ማድመጥ ካለብኝ #የተጎዱትን ማድመጥ ይቀናኛል።

 

 ማድመጥ ካለብኝ #የተጎዱትን ማድመጥ ይቀናኛል።
መሄድ ካለብኝም #ሃዘንተኞችን ማዬትን እፈቅዳለሁኝ።
መርዳት ካለብኝ #አራሽ #አልባ #ስደተኛ #እህቶቼን #ነፃ አገልግሎት ብሰጥ እወዳለሁኝ። አቅም በነበረኝ ወቅት።
ማድመጥ ካለብኝ #ርህርህና ያላቸውን መልዕክቶች ባደምጥ እወዳለሁኝ።
ማተኮር ካለብኝ #በሰውኛ እና #ተፈጥሮኛ ጉዳዮች ላይ የሚተኩሩ ሰብዕናወችን መልዕክት ትኩረት መስጠትን እፈቅዳለሁኝ። በመሆኑም ነው አንጀቴ የተጎዳው። ቢሆንማ ደስታን ማን ይጠላል። ግን ዕንባ እያለ እንደምን ይቻላል? ሁልጊዜ የዕንባ ዜና???
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ግን እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት።
……… እንሆ ርህርህናናን በአጽህኖት የጠዬቀውን ከአቶ ስንታዬሁ ፔጅ ያገኜሁት ነው። ዕንባን ያወያዬ ቁምነገር።
"እንደ አንድ አባት አማራ የልጅቷ ህመም በስሜት ላይ ሆኜ ይኽን እንረሳው ይሆን?
አማራ፦
ከምኒልክ ጡት ቆረጠ ምናባዊ ትርክት
ይልቅ በእውነታዉ ዓለም የተጨበጠ ጥሬ ሃቅ የሂትለር አገዛዝ ጭካኔ ያስናቀ የዚች ልጅ የአማራ ታሪክ ይበልጣል።
በሀገሪቷ ታሪክ ያልተፈጸመ የልጃችን አሰቃቂ ግፍ ለትወልድ ማስተማሪያ የትግል ፕሮግራም የሚቀዳበት መጽሐፍ ነው። የአማራ ሰቆቃ በወግና ድርሰት በኪነ-ጥበብ ማስተማሪያ የሚሆን ታሪክ ነው።
በአንድ ዘመን እንዲህ ሆነናል ለልጅ ልጅ የምትነግርበት አማራ ለምን ይታገላል? ለሚሉህ ቄንጠኞች ምንም አይነት ፍልስፍና የመዳረሻ ፕሮግራም ሳያስፈልግህ የደንቢዶሎ ግፍ ብቻ መታጊያ ነጥብ የህልውና መከራከሪያ ነው።
የግፍ ሂሳብ በፍትህ ማወራረጃ ምዕራፍ ወደትግል ወጣሁ ለማለት በቂ ምክንያት ነው።
የደንቢዶሎ ተወላጅ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በዳንዲ መጽሐፍ ላይ የተናገሩት!
ምኒልክ ጡት ቆረጠ የሚል ታሪክ ለማረጋገጥ ብፈልግ ብፈልግ አጣሁ።
//
የደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪ አማራ
//
ከራሷ አንደበት፦ 1አመት ከስድስት ወር በመንጋ ደፈሯት በፌሮ ብረት ማህጸኗን ወጉት በደም የጨቀየ አካሏ የማህጸን በሽተኛ ሆነች። በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ለልመና ወጣች በትምህርቷ ትልቅ ቦታ ተመኝታ ጎዳና ወደቀች። ልጄ ተምራ ትጦረኛለች ያለች የአማራ እናት ሙሉ ቤተሰብ በሀዘን ተበተነ። እውነት ቢዘገይም ጥሬ የታሪክ ሃቅ ወጣ። ማህጸን በብረት በአማራ ተፈጸመ ለልጅ ልጅ ተጻፈ!
"
ጻፍበት ቅስቅስበት ቁጭት ፍጠርበት!"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?