"ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኽ።" "ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ወጭት ጥዶ ማልቀስ።"
"ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኽ።" "ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ወጭት ጥዶ ማልቀስ።" "አገራዊ" ምክክር ኮሚሽኑን ሳስብ ሟቹ ተስፋዬ ገብረአብ ታሪክን እንዳይደግመው እሰጋለሁኝ። የሆነ #ልብወለድ ታሪክ በአዲስ እንደ ቡርቃ ዝምታ ኮሚሽኑ ይፃፍ ይሆን እላለሁኝ። ኢትዮጵያን #ተቀላች ፣ #ተጠማኝ ፣ #ጥገኛ ፣ #ምርኮኛ የሚያደርግ የታሪክ ዝገት በራስ አገር ልጅ እንዳይፈጠር ያሰጋኛል። አዲስ አበባ "ክልል ትሁን፣ አዲስ አበባ ራስ ገዝ" ትሁን ከውድድር ውጪ የሆነበት ሁኔታን ከውስጤ ሳስበው።) #ምዕራፍ ፲፱። 1) #የአብን እና የብልፄው ፍቺ በአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአቅም ኩነት ላይ። 2) " #የአገራዊ " ምክክር ኮሚሽን አብን ስላቀረበው ቅሬታ የሰጠው ማስተባበያ። 3) " #የአገራዊ " ምክክር ኮሚሽኑ የመብት ልክን ያጋለጠው የአቶ ያሬድ ኃ/ማርያም መረጃ (የህግ ባለሙያ እና የሰባዕዊ መብት ተሟጋች።) BBC የኮሚሽኑን ማስተባበያውን ይዞ ወጥቷል፣ የአቶ ያሬድን መረጃ እና የአብን #ደፋር መግለጫ ከፌስቡካቸው ያገኜሁት ነው። "ልብህን በምግባር አቅና፣ መከራውንም ታገስ፣ አትጠራጠር በመከራውም ብትጠራጠር አትጠራጠር።" (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፪ ቀጥር ፩) አቅምን መጥኖ ማስተዳደር ይገባል። የኦሮሞ ብልጽግና ፍላጎቶን በግልጽ ሲያሳውቅ ነው የኖረው። ያን አድምጦ አቅምን በቅጡ መያዝ፣ የአቅም መግቦቱንም ማመጣጠን ይጠበቅ ነበር። ሌላው ወሳኝ ጉዳይ ለመደገፍ ይሁን ለመቃወም እንዲሁም እንደ እኔ #ለመሞገት የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ አጥንቶ መነሳት ይገባል። ዴሞግራፊን እኔ #አሉታዊ እና #አወንታዊ ብዬ በሁ...