Zenebe Kassie እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር።
እሙኃይ እንኳን ደስ አለወት። እናት ዓለም በረከተወት ይድረሰኝ። አሜን። እሙኃዮዋን እናቴን ያስታወሰኝ እለት ነበር። እንደአከላተምኳት ፈቃዷን ሳልፈጽም መራራ ስንብት ሆነ። ይህ መከራ የመጨረሻ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው። ከውስጤ ስለ እናቶቼ አስባለሁ። አንገላትተናችኋል። አሰቃይተናችኋል። ሃዘን ስጦታ አቅርብነልቻኋል። ይቺ አገር ኢትዮጵያን ብለን ግን እራሳችን ረስተን ወጣትነታችን፤ ሐሴታችን ሁሉን ሰጥተን አሁንም እዛ ረግረግ ውስጥ መሆናችን ሳስበው ምጡ ምጥ ብቻ አይደለም። በሽታ ይገዛል። የሆነ ሆኖ ከእሱ አብራክ የተፈጠሩ ልጆቹ፤ እሱንብላ አብራ እምትከላተመው የትዳር አጋሩም ያሳዝኑኛል። እንኳን ደስ አላቸው። ብቻ ለመኖር ለወሰነው ቢያንስ ይህን አቃለናል ብዬ አስባለሁ። ለዘኔ ከእህት። "ላም እረኛ ምን አለን" እባክህ አዳምጥ። በጥዋቱ ጽፌልህ ነበር አልሰማህኝም። 1) በምግብ ሊበክሉህ ስለሚችሉ ብርቱ ጥንቃቄ አድርግ። 2) ቅንነትህን በቅጡ አስተዳድረው። ፖለቲከኛ ቅንነቱ ብቻ ለድል አያበቃውም። ጥበብ ያስፈልገዋል። 3) ገራገርነትህንም እንዲሁ ማኔጅ አድርገው። ዓላማን በራስ እጅ ለማበጀት መወሰን ጎዳናህ ይሁን። 4) ለአንተ ሲሉ 12993 ተማሪወች ቤተሰቦቻቸው ወደ 64 ሺህ ከተስፋ ውጪ መሆናቸው ግቡን እና ስኬቱን አጥናው። ለቀጣዩ እርምጃ ስለሚረዳህ። 5) የህዝባችን መሰዋት በሚቀንሱ በሚያመጣጥኑ መንገዶችብቻ ጥናት ውሰድ። ብዙውን በርደን ውጭ ያለው ይፈጽም። እናንተ ቋያ ውስጥ ናችሁ እና። 7) ለጥሞና አላማህም። ቆራጥ ነህ። ብቻህን ለአጅም ጊዜ የገደምክ ቆራጥ ወጣት ነህ። አገር ተደፈረችሲባል ነው የወጣህው። ያን ጊዜም ጽፌ ነበር። እዛው ሁን ብዬ። በቀለኛ ሥርዓት ስለሆነ ይቀሙናል በሚል። አሁንም #ጥሞና ውሰድ። እራስህ...