ልጥፎች

ከጁላይ 11, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሁለተኛው ምዕራፍ የኳስ ዊድንግ ሻውር ... በመስኮ።

ምስል
124 ደቂቃ በመስኮ „በችሎቱ አምስግኑት በታላቅነቱ አመስግኑት።“  (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፶ ቊጥር ፪) ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) 90 ደቂቃ አልበቃኝም አለች። ናፈቀችው የኮራን ድልቃ እናም እሲከ በቃት ድረስ ተደቃች፤ ተሰለቀ፤ች ታሸች፤ ተሸከረከረች፤ ዳናሰች እስክሰክታውንም አስነካቸው….   ሁለተኛ ምዕራፏን ዊድንግ ሻውሯን ከኮራ ጋር አሳምራ ከውና ኮከቤ ለኮራ አሰኝቶኛል ስትል ወሰናች እቴዋ ድንቡልቡሊት ለዋንጫ ከመረጠቸው ጋር ከፈንሳይ አገር ሰንበት እንገናኝ ብላለች። ኮራዝድንገቴ ናቸው። እንደ ሽምቅ ተዋጊ አደጋ መጣል ይችላሉ። የሰውነት አቋማቸው ጠንካራ ነው። እንዳልኩት ኮራ ለዋንጫ ውድድር ከፈራንሳይ ጋር ይጋጠማሉ ብዬም ነበር ትናነትና። ባለፈው ሳምንት መሸኛ ላይ የጨዋታ ጊዜ ተራዝሞ ያም አልሆን ብሎ በፔናሊቲ ነበር ኮራ ራሺያን በባዕቱ ስደት ልኮ ነው ለዛሬ ቀን የበቃው …. እንግሊዞች በጥዋቱ ቀንቷቸው ነበረ። ብዙ ጊዜ ነፃ ምት ክርስቴኖ ሮናልዱ ነበር ለግብ የሚበቃው፤ ዛሬ እንግሊዞችን ቀንቷቸው የመጀመሪያ ግባቸውን አገኙ። በጥዋቱ ነበር ደስታ እንኳን ደህና መጣችሁ ያላቸው። ኮራ ትንሽ ግፊያ አብዝተው ነበር የቆዩት በሰጨኝ ብለው። የሆነ ሆኖ 68ኛው ደቂቃ ላይ ቀናቸው እና ቀጥለው ተፋልመው 90ው ደቂቃ በእኩል ነጥብ ጨዋታው ተራዘም። ጎሏ አገባቧ የነፍስ ያህል ነበረች። ወርቅ ነበረች። መጨረሻ ከሁለተኛ እረፍት መልስ ኮራ አቅሙ አጣናክሮ በትጋት እና በተከታታይ የማጥቃት ጥበብ ጥረቱ ተሳክቶ 109 ዲቂቃ ላይ ለስኬት በቃ።  ስለሆነም እንግሊዝን 2 ለ 1 በመሸኝት ለዋንጫ ከፈርንሳይ ጋር   የመጨረሻው ጨዋታ ይኖረዋል። ጨዋታን ...

መሆን ይቅደም!

ምስል
ህልምህን ስታገኘው በህልምህ ውስጥ ለመኖር ፍቀድ። „አስተዋይ መልካም ምክርን ገንዘቡ ያደርጋል“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭) ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) ·        ጠብታ። የሚገርሙኝ ነገሮች እጀግ በራካታ ናቸው ዛሬ ጥዋት ዩቱብ ያቀረብልኝ የዓለም አቀፍ ጋዜጠኛው የአቶ አለምነህ ዋሴ ዶር ለማ መgርሳ ለጨፌ ኦሮምያ ጉባኤ ያደረጉትን ንግግር መሰረት ያደረገ ነበር። „የያዙት ወርቅ ከመዳብ ቁጥር“ ነው እንዲሉ ያገኘነውን ወርቅ አያያዝ እንወቅበት የሚል ሁለንትና ዕድምታ አለው። እኔ ደግሞ የቀደመውን ብሂል ገልበጥ ላድርግ እና የያዙት ወርቅ ከመዳብ ሳይሆን ከብረትም አንሷል ባይ ነኝ። አዎን ዘመናይነቱ፤ ቅልጣኑ፤ የኬክ ቁረሱልኝ አቃቂሩ ስለሚያቅለሸልሸኝ። የትም ዓለም በዚህ በ100 ቀን ታይቶ የማያውቀውን ትንግርት ነው አላዛሯ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለችው፤ ዕውን አላዛሯ ኢትዮጵያ ናት ይህን ሁሉ የተግባር ዕንቁ በመሰብሳብ ላይ ያላቸው ያሰኛል? እኔ የጠበቅኩት ነው። ከመጀመሪያውም ጀምሬ የተጋሁበት ነው። እንዲያውም ይህ በግራ በቀኝ ውጥረት እና የሰላም ህውከት እዬተዋከበ የተከወነ ሲሆን የተረጋጋ ሁኔታ ቢገጥመው ምን ሊሆን እንደሚችል ሳስበው እራሱ ደረጃም፤ ልክም ለማውጣት ይቸግረኛል። ህውከቱን የወያኔ ሃርነት ትግራይ በፊታውራሪነት ያልታደለ በሉትና፤ ሌሎቹ ደግሞ የቤተመንግሥቱ ወንበር ቀረብን ያሉ ናቸው። ለውጡን ሊደግፉ ሲገባ ለውጡ ተቀልብሶ ለእነሱ የቀይ ምንጣፍ አሸሼ ገዳሜ እንዲውል ነበር ያለሙት። መከራው ይሄው ነበር። ቢሰጣቸው እኮ ለግማሽ ቀን አይችሉትም። ምክንያቱም ትንፋሻቸው ያጠረ፤ ዓይናቸው የጠበበ፤ ትእግስት ያልፈጠራላቸው፤...