ልጥፎች

ከጁላይ 29, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን?

ምስል
  ስለምን ኃላፊተት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማብቀል ተሳነን?   "በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀምጠን ጽዮንን ባሰብናት ጊዜ አለቀስን። (መዝሙር ፻፴፯ ቁ ፩) እንዴት አደራችሁልኝ ማህበረ ክቡራን እና ክቡራት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ አምላኬን ተስፋ አድርጌ ደህና ነኝ። ሰሞናቱ እንደ ደመናም፤ እንደ ወጀብም፤ እንደ ዝናብም ይቃጠዋል በቅድስቷ በዕቴ በቪንተርቱር ከተማ። ማሰብ። ማሰብ። ማሰብ። እያሰብኩ ሃሳብን አስበዋለሁኝ። ስለምን ኃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት ተሳነን? እኛም ሆን የቀደሙት ስለምን መዝራትን ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ከማብቀል፤ ተጠንቅቆ ከማሳደግ ጋር ምኑ አፋተን? #በኃላፊነት እና በተጠያቂነት መሐል ጉልቻው ከፈረሰ ቆዬ። ግን ለምን?   #አደራ ምንድን ነው? #ትውፊትስ ምንድን ነው? #ትሩፋትስ ምንድን ነው? #ቅርስ ውርስስ ምንድን ነው? #ታሪክስ ምንድን ነው? #ባህልስ ምንድን ነው? #ወግ - ልማድስ ምንድን ነው?   ግን ምንድን ነው እራሱ #ምንድን ነው? መልስ ይሻል? እንጀራን እዬበሉ እንጀራ የተፈጠረበትን ሥልጣኔ ማብጠልጠል? አማርኛ ቋንቋን እዬተናገሩ አማርኛ ቋንቋን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መፍጨርጨር? ሰንደቅ ዓላማው ባስገኜው የነፃነት ትንግርተ ቤተ - መንግሥት ተቀምጦ ሰንደቅ ዓላማን መፎካከር? ግን ምንድን ነው? እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው?   ኢትዮጵያ በሚለው ሙሉ አቅም ባለው ኃይለ ሚስጢር ለሥልጣን ተበቅቶ፤ ለሽልማት ተበቅቶ፤ ለክብር ለዝና ተበቅቶ አዬር ላይ ተንሳፎ በቅሎ ዙፋን የተጨበጠ ይመስል "የራሴ ጥረት ስኬት" እያሉ መጎረር በማጓራት መጯጯኽ ምንድን ነው? ግን እራሱ ምንድን ነው ምንድን ነው?   የተሰደደውም ኢትዮጵያ በሚል ኃይለ - ሚስጢር ስደቱን

#ጎንደር ትናንት ዛሬና ነገ #ጎንደር ከ1624 እስከ 1792 ዓ.ም ድረስ የሀገራችን መዲና ነበረች፡፡

ምስል
  #ጎንደር ትናንት ዛሬና ነገ #ጎንደር ከ1624 እስከ 1792 ዓ.ም ድረስ የሀገራችን መዲና ነበረች፡፡ የጎንደር የከተሜነት ታሪኳ የሚጀምረው በአፄ ፋሲለደስ የንግስና ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይሁንና ጎንደር የሚለው ስያሜ በአፄ አምደፂዩን የንግሰና ዘመን ማለትም ከ1312 አስከ 1342 በዜና መዋዕል ተጠቅሶ መገኘቱ የጎንደርን ዕድሜ ለማሰላት በርካታ ዓመታተን ወደ ኋላ መመለስን የሚጠይቅ እንደሆነ አመላካች ነው፡፡   ጎንደር ፋሲለደስ የነገሱበትን 36 ዓመታት ጨምሮ የልጃቸው የፃዲቁ ዮኃንስና የልጅ ልጃቸው የታላቁ እያሱ 75 የንግስና ዓመታት የጎንደር ወርቃማ ዘመናት እንደነበሩ ታሪክ ይዘክራል፡፡ #የጎንደር የጨለማ ዘመን ተብሎ የሚታወቀው ደግሞ አፄ ተክለ ጊወርጊስ ስልጣን ከለቀቁበት ከ1792 ዓ/ም ጀምሮ አንደነበር ይነገራል፡፡ ኢትዮጵያ በዛጉየ ስረዎ መንግስት ማለትም ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ቋሚ የማዕከላዊ መንግስት መቀመጫ አልነበራትም፡፡ በአፄ ፋሲለደስ የንግስና ዘመን ጎንደር የሀገሪቱ ዋና ከተማ መሆኗ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት መመስረት አዲስ ምዕራፍ መክፈት ችሏል፡፡ #የጎንደር ከተማ ከ200 ዓመታት በላይ በተከታታይ ለአስራ አራት ነገስታት መቀመጫ መዲና በመሆን አገልግላለች፡፡ የጎንደር ከተማ ጥንታዊ ስልጣኔ ሰላም የሰፈነበት ህግና ፍትህ የተከበረበት ኪነ-ጥበብና እውቀት ለማስፋፋት እድል የተገኘበት ጊዜ መሆኑን ጥንታዊ የታሪክ አሻራዎች ይዘከራሉ፡፡ የጎንደር ጥንታዊ ስልጣኔ ሲዘከር የኪነ-ህንፃ ጥበብ፣የእደ-ጥበብ ቱርፋቶች፣የንግድ ማዕከልነቷና ዘመናዊ የከተሜነት ይዞታዋ ተጠቃሾች ነበሩ፡፡ የጎንደር የእደ-ጥበብ ውጤቶች ከጎንደር ወርቃማ ዘመን አስከ ዘመነ መሳፍንት ድረስ ከፍተኛ እምርታ የታየበት እንደነበር

#ቡርሽ ውል አለኝ ሽውም። ውስጣችን ጎድፏል። ውስጣችን #ጎልድፏልም። እንተባተባለን። አለን ግን በሽሽት። እንኖራለን ግን በሽግሽጎሽ። እና? እናማ መኖር ብለነዋል ድብቅብቆሹን።

ምስል
  #ቡርሽ ውል አለኝ ሽውም። "ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል።" (ምሳሌ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯)     አማረኝ። ሽው አለኝ እንዲያው ሽው። ትዝ አለኝ እንዲያው ትዝ። ውል አለኝ እንዲያው ውል። ይናፍቃል። ያሳሳል። ያጓጓል። ምኑ በሏ ክብረቶቼ? ግን እንዴት ዋላችሁልኝ ማህበረ ክቡራን እና ማህበረ ክቡራት? ጉንፋኗ ተገስ ስትል ከች አልኩኝ። ሸጋ ነው አይደል። ኦኦ ዬናፈቀኝን ፍለጋ እንሆ እማስናለሁኝ። እናንተስ? አብረን እንማስን እስቲ። ቡርሽ ፍለጋ አብረን - አብረን እላለሁኝ። ቡርሽ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ያስፈልገናል። ውስጣችን ጎድፏል። ውስጣችን #ጎልድፏልም ። እንተባተባለን። አለን ግን በሽሽት። እንኖራለን ግን በሽግሽጎሽ። እና? እናማ መኖር ብለነዋል ድብቅብቆሹን። አገር ከአለትውልድ አይታሰብም። ትውልድም ካለ አገር አይሞክርም። እንደ ኩርድሾች ካልገጠመን። ለነገሩ ኩርድሾችን ለመሆን እዬቧጠጥን ነው። ማህከነ። አዬ አንሻዬ የአንቺን ህይወት ምነው ሁሉ ቢያይልኝ። አይሻ የኩርድሽ የራዲዮ ጋዜጠኛ ናት። ዬማውቃት ለ15 ዓመታት ነው በራዲዮ ጋዜጠኝነት ነው። ቅድመ መሰናዶ ከእኔ ቀጥላ እሷ ናት። ስትዲዮ እምትረከብ ከኮረና በፊት፦ እና እህት አንሻዬ ቁጭ ብላ ምግብ ስትመገብ አላዬትም። ቁጥር ሁለት ስትዲዮ ስለቅላት #ኬባቧን ይዛ ትገባለች። ኬባብ በሥጋ በሰላጥ የሚዘጋጅ ፋስት ፋድ ዘርፍ ውስጥ ነው። ምነው አንሻ ለምግብ ጊዜ ቢኖርሽ ስላት " #ስሞት ይሆናል" ትለኛለች። መንገድ ላይም ሳገኛት ምግቧ መንገድ ላይ ነው። መጠጧም እንዲሁ። ሁልጊዜ እንደባከነች ነው። አርበኛ ሴት የኩርድሽ ጓዶቿ ታጋዮች ጉዳይ ውስጧ ነው። ኩርድሽ ሴቶች አቻ እና ወደር የላቸውም። የወጣላቸው አርበኛ፤ የወጣላቸው ጀግናም ናቸው። አላቃዬ እራሱ እግሯን ያጣችው በትግል

“ወልቃይት፣ ጠገዴ እና ቀብቲያ ሁመራ፣ የበጌ ምድር ግዛት እንጂ የትግራይ አካል ኾነው አያውቁም" አቶ ገ/መድህን አርአያ፣ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የሥራ አመራር የነበሩ

ምስል
ከአቶ አስፋው ሞገስ የተገኜ ነው። እንዴት ናችሁ ውዶች? ምንጩ ከዕውነት አርበኛው ከአቶ ገብረመድህን አርያ የተገኜ ነው። አሟቸው ነበር። ተሻላቸው ይሆን? “ወልቃይት፣ ጠገዴ እና ቀብቲያ ሁመራ፣ የበጌ ምድር ግዛት እንጂ የትግራይ አካል ኾነው አያውቁም" አቶ ገ/መድህን አርአያ፣ የቀድሞ የህወሓት ታጋይና የሥራ አመራር የነበሩ     አዲስ አበባ: ሐምሌ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) "ከዛሬ 45 ዓመታት በፊት፣ ኢትዮጵያውያን የግራ ዘመም ፖለቲከኞች አውራ የኾነው ትህነግ (ወያኔ) በተከለው አሜኬላና በቀበረው የሴራ ፖለቲካ ፈንጅ እርስ በርስ ተባልተው ዛሬ ላለንበት የፖለቲካ መድረክ ከመብቃታችን እና ሀገሪቱ በዘር በሽታ ከመታመሟ በፊት፣ ትህነግም ወልቃይት ጠገዴን የቅዠቱ አካል አድርጎ ካርታ ላይ ሳይስል፣ በወያኔ ከፍተኛ አመራር አባላት አማካይነት ለወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አንድ ኹነኛ ጥያቄ ቀርቦ ነበር" ይላሉ የቀድሞ ታጋይ ገ/መድህን አርአያ። በወቅቱ ይላሉ፣ እኒኽ ጉምቱ ፖለቲከኛ፣ "ወልቃይት ጠገዴ የማን ግዛት አካል ነው...?" ተብለው ሲጠየቁ፣ በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ያለምንም ፍርሓትና ማመንታት “ወልቃይት ጠገዴማ፣ የበጌ ምድር ክፋይ፣ የአማራ ሕዝብ ርስቱ ነው" ብለው መለሱላቸው ይሉናል። አቶ ገብረመድህን አርአያ በትህነግ ቤት ከከፍተኛ አመራር አባልነታቸው ባሻገር፣ የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ ኾነው ሰርተዋል። ስለኾነም የትህነግን የተንሸዋረረ እይታና የተወላገደ አሥተዳደግ ጠንቅቀው የተረዱና ለዘመናት በተለያዩ የትግል ሥልቶች ሲታገሉ የመጡ ጨዋ ኢትዮጵያዊ ናቸው..። የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራርና የፋይናንስ ኃላፊ አቶ ገብረመድህን አርአያ በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም በኢትዮ ሚዲያ ጎልጉል ድረ-ገጽ ላይ "በወል

ዬአቅም ምንጩ ትውልዱ እና ዕጣው። #ከሳይለንት #ማጆሪቲው የተውጣጣ አጽናኝ፤ ሰባዕዊ ግብረ ኃይል ወይንም ቲም ቢመራት ምርጫዬ ነው። ትውልዱም ቢያርፍ። ማገዶነቱ ቢያከትም

ምስል
  ዬአቅም ምንጩ ትውልዱ እና ዕጣው። "ምንጮችህ ወደ ሜዳ ወንዞችህ ወደ አደባባይ ይፈሳሉን?" (መጽሐፈ ምሳሌ ፭ ቁ ፲፮)         እንዴት አደርን? ደህና ነን? አይዞን "ከመከራ ጀርባ ታላቅ ክብር አለ።" ይላል መጥሐፋ። በኢትዮጵያ ፖለቲካ አቅም አጀንዳ ሆኖ አያውቅም። አቅም ጊዜ፤ የሰው ልጅ ጉልበት፤ መንፈስ፤ መዋለ ንዋይ ነው። በአንድ የፖለቲካ ማዕቀፍ ውስጥ እነኝህ ሁሉ ያስፈልጋሉ። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ፋይናንስ ብቻ ነው እንደ አቅም የሚታዬው። ከዛ ውጪ ያለው ጥልቅ የሆነ እያንዳንዱ በግል ሁሉም በጋራ የሚያፈሰው የጊዜ እና የመዋዕለ መንፈስ እርዳታ ከመጤፍ አይቆጠርም። ለምን? በነፃ ስለሚታደል። አንድም ፖለቲከኛ ስለሚሰጠው የነፍስ ወከፍ ሙሉ ድጋፍ ከቁብ ቆጥሮት አያውቅም። እሱ በተገለባበጠ ቁጥር እዬደፋፋ አዲስ አቅም ሲመኝ ይሉኝታ እሚባል አልፈጠረለትም። ድጋፋ፤ እገዛው፤ ማበረታቱ ቀርቶ ማለት ነው። ከሁሉ የሚከፋው አንድ ኮቢ ሳይገዛ፤ አንዲት እራፊ ሳይሸምት ወላጅ ያሰናዳውን ትንፋሽ ቄራ ላይ መዋሉ ነው። ዘመን ከዘመን የኢትዮጵያ ትውልድ ይታጨዳል። አንዱን ደግፎ ሲወጣ፤ ሌላውን አሻም ሲል በግብግቡ ዬትውልድ መተራ። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ግብታዊ ናቸው። ግብታዊነታቸው ሳያቅዱ ተነስተው ስለሚፈጠረው የትውልድ ብክነት አንድ ቀን አጀንዳቸው ሆኖ አያውቅም። በዛው በተደረተው አስተሳሰብ በአዲስ ሸበላ ድምፅ የፖለቲካ ድርጅት ባመረቱ ቁጥር ያልደከሙበትን ትውልድ እዬዘረፋ ለካቴና፤ ለስደት፤ ለመሰወር እና ለዕልፈት ይዳርጋሉ። እነሱ አክተር ናቸው። ተተኪ ማብቀል ሃራማቸው ነው። ተተኪ ብቻ ሳይሆን የተሻለ ዕሳቤ ካለም ገብተው አነኩረው በአንጃ አንቆጥቁጠው ይበትኑታል። ይከተክቱታል። ከበተኑት በኋላ እስከ ግል ህይወት