ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እግዚአብሄር አቦይ ስብኃት ነጋን፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን፤ ሻለቃ ዳዊትን እንዲጠራላቸው ተማፀኑ። #የአብቹ ላንቃ መልዕክት ልኳል።
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ እግዚአብሄር አቦይ ስብኃት ነጋን፤ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን፤ ሻለቃ ዳዊትን እንዲጠራላቸው ተማፀኑ። #የአብቹ ላንቃ መልዕክት ልኳል። ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በህይወት እያለ ይህን ይሰማ ዘንድ ፈቃዱ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን። እኔ በአብይዝም እና ህህዋቲዝም ጦርነት ካወገዙት በጣት ከሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊ ዜጎች አንዷ ነበርኩኝ። ሰቢዕዊ ቀውሱን ብቻ ነበር እምዘግበው። እንዲያውም ደስታችሁን በልክ ያዙት ምክንያቱም ሌላ ደስታ ስታገኙ መደርደሪያ እንዳይጠባችሁ፤ ከዚህም ሌላ ደስታችሁን ስትነጠቁ የሥነ ልቦና ህመም ተጠቂ እንዳትሆኑ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ደስታ ሲበዛ ፈጣሪ ይከፋ እና ምርቃት ያነሳል በማለት ስሞግትም ነበር የመቀሌ ተያዘ ርችት ጊዜ። አቶ ሻንቆ የሚባሉ ጥሩ ወዳጄ በጣም ይከፋብኝ ይሞግቱኝም ነበር። ዛሬ ያለውን ነገር ሁል በዝርዝር አስቀድሜ ጽፌዋለሁ ልቦና ላላቸው ወገኖቼ። አቅምም አላባከንኩም። ህወሃት ቤተ መንግሥቱን ፈቅዶ ከለቀ ጀምሮም በህወሃት ላይ አንዳችም ነገር አልፃፍኩም። የከፋኝ አማራ ክልል እና አፋር ክልል ላይ የፈፀመው በደል ነበር፤ እንጂ የአብይዝም ካድሬወች ውሃ በቀጠነ ህወሃትን ሲያብጠለጥሉት አቅም አላባከንኩም ፈቅዶ መንበረ ሥልጣንን ከማስከበር ሌላ ምን ይምጣላችሁ በማለት ነበር የሞገትኩት። ለዛውም ለእኔ ስለ ህወሃት ሆነ፤ ስለ ሻብያ ቀስቃሽም፤ ፕሮፖጋንዲስትም አያስፈልገኝም። በጦርነት ቀጠና ውስጥ ስለአደኩ ሁሉን በደል አውቀዋለሁና። የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አዲሱን ዓዋጅ አውጃዋል። ለሰማዩም ዳኛ ውሰድልኝ ብለዋል። የአብይዝም እና ህወሃቲዝም ጦርነት ሆድዕቃው ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው እና እያዬን ነው። እያዳመጥን ነው። ...