ቢያንስ አውሮፕላኑ ሰርጎ ከገባበት ጥልቀት ባነሰም እራስን መፈተሽ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ ይጠይቃል
እንኳን ደህና መጡልኝ። ቢያንስ አውሮፕላኑ ሰርጎ ከገባበት ጥልቀት ባነሰም እራስን መፈተሽ ወደ ፈጣሪዬ መመለስ ይጠይቃል፤ - የወቅቱ የመከራ አስተምህሮ - ይህ ይመስለኛል። „እግዚአብሄር የበቀል አምላክ ነው። የበቀል አምላክ ተገለጠ።“ መዝመር ፺፫ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ነፍስ ይማርልን አማኑኤል አባታችን!አሜን! · ፍላሎት … የሲንጋኮፕር እርምጃ ደግሞ ይገርማል። ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በዬር ወሰኗ ለተወሰነ ጊዜ ትውር እንዳይል እገዳ ጣለች። በዚህ በመጋቢቱ መባቻ 2011 ዕለት በተከሰተው አደጋ መሰረት ኢትዮጵያ፤ ደቡብ አፍሪካ፤ ሜክስኮ እና ቻይና በዚህ አውሮፕላን በረራ የማድረጉን ነገር ጊዜያዊ ማዕቀብ ጥለዋል። የቦይንግ 737 ማክስ የሱባኤ ጊዜ። እኛም እንደለመደብን እንደ አምናው ዘንድሮም ሱባኤ ላይ ነን። ሁዳዴው የግሎባሉም ሆኗለኝ። እንዲህ ለመከራ ጊዜ አንድ የሃዘን ወቅት እንደሚኖርንም ግሎባሉ እንደሚሆነው በተለመደው የመኖር ዘይቤስ ምን አለ ፍቅሩን ቢሰጠን? · ነገረ በረራ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ነፍሴ ከበረራ ጋር ከተጣመረ አምስት አመት ሆነኝ። የዛ ጀግና የዛ የሰባዕዊ መብት ተሟጋች፤ የዛ ጠንቃቃ፤ የዛ አስተዋይ የረዳት አውሮፕላን አባራሪ ሃይለመድህን አበራ ጄኔባ አውሮፕላን ማርፊያ በሰከነ...