ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ናት። ተስፋዋም መርቆ የፈጠራት አምላኳ ነው።
ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ናት።
ተስፋዋም መርቆ የፈጠራት አምላኳ ነው።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
የፖለቲካ ሊቃውንታት ይሰጋሉ። ስጋት ለምን ተፈጠረ ልል አልችልም። ገፊ ምክንያቶች አሉና። ተጨባጭ የአመክንዮ ምልክቶችም አሉና። ኢትዮጵያን አብዝተው ከሚቀናቀኗት፤ ከሚቀኑባት፤ ሊበቀሏት ከሚሹ እጆች በማህበረ ኦነግ ሥር ስለወደቀችም። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ የራሷ ማንነት ያላት አገር ከመሆኗም በላይ የተበጀችበት መሠረታዊ አመክንዮ #ዊዝደማዊ ስለሆነ ኢትዮጵያ ተስፋዋ ተንጠፍጥፎ ፍስስ የምትል አገር አድርጎ ማዬቱ መብት ቢሆንም ግን እኔ አይመስለኝም። ኢትዮጵያ እኮ ደርግ እና ህወሃት ሻብያም ታክሎ በኃይል ርክክብ ሲያደርጉ ብዙው በዕት የመንግሥት አስተዳደር አልነበረውም።
ያ የሆነበት ምክንያት እኔ እንደምረዳው የተሠራችበት #የዊዝደም ቅመም ንጥር ጠንካራ በመሆኑ ነው። በኋላም እንዳትቀጥል ተደርጎ በተሠራው ህወሃት ሠራሽ የዞግ ክልል ውስጥ እራሷን ማስቀጠሏ እኮ የጥበቦች ጥበብ #ልቅና ነው። ይህም ሆኖ መላ የአፍሪካ አገራት፤ መላ ቡኒ ዕንቁ ሁሉ ይመኩባታል። ይጽናኑባታል። ተስፋ ያደርጉባታል። ሙሉ ስድስት ዓመት እንደ ነሃሴ ዶፍ ደም ሰርክ እዬፈሰሰም አፍሪካውያን ኢትዮጵያ #መራሂት እንድትሆን ይመኛሉ። በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የአደባባይ ሹመት አፍሪካውያን ያስተላለፋት መልዕክት እኮ መጸሐፍ ይወጣዋል። አፍሪካውያን ስለ ኢትዮጵያ ያላቸው ተስፋ የላስታ አለት ዓይነት ነው። ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን እንደ #ኃይማኖታቸው እንደሚዮዋት ነው እኔ እማስበው።
ኢትዮጵንይዝም እኮ መቼውንም ቢሆን ሊፈቀፈቅ የማይችል ኮከብ #አስተምህሮ ነው። ፋና "ከሲንጋፖር ምን እንማራለን" የሚል መሰናዶውን የኢትዮጵያን ሥም በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጽፎት አይቻለሁ። ያ የተለመደ ኮንፊዩዝድ እና ኮንቢንስ መሆኑን ባውቅም ደፍረው ያን ማድረጋቸው ያስገደዳቸው ኃይል ርቁቅ መሆኑ ግን ይረዳኛል። በመንፈስ ቅዱስ አስገዳጅነት መሆኑን አምናለሁ። እርግጥ ነው የመሪያቸው የፋና ላምሮት ኮንፊደንስ እና ብቃት እንዳላቸው ማስተዋሌን ልዘለው አልሻም።
የሆነ ሆኖ በአብይዝም ዘመን በዬትኛውም የወጣት ግንባታ ሂደት እኮ ፋና የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አይደለም ቀለማቱን አይደፍርም፦ በወጣቶች የሙዚቃ ውድድር። ፋና ብቻ አይደለም። ኤንቢሲ፤ አዲስ ዋልታ፤ ኢቲቢም አይዶላቸው #ድርቅ የመታው ነው። መብራቱ እንኳን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ እንዳይኖረው ታስቦ፤ ታቅዶ ነው የሚከወነው። እኔ ከውስጤ እያንዳንዱን ቅንጣት እከታተላለሁ። የቲሙ አልባሳትም እራሱ ቀለማቱን አብዝቶ ይፈረዋል።
የፋኖ ላምሮት ዓርማ፤ የአገራዊ ምክክሩ መለያ ምልክት፤ የጠቅላይ ሚር አብይ ከሀ እስከ ፐ ልዩ ፐርሰናል ፕሮጀክት፤ የቀዳማዊት እመቤቷ ቢሮ ፕሮጀክት ሁሉ ከኢትዮጵያዊ ማንነት ጋር #ተፋተው ነው የሚወጠኑት። የአባይ ድልድይ ምርቃት የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ልብስ #ጀርመን ጠቀስ ነበር። ሆን ተብሎ ታቅዶ የተከወነ ነው። አማራ ክልል ለሚፈፀም ሴሪሞኒ #ጀርመን ጠቀስ ቀለማት? የሚገርመው ጠሚር አብይ በአብዛኛው ቦታ ባለቤታቸውን ይዘው ሲጓዙ ግን #የወለጋው #የለቀምቱ ግን ትውር አላደረጓቸውም። ይህ በነቃ ህሊና የሚከወን አመክንዮ ነው።
የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ በሶሻሊዝም ርዕዮት ሆነ፤ አሁን ደግሞ በአሳቸው መሪ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ፓን #አረቢክ፤ #እስያ ቀመስ #ፒኮካዊ ሁነት ሲሰላ ኢትዮጵያ እና ተስፋዋ ሊያሰጋ ቢችል አይደንቀኝም። ያ የግለሰብ ሰብዕና ነው። በግለሰብ ሰብዕና ከተለካች ሊሆን ይችላል። ኢትዮጵያ ግን ማንነቷ #ከግለሰቦች #በላይ፤ በላይ የላቀ ብቃት እና ልዕልና በተመሠጠረ #ዊዝደም ስለተፈጠረች ተስፋዋ ይጠነዝላል ብዬ አላስብም። ኃያል ማንነቷ እኮ በ፮ ዓመቱ ኦነግ መራሽ ዘመቻ ሊፈራርስ አልቻለም። አለች እኮ። አይደል????
ወደፊትም ትኖራለች። የአማራ ህዝብ ዝቀሽ ትዕግሥት አስቀጥሏታል። ትናንትም በዘመነ ህወሃት አኟክ፤ ጉራጌ እና አማራ የደረሰባቸውን ጫና ተቋቁመው ኢትዮጵያችን አለችልን። ወደፊትም እኔ እንደ ሥርጉተ በአባታችን በአምላካችን በአላህ ቸርነት ፀንታ ትኖራለች ብዬ አስባለሁ። ግርማ ሞገሷ ኃያል ነው። እንደገና የአማራ ህዝብ መከራን የመሸከም ዝቀሽ ትዕግሥትም እስከ ቀጠለ ድረስ ኢትዮጵያ ትቀጥላለች።
ኢትዮጵያዊ ማንነት እራሱ ተፈጥሯዊ ተከላካይ መንፈስ አለው ብዬ አምናለሁ። ያ መንፈስ በተመረቁት ዘንድ ኢትዮጵያዊነትን ልጆቻቸውን መግበው ስለሚያሳድጉ ንጥረ ውህዱ በሰማያዊ ፀጋ በረከት ኢትዮጵያን ያስቀጥላታል። እንደ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እና እንደ ቲማቸው ቢሆንማ በትግራዩ ጦርነት እና በዓለሙ ማህበረሰብ ጫና የታሰበው በሆነ ነበር።
እኔ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የቀደምትነት ነቀላ እና እስያ ቀመስ የፒኮክ መንፈስ ስርፀት አይደለም ኢትዮጵያዊ ማንነትን እማዬው። እእ። ኢትዮጵያዊ ማንነት የራሱ አጥቂም ተከላካይ ርቁቅ መንፈስ አለው ብዬ አምናለሁ። በተለያዩ ኢቤንቶች ጠሚር አብይ አህመድ አሊ ብሄራዊ ሰንደቃችን ሲፀዬፋት፤ ሲነጥሉት እሳቸውን ልጆች እንዲከተሉ፤ የአፍሪካ መሪወች ኢትዮጵያን ከመንፈሳቸው እንዲያወጧት ሲጣደፋ "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም እዬተናገረ" የመሻታቸው ቅስም እንኩት ሲል አስተውያለሁኝ። አሁን ኬንያ ጉባኤውን እንደዛ በኢትዮጵያኒዝም ሲክነው የላይኛው እንጂ ሰው ሠራሽ አልነበረም።
የኦሮሞ ልጆች ወገኖቻችንም ውስጣቸው #ንጥር ነው። በቤተክርስትያናችን ተጋድሎ አኮሩን እንጂ አላሳፈሩንም። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ከኤሌትሪክ እንደገባ ፕላስቲክ ኩምሽሽ ያለውም ለዛ ነበር። ከአፈርኩ አይመልሰኝ ብሎ ሲፍተለተል እኔ ከቤቴ ሁኜ እስቅም ነበር። ኢትዮጵያዊነትን መዳፈር መቃብርን መምረጥ ነው።
ሌላው ውህድ ማንነት ያላቸው ዜጎቿ መጠጊያቸው ኢትዮጵንይዝም ነው። ይህ ሁሉ ቁጥር ሥፍር የሌለው ስውር ሠራዊት አለው ኢትዮጵንይዝም። ኢትዮጵያኒዝም ባልቦካ የጭቃ ምርጊት አልተሠራም። ፈጽሞ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሠንደቅ ሊንኩ ቢጫው አድዮ ነው። አድዮ ብሄራዊ አበባችን ነው። ብሄራዊ አበባ ያላት ቅድሥት ምድር #ኢትዮጵያ።
ኢትዮጵያዊ ማንነት የራሱ ንጥረ ቅመም ዝልቅ የአሸናፊነት፤ የተፈሪነት ድባብ ባለቤት ነው።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
09/06/2024
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ