ሁለተኛው ምዕራፍ የኳስ ዊድንግ ሻውር ... በመስኮ።

124 ደቂቃ በመስኮ
„በችሎቱ አምስግኑት በታላቅነቱ አመስግኑት።“
 (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፶ ቊጥር ፪)
ከሥርጉተ ሥላሴ 11.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)


90 ደቂቃ አልበቃኝም አለች። ናፈቀችው የኮራን ድልቃ እናም እሲከ በቃት ድረስ ተደቃች፤ ተሰለቀ፤ች ታሸች፤ ተሸከረከረች፤ ዳናሰች እስክሰክታውንም አስነካቸው….  
ሁለተኛ ምዕራፏን ዊድንግ ሻውሯን ከኮራ ጋር አሳምራ ከውና ኮከቤ ለኮራ አሰኝቶኛል ስትል ወሰናች እቴዋ ድንቡልቡሊት ለዋንጫ ከመረጠቸው ጋር ከፈንሳይ አገር ሰንበት እንገናኝ ብላለች።

ኮራዝድንገቴ ናቸው። እንደ ሽምቅ ተዋጊ አደጋ መጣል ይችላሉ። የሰውነት አቋማቸው ጠንካራ ነው። እንዳልኩት ኮራ ለዋንጫ ውድድር ከፈራንሳይ ጋር ይጋጠማሉ ብዬም ነበር ትናነትና። ባለፈው ሳምንት መሸኛ ላይ የጨዋታ ጊዜ ተራዝሞ ያም አልሆን ብሎ በፔናሊቲ ነበር ኮራ ራሺያን በባዕቱ ስደት ልኮ ነው ለዛሬ ቀን የበቃው ….

እንግሊዞች በጥዋቱ ቀንቷቸው ነበረ። ብዙ ጊዜ ነፃ ምት ክርስቴኖ ሮናልዱ ነበር ለግብ የሚበቃው፤ ዛሬ እንግሊዞችን ቀንቷቸው የመጀመሪያ ግባቸውን አገኙ። በጥዋቱ ነበር ደስታ እንኳን ደህና መጣችሁ ያላቸው።

ኮራ ትንሽ ግፊያ አብዝተው ነበር የቆዩት በሰጨኝ ብለው። የሆነ ሆኖ 68ኛው ደቂቃ ላይ ቀናቸው እና ቀጥለው ተፋልመው 90ው ደቂቃ በእኩል ነጥብ ጨዋታው ተራዘም። ጎሏ አገባቧ የነፍስ ያህል ነበረች። ወርቅ ነበረች። መጨረሻ ከሁለተኛ እረፍት መልስ ኮራ አቅሙ አጣናክሮ በትጋት እና በተከታታይ የማጥቃት ጥበብ ጥረቱ ተሳክቶ 109 ዲቂቃ ላይ ለስኬት በቃ።


 ስለሆነም እንግሊዝን 2 ለ 1 በመሸኝት ለዋንጫ ከፈርንሳይ ጋር  የመጨረሻው ጨዋታ ይኖረዋል። ጨዋታን ከአሸነፈ የመጀመሪያው ዋንጫ ነው የሚሆነው በታሪኩ። ይህ ለትናንሽ አገሮች ሰፊ የሆነ መነቃቃት ይፈጥራል። የጨዋታውንም ስታይሊንግ ይቀይረዋል። ዬዬአራት ዓማቱ ጨዋታ ተመሳሳይ ቡድኖችን ለሴሜ ፋይናል ከቀረበ አልጫ ያደርገዋል የፊፋን ዓላማ። ተነሳሽነትንም ያጫጫል። ዘንድሮ ደስ ይላል ኮራ አዲስ ቡድን ነው ለዋንጫ ሲወዳደር እናም ልብ ያንጠለጥላል … አመጣጡ ድንገቴ ነው ልክ እንደ ኢትዮጵያዊው ሙሴ ስለዚህ በለስ ይቀናዋል የሚል ግምት አለኝ።

እርግጥ ነው ፈረንሳይ ከእንግሊዝ በቡድን ጨዋታ ብልጫ አለው ብዬ አምናለሁኝ። ስለዚህ ኮራ ጠንከር ያለ ፉክክር ይገጥመዋል ብዬ አስባለሁኝ። ፈረንሳዮች ሁሎችም ተመጣጠኝ አቅም እና ብቃት አላው።  ደካማ የሚባል አላይባቸውም ስለዚህ ፉክክሩ የጠና ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። ማንኛቸውም ቢያሸነፉ ደስ ይለኛል። ኮራ ድንገተኛው ካሸነፈ የዓለምን የእግር ኳስ ነባር ታሪክ በብዙ ሁኔታ እና መልኩ ይቀይረዋል። አዲስ የሥነ ልቦና አቅም ደክም ላሉ አገሮች ይፈጥርላቸዋል። በተለይ ለአፍሪካ።

 … ለውጥ ጥሩ ነው ይጥማል … ይኼው አላዛሯ ኢትዮጵያ በዬቀኑ ደስ የሚል ብሥራት የምትሰማው እንደ ሟርተኞች ጉልቻ ተለወጠ ወጥም ጣፈጠ …

እንግዲህ የሠርጉ ዕለት እንደ አቅማችሁ ስጦታችሁን ቆጣጠራችሁ ሞስኮ ላይ እንገናኝ በይልኝ ብላለች እሜቴ ድንቡልቡሊት …

ስፖርት የሰላም መሠረት ነው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።