ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 22, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እውን ለውጡ በማሸንፍ ወይንስ በንቃቃት ላይ?

ምስል
ስቅዛት በፈቃድ። „ጋሜል። ቀበሮች እንኳን ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ።             የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምደረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።“                    ሶቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 22.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=3KaJ74W-az0 Ethiopia: በቡራዮ ከተካሄደው ጥቃት የተረፉ ዜጎች ፖሊስ ሦስት ቀን ሙሉ ስንጨፈጨፍ አልደረሰልንም                       አሜኑ! ይቻላል ወይ በጃዋርውያን/ በኦነግውያን መንፈስ አገር እየታመሰ?  እንዴት ናችሁ ውዶቼ አንድ ኢሜል አንድ ወዳጄ ላኩልኝ። እኔ እኮ መሬት ላይ የጋሞ አዛውንታት የሠሩትን ማቃለሌ አይደለም። ያ መልካም ነገሩ ኦሮምያ ላይ ካልሠራ ምንድነው ፋይዳው ነው ጉዳዩ።  እነኛ ቅኖች መበደልን በበቀል አለመመለሳቸው በፈጣሪ ዘንድ ያስደግፋቸዋል። ነገር ግን መንግሥት የተጠቀመበት የቄሮ ወንጀል እንዲሸፈንለት መሆኑ ነው  እኔ የማይመቸኝ፤ ሌላው አባገዳዎች ኦሮምያ ላይ ጉዳት ሳይደርስ ለቃችሁ ውጡ ማለታቸውን ከኦሮምያ የተፈናቀሉ የአማራ ልጆች ከ6ወር በፊት ገልጸዋል። አባ ገዳዎች እንደ ጋሞዎቹ መሆን ተስነቿው ነው የማዬው። አባ ገዳዎችም የኦነጋውያን መንፈስ እንጂ ለአብይ ካቢኔ ክብካቤያቸውን አላዬሁም። ቡራዩ ላይ አባ ገዳዎች የሉንም? ቢያንስ ሬሳ አስነስተው በክብር ለማስቀብር ምን አገዳቸው? ሞትስ ቢሆን ምን አለ ቢቀበሉት። ሰማዕትነት ነው። ሊቢያ ላይ አኮ አንድ ሙስሊም ሰማዕት ራሱን ቀራኒዎ አውሏል ከወገኖቹ ጋር። አባገዳዎች ከተጠቂዎች ቀደመው ቢሰው የአቡነ ጴጥሮስ ትውፊታቸውን ከወኑ ነበር