#የሚገርመኝ የኮፒ ራይት የይገባኛል #ስውር ሂደት።

 

#የሚገርመኝ የኮፒ ራይት የይገባኛል #ስውር ሂደት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 1 person and smiling
በመጠነ ሰፊ ጉዳይ #የኮፒ ራይት ፍልሚያ አለ። ጎልቶም፤ ደብዝዞም። ድርጊተኞች ዝም ስላሉ፦ ትውር አትበሉብን #ዳንኪራም አዳምጣለሁ። እንዲህ ዓይነቱ ዕሳቤ ብዙ ተሳትፎወችን ያለዛል፤ ያዝላል፦ ወይንም ያኮማትራል። የህውኃት እና የአብይዝም ጦርነት ማገባደጃ ሰሞናት አንድ ቅን ሰው ቤተሰቦቹን፤ ወዳጆቹን፤ የትምህርት ቤት ጓደኞቹን ይዞ ለአንድ በጦርነት ለተሰዋ ሰማዕት ፋኖ እያንዳንዱ #በዓመት 600 ዶላር ማዋጣት አለበት ለሰማዕታት ቤተሰቦች፤ መጦሪያ ወይንም ለልጆች ማሳደጌያ በሚል ንቅናቄ ጀመሩ።
ግብረ ምላሹ ጥሩ ነበር። በኋላ የፖለቲካ ድርጅቶች ፋኖን ውሃ በቀጠነ እያነሱ ተደመምንበት ሲሉ በሳይለንት ማጆሪቲ የተጀመረው ንቅናቄ #ቀጥ አለ። ዘመነ አስተሮዬ ነበር ወቅቱ? ይህ ጠቀመ ወይንስ ጎዳ???? መዝኑት። በሌላ በኩል አማራን በሚመለከት ከህወኃት እና ከአብይዝም ጦርነት ጦስ ጋር የገነነ መከራ ነበር አማራዬ ላይ። ከ2023 ግንቦት በፊት። ከዛ #ያ ጉዳይ #ፀጥ አለ። ነገር ግን ስኬቱ በኮፒ ራይት ተንገላታ። ከዛስ? ያ የቅኖች ጥረት አሁንም #ፀጥ አለ።
አሁን በቅርቡ "ፋኖ በሚል ሥም ራሱን የሚጠራው የሚል ድምጽ ተደመጠ።" የሰከነ ተግባር በተከወነው ስኬት መነሻነት ደርጅቶ ክትትል ቢደረግለት የተገኜው ስኬት #ጥበቃ የበለጠ ያገኝ ነበር። በተጨማሪም ለአዲሱ ቻሌንጅ በር አይከፈትም ነበር የገዘፈ የህልውና፤ የገዘፈ የማንነት ተጋድሎ የሚዲያ ሰብል ብቻ በመሆን አዬር ላይ ከቀረ ነገም ያሳስባል። ምክንያቱም እኛ እያለን ይህን ያክል መከራ አማራ ተሸከም ከተባለ እኛ ስናልፍስ????
የሆነሆኖ ብዙ ችግር በአንድ የተወሰነ ቡድን መልካም ፍቃድ ጥረት ብቻ መቋቋም አይቻልም። ለዛ እኛ ብቻ ለሚለው ቲምም እዩኝ እዩኝ የማይሉ ዝምታወች የተገበሩት ሥጦታ ነበር። ይህም ሆኖ ቁንጮ እኛ ነን መባሉ ብቻ ሳይሆን ግድፈትን እንደ ውዳሴ ማርያም እዩልን የተገባ አይደለም።
የሁሉም ችግር መፍትሄው በእኛ እጅ ነው ብሎ #መታበይም፦ ትርፍ ሄዶ ህዝብን መወረፍም፦ ትርፍ ሂዶ ሰብዕናን መደፍጠጥም አይገባም። የሚጎዳው #አጤነትን እና #ቀዳማዊትነትን ምኞትን ብቻ ሳይሆን #አደራንም ጭምር ነው። አራጊ ፈጣሪ አንድ ቡድን ብቻ ሊሆን አይገባም። እኔ ነኝ ጉልላትም ማለትም አይገባም። አይተነዋል እኮ ምን ውስጥ ወስዶ እንደቀረቀረን ከዚህ ቀደም።
እንደማስበው #ጥሞና ቢወሰድ። #አርምሞ ቢደረግ። #ፍላትን አስታግሶ #ትነትን መቋቋም ቢቻል መልካም ነው። ብዙ መስዋዕትነት አለ። ያን ደግሞ በህብራዊነት ጥረት እንጂ #ሰሞንኛ በሆነ የቅርበት እና ርቀት ዲፕሎማሲያዊ ጉዳይ መፍትሄ አያገኝም። አቅም ያለው ሁሉ ተስቶፎ ሊያደርግ ይገባል። #ዕብጠትም#መወጠረም#መንጠራራትም "ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል" ይሆናል።
መታበይ መጀመሪያ የሚያጠፋው እራስን ነው። መታበይ #ያከስላል። መታበይ መኖርን #ኤክስፓዬርድ ያደርጋል - ክስተትንም። መታበይ የተቃጠለ ካርቦን ያደርጋል። አክሰሱ ያላቸው ሚዲያወች በድፍረት መገሰጽ አለባቸው። ማንም የማንም #ረድ አይደለም እና። ሰው ሙሉዑ ፍጥረት ነው። ባይማር እንኳን ተፈጥሮ የምትገልጥለት #ሚስጢራዊነት አለው። አባቶቻችን የተማረውን ሊቅ ሲሉ ቀለማዊ ዕውቀት ዕውቅና ያላገኜውን ሊሂቅ ይሉታል። የሰው አፈጣጠር #ሚስጢራዊ ነው። ስለሆነም ነው ቀንና ሌሊት ተሠርቶልን ረቂቁን ተግባር ሌሊት እሚፈፀመው።
ሌላው በትልቁ የሚገርመኝ ሌት እና ቀን የሚታትሩ ዓራት ዓይናማ ጋዜጠኞች በውስጣቸው #ስጋት እንዲፀንሱ የሚደረገው ሁነትም ይገርመኛል። ጋዜጠኝነት በራሱ #የነፃነት #ምልክት ነው። ማንም ሰው ሊገስፀው፤ ሊያሸማቀው አይገባም። ጋዜጠኝነት ፈተናን ፈቅዶ የሚቀበል ሩህሩህ የሰብዕና ባለሟል ነው።
አለቃም ቢሆን የጋዜጠኝነት ሙያ ላይ ዲስክርምኔሽን ሊፈጥር አይገባም። ጋዜጠኛው የራሱ ህሊና አለው። ማንም የማያዝበት ለራሱ ከላይኛው የተሰጠው እንደራሴነት።
ለዬትኛውም የግድፈት ዓይነት ፍራሽ ወይንም ትራስ ማቅረብ የተገባ አይደለም። በትክክል ከችግሩ ሴንተር ላይ ተነስቶ ግድፈትን ማረም፤ መገሰጽ ይገባል። ጋዜጠኛ ለዚህ ነው የተፈጠረው። ጋዜጠኛው ይሞገት ግን ህሊናህ ዶዱማል ግን ድፍረት ነው።
"ወደ እግዚአብሄር እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"
ለትውልድ ግድፈትን ጠጥተህ ለሽ በል አይጠቅመውም። ጠቃሚው ነገር ግድፈትን ነቅሶ አውጥቶ ማረም ነው። እርማት እኮ በራሱ ዩንቨርስቲ ነው።
አይበቃኝም ይብቃኝ። ቸር ቆዩኝ ቸሮቼ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
04/06/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።