ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 28, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"ሳናውቅህ ስናውቅህ" ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን በአማክንዮ ይሞግታል።

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎጌ በሰላም መጡልኝ። " ሳ ናውቅህ ስ ናውቅህ " „ፃድቅ ሲጣል ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።“ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 36 ቁጥር 25።) ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ 28.01.2020 " ሳናውቅህ ስናውቅህ " በጣም ከባድ አመክንዮ ነው። ስለ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ነው። አውቀናቸዋል የሚሉትም ቢሆኑ የሚያውቋቸው አይመስለኝም። በቻ በቅኔው ጎጃም ቅኔ እንዲህ ቅኔውን አሳምሮ ይዘረፈዋል። የቀረብኝ ዘመን ይቆጨኛል። ፌስ ቡክ ሳልሳተፍ። ትልቅ የትምህር ተቋም ነው። የመኖር ዩንቨርስቲ። ሥልጡን። ዛሬ የርህርህና ተጋድሎ እለት ነበር። ሰው ሆነው ስለመፈጠራቸው የሚያውቁ ብፁዓን ዘሩን ለማጥፋት በተዘመተበት የአማራ ህዝብ ላይ የራሄል ዕንባን ያመሳጠሩ ህዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ ከተሞች ተደርገዋል። ጠንከር ብሎም በቀጣይ ጊዜያቶች እንደሚቀጥሉ ተስፋዬ ፅኑ ነው። ርህርህና በታገደበት የአብይዝም የመቃብር ሥፍራ ዘመን እንዲህ እርህርህናዊ ፀጋን ተጎናፅፈው፤ ሞትን ፈቅደው በጥዋቱ ለእዮር ያመለከቱ ወገኖቼን አመሰግናለሁ። ሰው ነኝ ማለት የሚገልፀው ተግባሩ ነውና። ብዙ መሳጭ ትምህርቶች ነበሩ። ብዙም ገሳጭ መምህር መልዕክቶችን   አንብቤያለሁ። 1.     " ጉዳዩ ሌላ ነው። ዕውነቱን ህዝብ ያውቀዋል " ይላል የሰማዕት የአማራ ሊሂቃንን የዶር አንባቸው መኮነን እና የብጄ አሳምነው ፅጌን ፎቶ ጎን ለጎን ያደረገ