም አይገባም። የተፈላሰ ነው አካሄዱ። ከመርህም አንጻር አያስኬድም። መንበረ ሥልጣኗን የአዲስ አበባን የተዳፈረ ነው የ ኦዴፓም የምክር ቤት አባል ጊዜያዊ የ አዲስ አበባ ም/ ከንቲባ አድርጎ መሾም። 

እርግጥ ለመሸጋገሪያነት ሊሆን ይችላል። ይህን ብአዴን በዝምታ ሊያው ከቻለ አዲስ ጦርነት መጠበቅ ይኖርበታል ብአዴን ራሱ። ዝምታ ጌትነት አይደለም። ጌትነት ለነፃነት ቆርጦ እና ወስኖ መታገል ነው። ማቄን ጨርቄን ሳይሉ። ብአዴን በራሱ መንፈስ ውስጥ መቆም ይኖርበታል። 

ጠ/ሚር አብይ አህመድም ቢሆኑም የአዲስ አባባ ህዝብ ለሰጣቸው አቻ የለሽ ፍቅር እና ራሱን ገብሮ፤ አካሉን አጉድሎ ላጎናጸፋቸው ልዩ የሰማይ አክብሮት ለዚህ ህዝብ አንባሳደሩ ሊሆኑሉት ይገባል ባይ ነኝ። መሪው ብቻ ሳይሆኑ የበላይም ጠባቂው መሆን እንደ ማለት።

ነፍሰጡር እናቶች አሉ በዚህ ዓመት አዲስ ልጃቸው የአዲስ አባባን ኗሪነት የሚቀላቀሉ፤ እነሱ የሥነ - ልቦና ጦርነት ታውጆባቸዋል ገና ከመፈጠራቸው በፊት ህጻናቱ ጽንስ ላይ እያሉ። ደሙ ያልረጋ ጽንስም በዬለቱ ይጸነሳል። አዲስ አበባ ላይ የሚወለዱ ህጻናቱ የእኔ የሚሉት የትውልድ ሥፍራ የላቸውም። ስለዚህ እኔ እምለምናቸው ጽንስ ውስጥ ላሉ ድምጽ አልባዎቹ ህጻናት አይዛችሁን ለመስጠት መፈቀድ ግድ ይላቸዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ። እናት ከተጽናናች ጽንሱም ይርጋ ይላል። 

ሌላው የማያውቁት ነገር የጉራጌ እና የአማራ ህዝብ ከርስቱ ሲፈናቀል በልቡ ምን እንዳለ ማንም ሊያውቀው አያችልም። ይህ ደግሞ ሌላው ፍንጂ ነው ጊዜ ጠብቆ ሊፈነዳ የሚችል። ዝም ማለት መስማማት ማለት አይደለም። 

እኔን ፈተነኝ ብዬ ስናገር ለጫዋታ ሟሟያ አይደለም። ከራስ በላይ የሚቀድም ነገር ነፃነት ብቻ ነው። ለዚህም ነው እኔ ነፃነቴን አስበልጬ ድምጼን በዬዕለቱ ማድመጥ የምትናፍቀውን እናቴን በሯን የከረቸምኩባት። ይህ ውሳኔ ከባድ ነበር። ግን አድርጌዋለሁኝ። ነገረ አዲስ አባባ እኔን የመንፈስ ጉለበታም አቅም አለኝ የምለውን የፈተነኝ ሌላውን ብዬ ሳስብ መገመት አይቸግረኝም። እኔ ሥርጉተ ሥላሴ "መዲና ከተማ የለሽም፤ አለኝ ብትይ፤ በትውስት ነው" እዬተባልኩኝ ነው። ስንፈልግ ብቻ እኛ ካሻን ብቻ? ህም ነው።

ይህ ዕውነት መደፈር አለበት። አዲስ አባባ የሁሉም ናት። የአንድ ብሄረሰብ ብቻ አይደለችም። ሃቁ ይህ ነው።  

ስለሆነም ማህጸን ውስጥ ለሚኖሩ ህጻናት፤ ጋብቻቸውን ለሚፈጽሙ ወጣቶች፤ ለመጸነስ ላሰቡ እናቶች፤ ሰኔላቸውን ቹቻቸውን አዘጋጅተው ለተቀመጡ የዕድሜ ባለጸጋዎች ሁሉ የመኖር ዋስትና ሊሰጣቸው ይገባል። „የኢትዮጵያ ሱሴ ነውን“ ቀንበጥን የጨነገፈ ያስጨነገፈ አቋም ነው ኦነግውያኑ ያላቸውና።

በዚህ ላይ የጠ/ሚር ቢሮ ይህን ይወጣል ለማለት አልደፍርም። ከዚህ የመንፈስ እርካብ ጋር ያለው ቀረቤታ መስከረም ብዙ አስተምሮኛል እና። ብሄራዊ የመሆን አቅም ያነሳቸዋል የ ኦነግውያን መንፈስ የተጋባባቸው ሊሂቃኑ። ኢትዮጵያዊነት እኮ የሚጨለጥ የቢራ ኮረፌ ሳይሆን ደም ነው። ስለዚህ ጠ/ሚር አብይ እራሳቸው በስማ በለው ሳይሆን መንፈስን ወደ ቀደመው ትውፊቱ የመመለስ ኢትዮ አፍረካዊ ሃላፊነት አለባቸው። የተግባር እርምጃም እጠብቃለሁኝ።

የአዲስ አባባ ልጅ ብሄር የለውም። አዲስ አበቤ ናሙና ነው  ለኢትዮጵያዊነት። በዬዘመኑ ይገብራል አዲስ አበቤ፤ ነገር ግን ባለቤት ጽኑ፤ ቋሚ የሆነ የእኔ የሚለው ዋቢ ከቶም አግኝቶ አያውቅም፤ አሁን እኔ አለሁኽ ሊሉት ይገባል ዶር አብይ አህመድ። ይህ ከብሄራዊ ድርሻቸው ጉልሁ ሊሆን ይገባል። አህጉራችንም መዲናዋ ዋስትና እንዲኖረው የቀደመ ሥልጡን መንፈስ መኖር አለበት።  

አዲስ አባባ ባለቤት የሌለት ከተማ ሆና የፈለገ ሰማይ ጠቀስ መልካም ነገር ቢታቀድላት፤ ቢታለምላት ሥነ - መኖሯ በማንነቷ ውስጥ መስከን ካልቻለ ትርፉ የውርንጫ ድካም ነው። ይህ ደግሞ በዓዋጅ ሳይሆን ጠረኗን ጠረኔ ያለ ንጹህ ድንግል ህሊና ያለው ሙሉ ሰው ያስፈልጋታል። ለዚህ ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ብቁ ስለሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አሉሁላዋቸው እንዲሏቸው እሻለሁኝ - ይህ ለይደር ሊቀጠርም አይገባም።

የሱማሌን፤ የጋንቤላን ችግር አዲስ አባባ ስትፈታ የራሷን መርግ ችግር ግን ተሸክማ አንገቷ ሊበጠስ እያቀሳተች ነው ያለው። መንፈስ ሲሸፍት ከባዱ ውደቀት ነው። የመንፈስ ስንቅ መዲናዋ ላይ ይፈጠር።

የተጎዳ፤ የተገፋ፤ የተገለለ፤ መስዋዕትነቱ በዬዘመኑ ሲባክን የኖረ ነው የአዲስ አባባ ህዝብ። ካሳ ያልጠዬቀ፤ ካሳም ያልተከፈለው፤ ለመስዋዕትነቱም ዕውቅና ያልተሰጠው። አይዞህ ባይም አጣ። ቢያንስ አሁን የመንፈስ ካሳ ያስፈልገዋል።

ይህን የመንፈስ ካሳ ከኢንጂነር ታከለ ኡማ ሳይሆን ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ነው እኔ እምጠብቀው። እኔ በኢንጂነር ታለ ኡማ የነበረኝ ተስፋ እንጥፍጣፊው የለም። ጠብታ እንኳን። መንፈሴን ኦነግውያን እንዲመራኝ አልፈቅድም ዛሬም ወደፊትም። በ እነሱም ተስፋ አድርጌ አላውቅም ወደፊትም። መንፈሴን የአብዲሳ አጋ፤ የሃይለማርያም ማሞ - የጦሩ ገበሬ፤ የጸጋዬ ገ/መድህን ብቻ እንዲመራኝ ነው እምሻው።

·      ምርኩዝ ሰብዕናን ለምስክርነት እና ለተስፋነት።

https://www.youtube.com/watch?v=8Z6HexcMHGU

Ethiopia - Dr Abiy ከላይ ስትሆኑ በዛ መነጽር ብቻ ታች አትመልከቱ

https://www.youtube.com/watch?v=k07ZojV5DXg

Ethiopia - ….ኢትዮጵያ ትበለጽጋለችትለወጣለች!

Dr abiy ahmed about trusting youth, ወጣቱን የዘነጋ ፖለቲካ የትም አያደርስም

·      እርገት

አብይ ለወጣቶች አዲስ ቀለም ስለመሆኑ። ካለፈው ዓመት የሙግት አውድ የተወሰደ።
ወጣቱን በሁለት ጎራ ለይተን ልናዬው እንችላለን። በአንድ በኩል በጣም ፈጣን ጭንቅላት ያለው። ተሎ መማር የሚችል። በምክንያት ከነገርከው ማድመጥ ማመን፤ መስራት የሚችል ሃይል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግልፍተኛ ነው። ስሜታዊ ነው። ይህነን እንዴት አስታርቀን ለምንፈልገው ዓላማ እናውላለን ነው። አንደኛው የግልፍተኛ ወይንም የኢሞሽናል ሰዎችን ማስታገሻ መንገድ የሚናገሩበት፤ የሚተነፍሱበት፤ አውድ ማስፋት ነው። በሶሻል ሚዲያ ይሁን በኮንቤንሽናል ሚዲያም ይሁን። ሃሳባቸውን እዬሰጡ፤ ሃሳባቸው ደግሞ እዬተገራ፤ እዬታረመ ሲሄድ ሰዎቹ ሞር ሻርፕ እዬሆኑ፤ እያደጉ፤ እየበቀሉ ይሄዳሉ።“

ዶር አብይ አህመድ/ አሜኑ/ ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ነበር ባለፈው ዓመት። ያን ጊዜ እንደ አልባሌ የታዬ ነበር። ሳተናው ብቻ ነበር የለጠፈው። 

ይህን ዛሬም የአዲስ አበባ ወጣቶችን ባለተስፋ ባደረጉት ንግግር ላይ እንደ ቃላቸው ለመሆን ስለመቻሉ አዳመጫለሁኝ። አብክሬ በአጽህኖት በትህትና አማሳስበው ግን ጥሪ አለበዎት ጠ/ሚር አብይ አህመድ በማለት ነው። የጣሊያንን የኢትዮጵያን የማፈረስ አናታዊ ሙጃ አሰተሳብ ከሥሩ ነቅሎ ምርጥ ፍሬ ማስበል።  

ይህ ጥሪ ደግሞ እኛ ኢትዮጵውያን መናህሪያችን አዲስ አባባን መዲናችን እንድንል የማድረግ ነው። አሁን እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ዝንቅ ስሜት ነው ያለኝ። መዲናዬ ለማለት አልችልም። የለዬለት የማዕከላዊ መንግሥት አቅም ያለው አቋም ስላለዬሁኝ።

ለዚህ ነው ተስፋ ሰጪ ንግግር ስለሆነ ይህን ንግግር የዕለቱ አጀንዳዬ ያደረኩት። ለዚህ ቀጣይነት የሞል የህንጻ ግንባታ ሳይሆን ለአዲስ አበቤዎች ማገዶ መሆን አለበዎት ጠ/ሚር አብይ አህድም ማለትም የፈለግሁት። በሩቅም በቅርብም ያለው ጽኑ መንፈስ ተነቃንቋል። ኦነግ የተፈጠረበትን ኢትዮጵያዊነትን የመናድ ነው የሰራው፤ እርስዎ ደግሞ የተፈጠሩበትን እዬራዊ ጥሪ ይስሩ ነው ቁም ነገሩ። የህቺ ሥንኝ የእርስዎ ናት እና … ከስታወሷት …

·      እርገት በአብዩ አሜኑ ሥነ ግጥም ቋጠሩ ቅኔ።
„አንቺ ሐገር ኢትዮጵያ ልኑርልሽ እንጂ ሌላ እኔ ምን አልኩሽ
ትላንትሽ ከዛሬሽ ታሪክሽ ከዕውነትሽ ሥምሽ ከዕውነትሽ“
ሲተረጎም፣ --- ታሪክሽ አንቺን ሲገልጽ ከእውነት ነው። ሥምሽም ዕውነት ነው። ዕውነትም አንቺ ነሽ ነው። 

የዕውነትን ሥነ - ምግባር ሞራላዊ ዕሴት እምዬ ውዴ እናትዬ ነሽ። ዕብለት አንቺን የመግለጽ ድፈረትም አቅም የለውም ነው ቅኔው።

የጣይቱ መንፈስ ያብባል ገና!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።፡

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።