ልጥፎች

ከጁላይ 2, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዳማዊ ቀን እና ጠይም ዕንቁዎች ያሉበት የቤልጀሙ ቡድን ለሩብ ...

ምስል
ጠይም ዕንቁዎች ያሉበት የቤልጀሙ ቡድን ለሩብ ፍጻሜ አለፈ። ከሥርጉተ ሥላሴ 03.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዕን ናቸው፡ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፲) የቀኑን ጨዋታ አልተከታተልኩትም። ብራዚል ለሩብ ፍጻሜ እንዳለፈ ፊፋ ሪፖርት ላይ አንብቤያለሁኝ። የምሽቱን ግን በርጋ ተከታትዬዋለሁኝ። ቤልጀም እና ጃፓኖች ነበሩ የተጋጠሙት። የመጀመሪያው የእረፍት ክ/ ጊዜ ላይ ጀፓኖች በሚገርም ብቃት ተንቀስቃሰዋል። እስኪገርመኝ ድረስ። ፈጽሞ እንዲህ አለጠበቅኳቸውም ነበር። ፍጥነታቸው፣ የመከላከል ሆነ የማጥቃት ውህደታዊ እንቅስስቃሴያቸው በአግራሞት ነበር የተከታተልኩት። ለዛውም ከቤልጄም ጋር … ህም! እርግጥ ነው ከ2014 የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ጀምሮ ቤልጀሞች የተከደነ ብቃት እንዳላቸው አስተውያለሁኝ። በ2016 ፈረንሳይ አገር ተካሄዶ በነበረው የአውሮፓ የዋንጫ ጨዋታም አስደሳች የአጨዋወት ስልት እና ሙሉ ሞራላዊ ሥነ - ምግባር እንዳላቸው በተጨማሪነት አይቻለሁኝ። እንዲያውም ያን ጊዜ ቤልጀም እና ፈረንሳይ የቦን ጥቃት ሰለባ ስለነበሩ ብዙ መከራ ያሳለፉ ስለሆኑ ከሁለቱ አገሮች ለአንዱ ዋንጫው ቢሆን የህዝቡን መከፋት ሚዛናዊ ያደርገዋል የሚል ህልም ነበረኝ።  ነገር ግን ዋንጫውን ፖርቹጋል ወሰደ። ፈረንሳዮች አጅግ ብርቱዎች ነበሩ በለስ ሳይቀናቸው ቀረ። ዘንድሮም እኔ ለቤልጄም ያው መስል ህልም አለኝ። ያው ከሲዊዝሻ ባይበልጥብኝም። ነገ ቀን ላይ ሲዊዝሻ ከሲወዲን ጋር ግጥሚያ አለባት። በሻማ ብርሃን ነው እምታደመው። መቼም መነኩሲያዋ ሲወዝ ቆቧን አውልቃ ለሩብ ፍጻሜ ካለፈች የእኔውም አይቀርለትም ...ፌስታው ከልክ በላይ ይሆናል። ...