ልጥፎች

ከጁን 6, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

Conversation witb Elias Aweke, Wednesday June 5, 2024

ምስል

#የሚገርመኝ የኮፒ ራይት የይገባኛል #ስውር ሂደት።

ምስል
  #የሚገርመኝ የኮፒ ራይት የይገባኛል #ስውር ሂደት። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   በመጠነ ሰፊ ጉዳይ #የኮፒ ራይት ፍልሚያ አለ። ጎልቶም፤ ደብዝዞም። ድርጊተኞች ዝም ስላሉ፦ ትውር አትበሉብን #ዳንኪራም አዳምጣለሁ። እንዲህ ዓይነቱ ዕሳቤ ብዙ ተሳትፎወችን ያለዛል፤ ያዝላል፦ ወይንም ያኮማትራል። የህውኃት እና የአብይዝም ጦርነት ማገባደጃ ሰሞናት አንድ ቅን ሰው ቤተሰቦቹን፤ ወዳጆቹን፤ የትምህርት ቤት ጓደኞቹን ይዞ ለአንድ በጦርነት ለተሰዋ ሰማዕት ፋኖ እያንዳንዱ #በዓመት 600 ዶላር ማዋጣት አለበት ለሰማዕታት ቤተሰቦች፤ መጦሪያ ወይንም ለልጆች ማሳደጌያ በሚል ንቅናቄ ጀመሩ። ግብረ ምላሹ ጥሩ ነበር። በኋላ የፖለቲካ ድርጅቶች ፋኖን ውሃ በቀጠነ እያነሱ ተደመምንበት ሲሉ በሳይለንት ማጆሪቲ የተጀመረው ንቅናቄ #ቀጥ አለ። ዘመነ አስተሮዬ ነበር ወቅቱ? ይህ ጠቀመ ወይንስ ጎዳ???? መዝኑት። በሌላ በኩል አማራን በሚመለከት ከህወኃት እና ከአብይዝም ጦርነት ጦስ ጋር የገነነ መከራ ነበር አማራዬ ላይ። ከ2023 ግንቦት በፊት። ከዛ #ያ ጉዳይ #ፀጥ አለ። ነገር ግን ስኬቱ በኮፒ ራይት ተንገላታ። ከዛስ? ያ የቅኖች ጥረት አሁንም #ፀጥ አለ። አሁን በቅርቡ "ፋኖ በሚል ሥም ራሱን የሚጠራው የሚል ድምጽ ተደመጠ።" የሰከነ ተግባር በተከወነው ስኬት መነሻነት ደርጅቶ ክትትል ቢደረግለት የተገኜው ስኬት #ጥበቃ የበለጠ ያገኝ ነበር። በተጨማሪም ለአዲሱ ቻሌንጅ በር አይከፈትም ነበር የገዘፈ የህልውና፤ የገዘፈ የማንነት ተጋድሎ የሚዲያ ሰብል ብቻ በመሆን አዬር ላይ ከቀረ ነገም ያሳስባል። ምክንያቱም እኛ እያለን ይህን ያክል መከራ አማራ ተሸከም ከተባለ እኛ ስናልፍስ???? የሆነሆኖ ብዙ ችግር በአንድ የተወሰነ ቡድን መልካም ፍቃድ

የማይተኩ ዊ፨ዝደም

ምስል
 

ክብሮቼ

    ክብሮቼ ቲክቶክ ጀምሬያለሁ። የፈቀደ መልካምነትን ይኮመኩማል፨

Mr. Sibehat G/E

ምስል
 

ከአማራ ክልል ውጭ የሚኖሩ አዲስ አበባን ጨምሮ ስቃያቸው ሊወከል ይገባል። #አንሰበርም #አንሰብርም። #አማራነት #ይከበር። #አማራነትም #ያክብር።

ምስል
  ውዶች የቤታችን ታዳሚወች ውቦች እንዴት አደራችሁ? ግርማ ሌሊቱ እንዴት ነበር። ተመስገን ነግቶ ተገናኘን። "የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ" ትንቢተ ዘካርያስ ነው እንዲህ የሚለን …… " የሠራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፦ ስለ ጽዮን ታላቅ ቅናት ቀንቻለሁ። በታላቅም ቁጣ ስለ እርሷ ቀንቻለሁ።" (ትንቢተ ዘካርያስ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ከ፩ - ፫) #አንሰበርም #አንሰብርም ። #አማራነት #ይከበር ። #አማራነትም #ያክብር ።     ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖሩ የአማራ ልጆች ሚሊዮን ናቸው። ሚሊዮኖች የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ፦ የማህበራዊ ኑሮ፦ የሃይማኖት ዕውቅና ያለው ውክልና የላቸውም። ኑሯቸው #ግዞት ነው ማለት ይቻላል። በአገራቸው ውስጥ 33 ዓመት ተሰደው ኑረዋል። የትኛውንም የግፍ ጽዋ ስንቅ ኑሯቸው፤ አሳርን መገፋትን መገለልን መጠለያቸው አድርገው። በራሳቸው የፊደል ገበታ አይማሩም። ልማር ቢሉም እንደ ወንጀል ስለሚታይ ይቀጣሉ። ይገለላሉ። ከባዕታቸው በግፍ ይፈናቀላሉ፤ ይሰወራሉ፤ ይገደላሉም። #ሁነኛ የላቸውም። በኢትዮጵያ ተፈጠሩባት ግን መብት አልባ ግዴታን ብቻ በጫና ሲኮመኮሙ ኖሩባት። ይመርጣሉ ግን አይመረጡም። በአቅማቸው ያሉበትን በዓት ተግተው ያለማሉ፤ ግን ይቀጡበታል እንጂ አይሸለሙበትም። ለዚህ ነው ዛሬ የአማራ ወጣቶች እኛ ታላላቆቻቸው በዕድሜውም፤ በተመክሮውም በመቆዬታችን #ለዘብ አድርገን በምናያቸው ክስተቶ የሚበሳጩብን። ይገባቸዋል። አንድም ወጣትነታቸው ያስገድዳቸዋል። ሁለትም መከራው የገዘፈ እና የሰው ልጅ ከሚሸከመው በላይ ሆነ። ስለዚህ ቢበሳጩ ቢከፋቸው ሊሰማን አይገባም። የሆነ ሆኖ በማናቸውም ሁኔታ ነገረ አማራ ሲነሳ ሽዋ፤ ጎጃም፤ ጎንደር ወሎ ሲባል እሰማለሁ። አዲስ አበባ 5

እኔ እራሴ በዚህ ፁሁፍ ተደምሜያለሁ፨ የደጉን አማራ ሁለንትናዊ አቅም ማኔጅ የሚያደርግ መሪ ነው የጠፋው። ሙሴ አልባ ተጋድሎ ሰማዕትነት ብቻ።

ምስል
  የደጉን አማራ ሁለንትናዊ አቅም ማኔጅ የሚያደርግ መሪ ነው የጠፋው። ሙሴ አልባ ተጋድሎ ሰማዕትነት ብቻ። "እንደ ጠቢብ የሆነ ሰው ማን ነው?" (መክብብ ፰ ቁጥር ፩)     እንዴት አደራችሁልኝ? አላችሁልኝ? የአማራን አቅም የሚሻማ በሽ ነው። በአማራ አቅም የሚጎመጅ በሽ ነው። ዬአማራን አቅም የሚዘርፍ በሽ ነው። የአማራን አቅም ለራሱ ፍላጎት ኢንቤስት ለማድረግ የሚወራከብ ወዘተረፈ ነው። የኦሮሞ አቅም፣ የተጋሩ አቅም፣ የሱማሌ አቅም፣ የጋንቤላ አቅም፣ የደቡብ አቅም፣ የአፋር አቅም፣ የቤንሻንጉል አቅም ወዘተ በራሱ ጊዜ ካለ ማንም አዋኪ እና አዋካቢ በልጆቹ ይመራል፣ በራሱ ልጆች ይደራጃል፣ ይተዳደራል። ጠብ የምትል የአቅም ነቁጥ የለም። ጠበል። የአማራ አቅም ግን የሌላው ሳንጃ ተሸከሚ ነው። ለሌላው አንጋች እና አጋች እና አሳጋጅ ጥቅም ብቻ ነው። የአማራ ልጅ ሰኞ ይፀነሳል፣ ማክሰኞ ይወለዳል። እሮቡ ትምህርት ቤት ይሄዳል። ሃሙስ ለፈተና ይቀመጣል። አርብ ዩንቨርስቲ ይገባል። ዕሁድ ይመረቃል። ሰኞ ለሞት ይሰናዳል። የአማራ ልጅ ሱቅ ከምንገዛው ዕቃ እንኳን ያነሰ ዕውቅና አይሰጠውም። የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የአማራን አቅም ሲያጩ፣ ሲሟጥጡ ባላሳደጉት ልጅ፣ እንዲት ፔና ያልገዛ፣ በባለንብረትነት ባለቤት ሆነው ልባቸውን ነፍተው የፖለቲካ ድርጅት ይፈጥራሉ። በአንድ ቀን ደርሶ እሸት ቅመሱ የሚል ማገዶ ህዝብ አላ። አማራ ደግዬ፣ ቅንዬ። በተዥጎረጎረው ስማቸው ልክ ፔስቲ ያላወጡበትን ልጅ አገልጋያቸው አስደርገው ማገዶ ያስደርጋሉ። ልጁ የተጎዳበት ፖለቲከኛ አላውቅም። የአማራ ልጅ እኔ ገጠሩን በአደራጅነቴ ዘመን በእግሬ ኳትኜ፣ አቀበት ቁልቁለት ወጥቼ ወርጄ፣ ወንዝ ተሻግሬ ሙላትን ተጋፍጬ፣ ሰኔሏ ላይ መደብ ላይ ተኝቼ አውቀዋለሁኝ ጓዳውን፣ አሳሩን፣ መከራውን።