ልጥፎች

ከጁን 9, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አደርን። ነጋልን። አነጋልን።

 አደርን። ነጋልን። አነጋልን። ጨለማን አስታግሶ የብርሃን ጌታ ብርሃን ሰጠን። ተመስገን። ሰንበትን ለርህርህና፦ ሰንበትን ለትህትና። ሸበላ ለንበት። አሜን። ሥርጉ2024/06/0 9

ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ናት። ተስፋዋም መርቆ የፈጠራት አምላኳ ነው።

ምስል
  ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ናት።  ተስፋዋም መርቆ የፈጠራት አምላኳ ነው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   የፖለቲካ ሊቃውንታት ይሰጋሉ። ስጋት ለምን ተፈጠረ ልል አልችልም። ገፊ ምክንያቶች አሉና። ተጨባጭ የአመክንዮ ምልክቶችም አሉና። ኢትዮጵያን አብዝተው ከሚቀናቀኗት፤ ከሚቀኑባት፤ ሊበቀሏት ከሚሹ እጆች በማህበረ ኦነግ ሥር ስለወደቀችም። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ከመሆኗም በላይ የተበጀችበት መሠረታዊ አመክንዮ #ዊዝደማዊ ስለሆነ ኢትዮጵያ ተስፋዋ ተንጠፍጥፎ ፍስስ የምትል አገር አድርጎ ማዬቱ መብት ቢሆንም ግን እኔ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ እኮ ደርግ እና ህወሃት ሻብያም ታክሎ በኃይል ርክክብ ሲያደርጉ ብዙው በዕት የመንግሥት አስተዳደር አልነበረውም። ያ የሆነበት ምክንያት እኔ እንደምረዳው የተሠራችበት #የዊዝደም ቅመም ንጥር ጠንካራ በመሆኑ ነው። በኋላም እንዳትቀጥል ተደርጎ በተሠራው ህወሃት ሠራሽ የዞግ ክልል ውስጥ እራሷን ማስቀጠሏ እኮ የጥበቦች ጥበብ #ልቅና ነው። ይህም ሆኖ መላ የአፍሪካ አገራት፤ መላ ቡኒ ዕንቁ ሁሉ ይመኩባታል። ይጽናኑባታል። ተስፋ ያደርጉባታል። ሙሉ ስድስት ዓመት እንደ ነሃሴ ዶፍ ደም ሰርክ እዬፈሰሰም አፍሪካውያን ኢትዮጵያ #መራሂት እንድትሆን ይመኛሉ። በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የአደባባይ ሹመት አፍሪካውያን ያስተላለፋት መልዕክት እኮ መጸሐፍ ይወጣዋል። አፍሪካውያን ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ተስፋ የላስታ አለት ዓይነት ነው። ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን እንደ #ኃይማኖታቸው እንደሚዮዋት ነው እኔ እማስበው። ኢትዮጵንይዝም እኮ መቼውንም ቢሆን ሊፈቀፈቅ የማይችል ኮከብ #አስተምህሮ ነው። ፋና "ከሲንጋፖር ምን እንማራለን" የሚል መሰናዶውን የኢትዮጵያን ሥም በአረንጓዴ ቢጫ ቀ