እኔ ሥርጉተ©ሥላሴ ብልፄውን ስለምሞግት የደፂን ህወሃት ልደግፍ #አልችልም። ፈፅሞ! መቼውንም! ለምንግዜም!

 

እኔ ሥርጉተ©ሥላሴ ብልፄውን ስለምሞግት የደፂን ህወሃት ልደግፍ #አልችልም
ፈፅሞ! መቼውንም! ለምንግዜም!
 
"እግዚአብሄርን መፍራት ክብር ነው፤
የሚያስመካ ተድላም፤ ደስታም ነው፤
ተድላ ደስታ ይሰጣል፤ ደስም ያሰኛል፤
በሕይወት የሚኖሩበትን ዘመን ያበዛል።"
 
#ምዕራፍ ፲፱።
 
ህወሃት የሚለው የዞግ የፖለቲካ ድርጅት ስለተከፋፈለ፤ አንደኛውን ክንፍ #የደፂ ህወሃት
ወይንም #ደፂዝም ማለት ይገባል። 
 
አሁን ባለው ፖለቲካዊ ጭብጥ በቀደመው ሥም መጥራት የተገባ አይመስለኝም።
ህወሃት ሆነው ግን የህወሃትን አሁናዊ #ትወና ሊጋሩ የማይፈልጉ ወገኖች ስላሉ።
 
ወጣትነቴን አላውቀውም። ስለእኔ አስቤ አላውቅም። እኔን "የእኔ" አጀንዳ አድርጌም
አላውቅም። በማገኛት አጋጣሚ ሙሉ መንፈሴን ከእኔ ውጭ ላሉ ሰብዕናወች አስባለሁ፤
እጨነቃለሁ፤ የምችለውን አደርጋለሁኝ።
 
ዘመኔን ቅርጥም አድርጎ የበላው ደግሞ አውራው ህወሃት እና #ጨካኙ ጉዞው ነበር። ብዙ
በጣም ብዙ አቅሜን ያለ ገደብ በጸረ - ህወሃት ትግል ሰጥቻለሁኝ።
 
በቤተሰብ ይሁን በማህበራዊ ጉዳይም "ለእኔ" የሚል ሁነት ቀድሞብኝ አያውቅም።
ስለሆነም የድምጽ አልባወቹ የኢትዮጵያ እናቶች #ዕንባ መሪዬ፤ መስመሬ መርሆዬ ነው።
 
ፈጣሪ እረድቶን በራሱ በአምላካችን ጥበብ ፈቅዶ ህወሃት እራሱን ከመንበረ መንግሥቱ ሸኜ።
ይህ ትንግርት፤ ታምር ስለነበረ ከዚህ በኋላ በህወሃት ላይ የሚነሱ ወቀሳወች መበርከት
የለባቸውም ባይም ነበርኩኝ።
 
ህወሃት የአማራ ክልል እና አፋርን እስከ ወረረባት ቅጽበት ድረስ፤ የኢትዮጵያ ዜጎችን ቁስለት
ከዓለም ዓቀፍ ሚዲያ የማገኘውን መረጃ #በእኩልነት ዘገብኩኝ።
 
ጦርነት ለእኔ #ቤርሙዳ ትርያንግል ነው። እምትወደውን ያሳጣኃል። ቂም - ያመርታል። በቀል -
ያጫል። ጥላቻን - ያፋፋል። አገር ያሳጣኃል። ይህ ጎምዛዛ ገጠመኝ ነው።
 
ይህ የእኔ መስመር ፈፅሞ አይደለምና ጦርነትን የመደገፍ፤ #የማቆላመጥ፤ በዛ ውስጥ ሆኖ
መንፈስን ማባተል አልሻም። አላደርገውምም።
 
ሲጨንቃቸው፤ ሲቸግራቸው፤ መግቢያ መውጫ ሲያጡ ይህን መስመር የሚከተሉ ይኖራሉ። በሌላ
በኩል የበለጠ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን የሚያስቡም እንደ ዘለንስኪዝም ያሉም ይገጥማሉ።
 
በዚህ በሁለቱም መስመር አክተሮች አይጎዱም። ንጹኃን ይጎዳሉ። ንጹኃን ዋስትና ያጣሉ፤
ስለዚህም ከጦርነት በመለስ ያሉ የትግል መስመሮች፤ መስዋዕትነትንም ስለሚቀንሱ፤
በተግባርም ህወሃትን ያሰናበተ ጤነኛ መንገድም ስለሚኖር ጦርነቱ ያስፈራኛል።
 
ግን የህዝቤ - ጉዳት፤ የአገሬ ሥልጣኔ ውድመት - ይቆረቁረኛል። #ተውም እላለሁኝ። አሁንም ተው!
እላለሁኝ። ከዚህ ባለፈ እራሴን አፍርሼ፤ የገነባሁትን የራሴን አሻራ #ንጄ ጦርነትን ጎሽ የደፂዬ¡ ህወሃት
እንኳ "ደህና መጣህ" አልለውም። 
 
ለእኔ ለሥርጉተ©ሥላሴ ስለ ህወሃት ይሁን ስለ ሻቢያ፤ ስለ አገሬ ፖለቲካ ቀስቃሽ ፕሮፖጋንዲስት
አያስፈልገኝም። እኔ ደራሽ ፖለቲከኛ አይደለሁም። ወይ ትንሽዬ ጊዜ ፋታ ሰጥ ሁነት ሲገኝ ከጎርፋጎርፍ
ጋር ከች ያልኩ አቤቱ ጎርፍ አምጥቶ ደለልም የሠራብኝ አይደለሁም።
 
ስለ አገሬ ፖለቲካ፤ የሰብአዊ መብት አያያዝ፤ የየፓርቲወች አደረጃጀት እና አወቃቀር የሠራሁበት መስክ
ነው። ተኝቼ - አላውቅም። አንቀላፍቼ - አላውቅም። ሁሉንም በቅንነት አያለሁ። ዝበት ሳይ ደግሞ በብዕሬ
እሞግታለሁኝ። አክብሬ በትህትና ነው የማይመቸኝን አካሄድም እምሞግተው።
 
በተለያዬ የፖለቲካ ድርጅት ያሉ፤ በጓዳ እየመጡ በተለያዬ ሁነት #እንዳግዛቸው ለሚጠይቁኝ አክባሪ ወገኖቼ ሁሉ እኔ
የራሴ ጎዳና፤ የራሴ አሻራ ያለኝ ስለሆነ እራሴን አፍርሼ የምዳበለው፤ ወይንም ፈቅጄ የማዳብለው፤ ወይንም በቁሮነት
የምቀበለው ምንም ነገር አይኖርም። #ሥርጉቲዝም እራሷን ችላ በራሷ መንገድ የመጓዝ አቅም አላት።
 
ሥልጣን፤ ክብር፤ ውዳሴ፤ ሞገስ፤ ሰፊ ደጋፊ የሚሹ መንፈሶች ተዋህደው፤ ተመጋግበው ወይንም ተጠጋግተው አብረው ይሥሩ።
#አዋን ( አዋን የጎንደሪና አማርኛ ናት) ተገኝቶ ነው ህብራዊነት። እኔ ግን የእኔው አለቃው የእኔው ሃሳብ ብቻ ነው። ተስፋዬም የራሴ ጥንካሬ ብቻ ነው። ጥገኛ መሆን አልፈልግም።
 
አብሬ ሠርቼም በአንጃ ክፍፍል የሚመጣ የመንፈስ ድቀትም እንዲጎበኜኝ አልፈቅድም። ተያይዞ ማክተም አይናፍቀኝም። ለዛውም ከከርቤው የደፂ ጉድጓድ ፍላጎት ጋር። 
 
በውነቱ ወድቆም አያውቅ - ጥረቴ። ሰንፎም አያውቅ - ትጋቴ። ሽባ ሆኖም አያውቅ - ነፃነቴ። ለምን? በራስ አቅም መንቀሳቀስ
ቢወደቅም፤ ቢነሳም በራስ ጥረት ስለሚወሰን።
 
አብይዝምን በጥዋቱ #ከግንቦት 5/2010 ዓም ጀምሮ እሞግታለሁኝ። ወደፊትም - ይቀጥላል።
ግን አብይዝምን ስሞግት ያ ቤርሙዳ ትርያንግሉ የደፂ ሙሽርነት ናፍቆኝ አይደለም። ሊሆን አይችልም።
ምክንያት የደፂ ህወሃት ሰውኛም፤ ተፈጥሮኛም መቸውንም የመሆን አቅም ስለለው። አብይዝምስ?
የሚል ጥያቄ ሊመጣ ይችላል። ይኽው በቋሚነት እየሞገትኩት አይደል።
 
ለጠቅላዩ አውሮፓ ላይ ቅልጥ ያለ አቀባበል ሲደረግ፤ በሰልፍ ኢትዮጵያ ሲገባ፤ በሰልፍ የጦርነቱ ጊዜ
ድጋፋ ለአብይዝም፤ የገንዘብ ማሰባሰብን ከኢትዮጵያ ኢንባሲ ጋር ተፍተፍ ሲል የነበረ መንፈስ ዛሬ
እኔን ስሙ ቢል አላዳምጠውም። 
 
ድጋፋ በየዓይነቱ ሲጎርፍ፤ ኢትዮጵያን የማየት ዕድል እና ዲል ባለ አቀባበል እና ግጥግጥ አብሮነት
ቅብጥ እና ቅልጥ ሲል ሥርጉትሻ በዛው መሥመር ነበር ደርበብ ብላ የቀጠለች። ሙቀት የለ፤
ፍላት የለ፤ ፍላሎታዊ ወበቅ የለ። #በረዶነት የለ። በነበረው የሙቀት ልክ ይኽው ቀጥያለሁኝ።
 
አገር የገቡትን መውቀሴ አይደለም። የአፈር ናፍቆት አይቻልም። ወላጅን ማዬት ታላቅ ብሥራት ነው።
እንኳንም ይህን ፈጸማችሁ። ጸጸት የለበትም። አብይዝን የመሞገት መብቴን ለራሴ እያኮመኮምኩ፤
አብይዝምን ደገፋችሁ ብዬ ቃር አላመርትም። መብት ነው።
 
የደፂ ህወሃት ሥልጣን ላይ ያሉ የብልፄው ኦህዴዶች እኮ እየናፈቁት መሆኑን እየሰማን ነው።
በአንድ ወጥ ፓርቲ ውስጥ ይህን ያህል #ሽፍትነት???
 
የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ለአንዲት ሳምንት የደፂ መንፈስ ቢሳካለት ኦሮምያ፤ ሱማሌ ክልል፤
ከአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፤ እና የአማራ ክልል "ዋና ከተማ" ባህር ዳር የበቀል #አመድ ተመጋቢ ይሆናሉ።
የሆነ ሆኖ የአብይዝም እና የህወሃት ጦርነት አያስፈልግም ብዬ ቀድሜ የሞገትኩት እኔው ነበርኩ።
 
የመቀሌ መያዝ #ርችትን ሳይ ደስታችሁን በልክ ያዙ … በሦስት ምክንያት ብዬ ……
 
1) ተጨማሪ ደስታ ስታገኙ መደርደሪያ እንዳታጡ፤
2) ደስታችሁ ሲተን የሥነ - ልቦና ተጠቂ እንዳትሆኑ፤
3) የእግዚአብሄር ምርቃት እንዳይነሳ፤ በማለት ያንጊዜ አበክሬ ሞግቻለሁኝ። 
 
በቀጣይም አብይዝም - ይሞገታል። ግን የደፂ ህውሃትሻ¡ የደፂ ህውሃትዬ! ናፍቀሽኛል¡ እና ነይልኝ¡
ከች - በይልኝ¡ ብዬ ቅንጣት አቅም አላዋጣም። መንፈሱንም ጭራሽ #አላስጠጋውም። 
 
ሙሉ ፷ ዓመታት እምንታመስበት #ክፋ ሃሳብ መሥራች ይሁን #አናፂው ይሁን #አንጠረኛው፤ አረም
አብቃዩ፤ አረማሞው የህውሃት ሰው ጠል ዶክተሪን ነው። የአማራ ጠል ፍልስፍናው ነው። "የህወሃት
ምሥረታ ትክክል ነበር የሚሉ ወጣቶች" አድምጫለሁኝ። ሰቅጣጭ ሃሳብ ነው።
 
እኔ በህይወት እያለሁ ለጸረ - ሰው ማኒፌስቶ የአቅም መዋጮ፤ ሰርግ እና መልስ በእኔ ቤት አይታሰብም።
ህወሃት ልጆች አሉት። ህወሃት የልጅ ልጅ አሉት። ህወሃት አያት ለመሆን ችሏል። መከራው የማያባራውም
ወራሾች ስላሉት ነው።
 
ግን ህውሃት መምህር አቤል ጋሹ እንዳሉት " ህወሃት የመቃብር #ሬሳ ነው።" ለእኔም። ከልጅነት እስከ
ዕውቀት ነገረ - ሻብያ ይሁን፤ ነገረ - ህወሃትን በሚመለከት እያዬሁ እየሰማሁ ነው ያደግኩት።
 
ጦርነትን እኮ እኔ ያደግኩበት ነው። ጦርነት በቀል፤ ጥላቻ እና ቂም ከማምረት ውጪ ሌላ አስተምኽሮ
የለውም። ዘመንን ጢስ የሚያለብስ ራቁት ክስተት ነው። #አራቋች
 
ክብረቶቼ ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
16/08/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።