ልጥፎች

ከማርች 25, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው???? …

ምስል
  መቼ ይሆን ደግሞ አዬር መንገድ ዬንጥር ባህርዳር ጉዞ እንዳያደርግ ዬሚታገተው???? ……   "አቤቱ ፀሎቴንም ስማ ልመናዬንም ቸል አትበል።"  (መዝሙር ፶፬ ቁጥር ፩)     • በጭካኔ በሰለጠኑ፤ • በበቀል በተነከሩ፤ • በቂም በበቀሉ፤ • በጥላቻ በተዘፈዘፉ፥ • በበታችነት ስሜት ወፈፍ ባሉ፥ • በህሊና አቅም ማነስ በሚባትቱ፤ • በአንጃ ግራንጃ ግንዛቤ ዬሚውተረተሩ፤   • በተለጠጠ ፍላጎት አገር ያህል ቁምነገር በከንቱነት ዬሚመሩ ዘመነኞችን ለመታገል _ መበሳጨት _ መጣደፍ _ መንቦጅቦጅ _ ሱሪ በአንገት አያዋጣም።    • ብዙ ነገር ዬተፈጠርንበትን ባዕት፤ ዬዘር ሐረግ፤ ዬአልረገጥም ጽኑ አቋም እና አሻምነት ባይመቻችሁ እንኳን በጣም በርቀት ዬሚታዩ ዕሳቤወችን እህ ----- ብሎ ማድመጥ ይገባ ነበር ቤተ ሰለሞን ላይ ከሊቅ እስከ ደቂቅ አላችሁ። ግን ዓለማችን ዬጆሮ ገብያ አልከፈተች። በስልተ ቢስ እሰጣ ገባ፤ በግርግር ፖለቲካ፤ ወዳጅ እና ተቀናቃኝን ባለዬ ዬዝንቅ ጉዞ ባዶ እጅ እዚህ አደረሰ።    • ዛሬን ለማዬት ተስኖ አዳዲስ አዛይ ዕሳቤወችን እዬፈጠሩ ዬናዷችሁን አክ ብላችሁ ዕውነት - ሃቀኝነት - መርህ እና ዬትግል ታማኝነት ዬት ላይ እንዳለ መዝኖ መወሰን ይጠይቃል። አሁንም ለግብር ዬሚጠራው ማን እንደሆን አስተውላለሁ። በማን መሪነት? ምን አለን? ማን አለን? ነገስ ለማን - ልዕልና ይታሰብበት። ብቻውን ዬቆመው ዬአማራ ህዝብም ይሰብበት።    • ወደ ባህርዳር ጉዞ ዬሚታገትበት ዘመን ሊመጣ እንደሚችል እሰቡት። መታገት ዓይነቱ ብዙ ነው። ሁሉም እስረኛ እንደሆነ ይሰማኛል። ለዚህ ደግሞ መንገዱ ዬእስራኤሎች ጽናት እና ጥበብ ይመስለኛል። መሪ ማውጣትም ይለ...

ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።

ምስል
  • ወቀሳ ነቀሳ በተሻለ ደረጃ ሳይገኙ ከሆነ ነው አንካሳ።   "ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ። በእሽታ መንፈስ ደግፈኝ።" (መዝሙር ፶ ቁ ፲፪)     (1) ያለን ነገር ማወቅ። (2) ያለን ነገር ማጥናት። (3) ያለን ነገር መመዘን። (4) በአለ ነገር መነሳት። (5) በአለ ነገር ላይ መደራጀት። (6) ዬአለን ነገር ለመምራት በአለን ነገር ውስጥ ያለውን ዲስፕሊን ጠንቅቆ ማወቅ። (7) በአለን ውስጥ ያሉ መልካም ነገሮችን ከደም ጋር ማዋህድ። ( 8)ብስጭትን - ገረጭራጫነትን - ሞረድ አንጀትን ዬክፋት አውራ ጎዳናወችን አክ ማለት። አለን ለሚባለው ሁሉ ቀና ጎዳና ቀያሽ ነው። ለዚህ ደግሞ እራስን መግዛት ይጠይቃል። በአንድም በሌላማ ዬውርጅብኝ ናዳ ዬሚወርድባቸው ሰብዕናወች በዬዘመኑ አሉ። እነሱን ዬራስ ለማድረግ አለን ዬምንለውን በጥንቃቄ ይዘን …   • ተደማጭ፤    • አሸናፊ ማድረግ ካልተቻለ ዬወቀሳ ተርቲም ዛሬን አያተርፍም፣ ለነገም ጭጎጎት ነው። እዮባዊቷ ቅድስታችን ከዬትኛውም ተቋም በላይ ዬዘመኑ ዓውራ እንድትከስም ዬተፈረደባት አሳረኛ ናት። • አጥኑት ዊዝደሟን።    • ሁሉን ረብ አድርጋ በከፍታ ላይ ትገኛለች። • ሁሉን ነገር ታውቃለች። መሪዋ መንፈሥ ቅዱስ ነውና። • ስለሆነም ተፍተፍ ዬለም። • ባጉም ባጉምም አይታሰብም። • ግልቢያም ትውር አይልም። • ዬቂም ብቅልም ዬላትም። • ያላት አርምሞ፤ ተደሞ፤ ጥሞና ፆም ጠሎት፥ ስግደት፤ ሱባዔ፤ ምስጋና፤ ዝማሬ፤ ቅዳሤ፤ ማህሌት ወዘተ … እዮባዊቷን አለችን ማለት ይገባል፤ ነገረ ፍጥረቷ ቫወል ነው። • እኛ እናሰግርሽ እንደ በቅሎ እንጋላብሽ ግን ቀኖናዋም፤ ዶግማዋም አይደለም። • እዮባዊቷ ዬፖለቲካ ድርጅት አይደለችም።   • ተፅዕኖ ፈ...

ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል። 25/03/2024

ምስል
  ጭካኔን መጠዬፍ ጥላቻን አክ ማለትን ይጠይቃል። • ጨካኞች በሽተኛ ናቸው። እንደ ሙሉ ሰው ሊታዩ አይገባም። • ጨካኞች ያልሰለጠኑ ናቸው። ሥልጣኔ ኢንተግሪቲ ነውና። • ጭካኔ ዬአስተሳሰብ ድህነት ነው ወደ ኋላ አብራራዋለሁኝ። • ጭካኔ ዬድንጋይ ዘመን ህዳሴ ነው። ጭካኔ ሰብዕናን ገድሎ ጫካዊነትን ማነፅ ነው። • ጨካኝ ሱፍ እና ገበርዲን ከረባት እና ቀሚስ አደለም ሰብእናዊ ቀለም ነው። • ጨካኞች አመክንዮ ስለመፈጠሩ አያውቁም፣ እርካታቸው አመክንዮን መስቀል ነውና። • ጨካኝነትን ለፋክክር ዬሚያቀርቡ ልሙጥ ሰብዕና ያላቸው ናቸው እና። እንሰሳነት ስለማያስቀና።       #ኋላቀርነት ።   በኢኮኖሚ ሳይንቲስቶች ኋላቀርነት በኢኮኖሚ ዕድገት አለመመጣጠን ይሉታል። እኔ ደግሞ በአስተሳሰብ ዘሃ ዬህሊና ድህነት እለዋለሁኝ። ልቆ አይፈጠርም የሰው ልጅ። ቅዱሳን አሉ በቅብዓ ዬሚሰጡ። ነገር ግን ዬሰው ልጅ ዲግሪውን ቁብ አድርጎ አይፈጠረም። ሂደት ትምህርት ቤት ነው። መኖር ትምህርት ቤት ነው። ቤተሰብ ትምህርት ቤት ነው። የአኗኗር ዘይቤ ትምህርት ቤት ነው። ተፈጥሮ ትምህርት ቤት ነው። ቀደመው ዬታነፁ፤ ዬተገነቡ ቅርስ እና ውርሶች ትምህርት ቤት ነው።    ታሪክ ትምህርት ቤት ነው። ትምህርት ቤት ዬግድ ዩንቨርስቲ መግባት ብቻ አይሆንም። ዕድሉን ያገኙ ሁለገቡን ተምረውበት ክህሎቱን በሥልጠና ያዘምኑታል። ይህ ለታደሉት ነው። ላልታደሉት ደግሞ ትውስቱም፤ ውራጁም ብርቃቸው ነው። አሁን ለፋንታዚው ልዑል ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የውሃ ዳንስ፤ የፓርክ ግንባታ፤ የኩሬ ውሃ ዋና ብርቅ እና ድንቃቸው ነው። ይህ ግን አንዱን ቤተ ጊዮርጊስ የሚሰጠውን ሚስጢር አቻ ሊሆነው አይችልም።   ግብግቡ ዬጭካኔው ውርስ የሥልጣኔውን...

የለውጥ ሃሳብ።

ምስል
  የለውጥ ሃሳብ።   • የለውጥ ሃሳብ ሂደትን ማዕቀብ በመጣል ማስቆም ወይንም የታቆረ ማድረግ አይቻልም። በፍጹም። ተፈጥሯዊ ነውና!   „በታካች ሰው እርሻ፤ አዕምሮ በጎደለው ሰው ወይን ቦታ አለፍሁ። እነሆም፣ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፤ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል። የድጋዩም ቅጥር ፈርሷል።“ (መጸሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፴፩)       • በር።   ለእኔ በማሰብ ልቅና የአስተሳሰብ ለውጥ ይመጣል ብዬ አምናለሁ። የነቃው የህሊና ክፍል አዲስ ሃሳብ ሲያፈልቅ ሃሳቡን የሚቀበል ህሊና፤ አዕምሮ ሊኖረው ይገባል። ይህ አዕምሮ ያፈለቀውን አዲስ ሃሳብ የሚመጥን የሰብዕና አቅም የሚኖረው ከአቅሙ ከራሱ በመመንጨቱ ነው። አዲሱ ልቅና ያለው አስተሳሰብ ሃሳብ የትውስት ወይንም የብድር አይደለም። ስለምን? አዲሱ ዬአስተሳሰብ ልቅና ካለው ከራሱ ህሊና፤ የአዕምሮ የአቅም ፏፏቴ የመነጨ ስለሆነ ዲስፕሊኑን የመሸከም ብቻ ሳይሆን በቅጡ አደራጅቶ የመምራት፤ የማስተዳደር አቅሙ ተመጣጠኝ ነው።   .. ብቻም ሳይሆን ሚዛናዊነቱ በራሱ የአዕምሮ የውሃ ልክን የሚያስጠብቅ ተጠባባቂ የሃሳብ ማህበር ዘብም ይኖረዋል። እንደገናም የማህበራዊ ንቃተ ህሊናው የመሸከም ዲስፕሊን አንጻር ማዬት ይጠቅማል። ቀድሞ ነገር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማህበራዊ ንቃተ ህሊና አጀንዳው ሆኖ አያውቅም። መነሻ የሌለው መድረሻ ሲያልም የኖረ ልም።    • ምጥነት።   የወገቡ ስፋት 35 ሴንቲሜትር የሆነ ልብስ የ52 ሴንቲሜትር ስፋት ያለው ልብስ ቢጠለቅለት መዋኛ ገንዳ ነው የሚሆነው። ወይንም 35 ሴንቲሜትር የወገብ ስፋት ላለው 10 ሴንቲሜትር ስፋት ያለው ልበስ ቢባልም ይሄም በጅ የሚል አይሆንም። አሁን የገዳ ኦሮሙማ ...

ዬአስተሳሰብ ደራጎንነት እና ጢስ ጢንብሳዊነቱ።

ምስል
  ዬአስተሳሰብ ደራጎንነት እና ጢስ ጢንብሳዊነቱ።   "ዬማዳንህን ደስታ ስጠኝ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።" (መዝሙር ፶ ቁጥር ፲፪)       እነ ማበህረ ደራጎን በሄሮድስ መለስ ዜናዊ አንቀልባ በታቆረ ጥብቆ ህሊና ሊመጥነው በማይችል ቅዠት ውስጥ ሆነው እናያለን። ቅዠታቸውን ለማስቀጠል ያላቸው የአዕምሮ ብቃት አቅሙ አልተመጣጠነም። ያልገባቸው ጉዳይ ይሄ ነው። ስለዚህ ባነሰ ግምት ስድስት ዓይነት ጦርነቶች ተከፍቶባቸዋል።    • አንደኛው፣ … የሻገተው አስተሳብን ለመሳቀጠል ያለ ከራሳቸውም ጋር ራሳቸው ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። • ሁለተኛው፣ … በራሳቸው ማህበርተኛ ወስጥ የተፈጠረ አዲስ ሃሳብ አቅም አለ አስምጧቸዋል። • ሦስተኛው፣… በሃሳብ ልዕልና በሚያምኑ አቅሞች ሙግቶችን የመቋቋም ግብ ግብ ላይ ናቸው። • አራተኛው፣ … በራሱ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ውስጥ የተከደነ የጦርነት ቀጠና ውስጥ የተጠለለ የዲፕሎማሲ ተጋድሎ አለ። • አምስተኛው፣ … ከሁሉም ያልሆነ ግን የመንፈስ አቅሙ ሙሉዑ የሆነ፤ ልኩ ያልታወቀ አቅም ልዩ ኃይል አለ፤ ይሄ „ጸጥተኛ ፤ ጭምታዊ ድምጽ silent majority“ የሚባለው።    • ስድስተኛው፣ … የድሮ ዓለምዓቀፍ ወዳጆቻቸው ሂደቱን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪም በቅርበት እዬተከታተሉት መሆኑ ሌላው ፈተና ነው።   ለዚህ ሁሉ ፈተና የማህበረ ሌንጮ ህልማቸውን የሚሸከም የአስተሳብ/ የሃሳብ፤ የሰብዕና፤ የአዕምሮ ደረጃው ነገቲብ ላይ ነው። የዛገ ብርት ዝግት እዬጨመረ በሄደ ቁጥር ቀለሙ ብቻ ሳይሆን አገልግሎት የመስጠት አቅሙም ያኑ ያህል እዬተፈረፈረ ይሄዳል። ቀብር።   በሂደቱ ራሱን መሸከም እያቃተው ለበለጠ ክስመቱ ሆነ ዕድሜ ማጠሩ እራሱን በራሱ ያጣፋል...

አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል።

ምስል
  አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል።   "ዬደም ሰወች እና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ አይሞላም።:እኔ ግን አቤቱ እታመንኃለሁኝ።" (መዝሙር ፶፪ ቁጥር ፳፫)     ትግሉ የአልሞትም ባይ ተጋዳይነትን ስለሚጨምር የሚያስከፍለው መስዋዕትነት የከፋ ይሆናል። ግን አዲሱ ሃሳብ በአዲስ አቅማዊ ስልትና ስትራቴጂ በጥበብ ስለሚመራ አሸናፊ መሆኑ አይቀሬ ነው። ይህ ስለተፈራ ነው አብሮነት የተሰረዘው በገዳ ምርጫ ቦርድ። አብሮነትን የገዳ ምርጫ ቦርድ በድፍረት እና በማናህሎኝነት ሲሰርዘው ኢትዮጵያን ሰርዟታል። ኢትዮጵያ መለያ ማልያዋ አብሮነት ነውና።    በሌላ በኩል አብሮነትን ተስፋ ያደረጉ መንፈሶች ሁሉ ጆኖሳይድ ተፈጽሞባቸዋል። አሰምሌሽንም ተፈጽሞባቸዋል። ይህ በጣም ረቂቅ አመክንዮ ነው። በእኔ ውስጥ እኔ ስኖር ብቻ ነው ሊታዬኝ የሚችለው።    አንድ ኢትዮጵያዊ ተቋም ሲደረመስ በእኔ ውስጥ ያለው መንፈስም አብሮ መደረመስ ታውጆበታል ማለት ነው። አብሮነት ጆኖሳይደ ሲካሄድበት እኔንም ይጨምራል።   • እኔ ተቋሜ ኢትዮጵያ ናት። • ኢትዮጵያ ደግሞ የአብሮነት ማህደር ናት። • አብሮነትን ሥሙ ትውፊቴም ትሩፋቴም ነው። • ትውፊቴን የፖለቲካ አመንዝራዋ የገዳ ልዕልት ወ/ት ብርቱካን ሚዲቅሳ ሲፈጽሙት በእኔንም ላይ ፈረዱ።   እሳቸው 16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዛገው ገዳቸው ላይ ነው ያሉት። እኛ ደግሞ 21ኛው ምዕተ ዓመት ሰውኛ እኛዊነት ላይ እንገናኛለን። መመጣጠን ያልቻልነውም በዚኸው አመክንዮ ነው።    „ጸጥተኛ ድምጽ silent majority“ አባልተኞችም የቀና ቀን ጠባቂዎች ናቸው። ስብጥራቸው ሁሉንም የአቅም አይነት ያሟላ ነው። እነኝህ ከሁሉም ጋር ...

25/03/2023 የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አይቻልም።

ምስል
  • የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አይቻልም። • የዛገው ብረት በማረተ ሃሳብ … ??? "ኃያል ሆይ በክፋት ለምን ትጎዳዳለህ?"   "ሁልጊዜስ በመተላለፍ?" (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፩)     የዛገው የጉራጁ ኢህዴግ ኦህዴድ የማረቱ ምርኩዞቹ የዚህን የአዲስ ዘመን መንፈስ ሰላሙን በማወክ ትንፋሹን ማባከን ቀዳሚው መስካቸው ነው። የማያዋቀው ነገር ግን የአዲስ ሃሳብን ሂደት ማስቆም ቀርቶ መገደብ አለመቻሉ ነው። አንድ ጊዜ ተፈጥሯል። እንደ ጉርሻ ዋጥ ተደርጎ ጸጥ የሚባልበት አይሆንም። አዲስ ሃሳብ ምጡ እስኪ ወለድ ድረስ ነው። ከተወለደ በኋዋላ ግን በራሱ ጊዜ እድገቱን መቀጠሉ የተፈጥሮ ህጉ ነው።    አንድ በህክምና ዶር. የተመረቀ ሰው በዕወቀቱ ላይ የተለዬ ስልጠና እዬወሰደ ያዳብረዋል እንጂ እንደገና ወርዶ 7ኛ ክፍል ላይ ስለተፈጥሮ ሳይንስ ልማር አይልም። ምክንያቱም አቅም ፈጣሪው አዕምሮ ወደላይ ከመዝለቅ በስተቀር ወደ ታች መውረድን ስለማይፈቅድለት። አሁን ያለውን ቡቃያ የለወጥ መሻት በዛገ የምርኩዝ ጋጋታ፤ በወዬበ ኳኳቴ በፈለገው ዓይነት መጠራቅቅ መቋቋም አይችልም የአዳማ ሥርዕዎ መንግሥት። ይህ የለውጥ መንፈስ ከብሄራዊ አልፎ፤ አህጉራዊና ዓለምዓቀፋዊ ጫናም ፈጥሯል። ረቂቅ ነው። የፈጠረው ጫና በፍጹም ሁኔታ ኦህዴድ በሚያስበው መልክ በግርድፍ የሚሾከሾክ የገብስ ቆሎ አይደለም። በፍጹም። ሃሳብ ዬለም ብሎ አይመፃደቅ።   • መታዬት።   የዛገው ሙጣጭ ሃሳብ አዲሱን የለውጥ መንፈስን መቀበል ብቻ ሳይሆን ከአዲሱ መንፈስ ጋር ለመቀጠል እንኳን በግትርነት የሚሆን አይሆንም። የሚመጥን የአዕምሮ ብቃት፤ የሰብዕና ንጽህና፤ የሥነ - ምግባር ሞራል፤ የሥርዓት መዋቅራዊ ደርጁነት የለውም። ያስፈ...

25.03.2023 ነፃ የወጣ ኢትዮጵያዊ #የአዕምሮ ነፃነት!

ምስል
  ነፃ የወጣ ኢትዮጵያዊ #የአዕምሮ ነፃነት!     • ሃሳብ ነፃ የወጣ ነፃ የአዕምሮ ነፃነት ነው። ነፃ የወጣ ስል የአዕምሮ ነፃነቱ የትውስት ሰብዕናን፤ • የትውስት ፍልስፍናን፤ • የትውስት አቅምን፤ • በትውስት አዕምሮ የተፈጠረ ንድፈ ሃሳባዊ ቀመርን በፍጹም ሁኔታ የተጸዬፈ ነው።   በአካልም በመንፈሰም የዬትኛውንም ሐገር ፍልስፍና ወይንም የኤኮኖሚ አቅም፤ ወይንም የዲፕሎማሲ ጫና አልሞ የተነሳ አይደለም የራስ አቅም ይህ ራሱን ችሎ በራሱ ጊዜ ነፃነቱን አውጆ የተነሳው ሃሳብ በቀጥታ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ወዳጅ የሆነውን ሰዋዊነት፤ ተፈጥሯዊነት ኢትዮጵያዊ ቀለም ሰጥቶ የተነሳ ከሆነ ስለሰው ግድ የሚላቸው፤ ስለተፈጥሮ ግድ የሚላቸው ባለ አዕምሮችን ቀልብ ሲስብ ፕሮፓጋንዲስት ወይንም ቀስቃሽ ወይንም በፕሬስ ውደሳ ተቀባይነቱ ጥገኛ አይሆኑም። ጥራት ያላቸው ማስተዋሎች ብቻ ይደግፉታል። ያ ደግሞ ለግብ ያበቃል።    ዛሬ ሁሉንም በጋራ የሚያገናኘው አንድ ተፈጥሯዊ መርህ አለ #ሰብዕዊነት ። ከብዙ ቅን መንፈሶች ጋር የተሰራው ሃዲድም በዚህ መስመር ነው።    • አንደኛ … በራስ ወገን የታሰብ ከሆነ፤ • ሁለተኛ … አቅሙ ስፋቱና መጠኑ ባለጥሪት ከሆነ፤ • ሦስተኛ … ከማንም እና ከምንም ከዬትኛውም ሐገር የውለታ ጥገኝነት የሌለበት ከሆነ። • አራተኛ … ሁሉንም በአኩልነት በእቅፉ ለማድረግ ከልቡ ከፈቀደ፤ • አምስተኛ … ተረስተው፤ ተዘንግተው የኖርትን ሁሉ ፍቅርን በገፍ ከሰጠ። • ስድስተኛ … ነገስ ለሚለው አደራውን ለመወጣት ያለው የህሊናው መሳናዷዊ አቅሙ ሙሉዑ ከሆነ፤ • ሰባተኛ ሲጠልፉ ሲያነቅዙ ለኖሩት ጠለፋ ካልተመቼ፤ ከሁሉ በላይ ኢትዮጵያን ከነክብሯ፤ ከነግርማ ሞገሷ የእኔ ብሎ ከሚስጢሯ ከተነሳ ለቅኖች...

#ትውልዱ።

  #ትውልዱ ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት አደራችሁ ማህበረ ቅንነት? #ሰውኛነት በብዙ #መታገስን ይጠይቃል። ዕውነት ለመናገር በብዙ እንደምትታገሱኝም አውቃለሁኝ። እዬጎዳኋችሁ መሆኑን አውቃለሁኝ። ብዙ ጊዜ #በተጎዱ አመክንዮወች ዙሪያ ስለምሰራ። ለዚህም ነው አልፎ አልፎ ፎቶዬን እምለጥፈው። ስለሚጨንቀኝ። ሁልጊዜ መርዶ፤ በዕንባ እና ጭንቀት ላይ አተኩሮ መሥራት ለውድ ቤተሰቦቼ ከባድ እንደሚሆን አውቃለሁኝ። በደንብ ነው እምረዳው።    ነገር ግን ትውልድን እንሰብ ካልን የትውልድን ተስፋ #የሚያጫጩ ገጠመኞችን ሁሉ መጋፈጥ ግድ ይለናል። በዛ ዙሪያም የወረት ሳይሆን በተከታታይ ልንተጋ ይገባል። #ዩንቨርስቲወች አደራ ማውጣት አለባቸው። ይህ መብታቸው ሳይሆን #ግዴታቸውም ነው። በአደራ የተሰጡ ልጆችን አደራ #አለማውጣት ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ከሚሰማው የአንድ አገር መንግሥት የሚጠበቅ ባለመሆኑ ነው ሙግቱ። አንድ ወላጅ በብዙ ፈተና ውስጥ ሆኖ ወልዶ፤ አሳድጎ #አስብልልኝ ብሎ ልጅን ያህል የመኖር ተስፋ፦ አደራ ሲሰጥ አደራን መወጣት ግድ ነበር።   ያ አደራ ሲታመም ለምን ብሎ መጠዬቅ ደግሞ የእኛ ጉዳይ ነው። ለዚህም ነው ምላሽ እስኪገኝ ድረስ ጥያቄዬን ሳላቋርጥ ሳቀርብ የቆዬሁት። እርግጥ ነው አድካሚ ሊሆን ይችላል። እናንተን ውድ ቤተሰቦቼንም መጉዳቴን አውቃለሁኝ። ካልተደከመ #ማስበል አይገኝም።   የእኔ ልጅ ቢሆን? የእኔ እህት ብትሆን? የእኔ ታናሽ ወንድም ቢሆን?   የእኔ ታናሽ እህት ብትሆን ብሎ ማሰብ ይገባል። የሚገርማችሁ ለቤተሰቡ ሩህሩህ የሆነ ሰብዕና በዚህ አገራዊ፤ ብሄራዊ ጉዳይ ግን ቸለልታ ሳይ ህመሙ የፈፃሚው ብቻ ሳይሆን ሰውኛነት የነጠፈው በሌሎችም ላይ እንደ አለ ...

ማድመጥ ካለብኝ #የተጎዱትን ማድመጥ ይቀናኛል።

   ማድመጥ ካለብኝ #የተጎዱትን ማድመጥ ይቀናኛል። መሄድ ካለብኝም #ሃዘንተኞችን ማዬትን እፈቅዳለሁኝ። መርዳት ካለብኝ #አራሽ #አልባ #ስደተኛ #እህቶቼን #ነፃ አገልግሎት ብሰጥ እወዳለሁኝ። አቅም በነበረኝ ወቅት። ማድመጥ ካለብኝ #ርህርህና ያላቸውን መልዕክቶች ባደምጥ እወዳለሁኝ። ማተኮር ካለብኝ #በሰውኛ እና #ተፈጥሮኛ ጉዳዮች ላይ የሚተኩሩ ሰብዕናወችን መልዕክት ትኩረት መስጠትን እፈቅዳለሁኝ። በመሆኑም ነው አንጀቴ የተጎዳው። ቢሆንማ ደስታን ማን ይጠላል። ግን ዕንባ እያለ እንደምን ይቻላል? ሁልጊዜ የዕንባ ዜና??? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ግን እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት። ……… እንሆ ርህርህናናን በአጽህኖት የጠዬቀውን ከአቶ ስንታዬሁ ፔጅ ያገኜሁት ነው። ዕንባን ያወያዬ ቁምነገር። "እንደ አንድ አባት አማራ የልጅቷ ህመም በስሜት ላይ ሆኜ ይኽን እንረሳው ይሆን? አማራ፦ ከምኒልክ ጡት ቆረጠ ምናባዊ ትርክት ይልቅ በእውነታዉ ዓለም የተጨበጠ ጥሬ ሃቅ የሂትለር አገዛዝ ጭካኔ ያስናቀ የዚች ልጅ የአማራ ታሪክ ይበልጣል። በሀገሪቷ ታሪክ ያልተፈጸመ የልጃችን አሰቃቂ ግፍ ለትወልድ ማስተማሪያ የትግል ፕሮግራም የሚቀዳበት መጽሐፍ ነው። የአማራ ሰቆቃ በወግና ድርሰት በኪነ-ጥበብ ማስተማሪያ የሚሆን ታሪክ ነው። በአንድ ዘመን እንዲህ ሆነናል ለልጅ ልጅ የምትነግርበት አማራ ለምን ይታገላል? ለሚሉህ ቄንጠኞች ምንም አይነት ፍልስፍና የመዳረሻ ፕሮግራም ሳያስፈልግህ የደንቢዶሎ ግፍ ብቻ መታጊያ ነጥብ የህልውና መከራከሪያ ነው። የግፍ ሂሳብ በፍትህ ማወራረጃ ምዕራፍ ወደትግል ወጣሁ ለማለት በቂ ምክንያት ነው። የደንቢዶሎ ተወላጅ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በዳንዲ መጽሐፍ ላይ የተናገሩት! ምኒልክ ጡት ቆረጠ የሚል ታሪክ ለማረጋገጥ...