ተመክሮ ለመከረው ክብር ይገባዋል!
ብስለት። ተመክሮ ለመከረው ክብር ይገባዋል! „ቀን የሚያመጣው ምን እንደ ሆነ አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ከሥርጉተ©ሥላሴ 27.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ሊሂቃኑ የኢትዮጵያን የምሥራች ቀን ተገኝች ክብርት ትናፍቅሽ ሲባል አስከዛው ድረስ ነው እያሉ በሚመጻድቁበት ማግስት ትናንት አቶ ሌንጮ ለታ አንድ ቁም ነገር ላይ እርገት አድርገዋል። ከዚህ ቀደመም የሸግግር መንግሥት አያስፈልግም ብለው ፊት ለፊት ወጥተው የሞገቱ ነበሩ፤ የዶር መራራ ጉዲና ህሊና የተጽዕኖ ፈጣሪዎችን የአንድነት መንግሥትን አዲስ ሽል ይዞ ብቅ ሲል፤ ሌላውም የሽግግር መንግሥት አሁኑኑ በማለት መለከቱን ሲነፋ አሳቸው ግን ግን አያስፈልግም ብለው ነበር አቋም የያዙት። ወደ አገር ሲገቡም አጀብም፤ ጭብጨባም፤ ስልፍም አላስፈለጋቸውም እዩን እዩን አላሉም እንደ ማለት። በዛው ሰሞናት ደግሞ ከአህዱ ራዲዮ ጋር ውይይት ሲያደርጉ ስለምን ያን ያህል ወጣት በባዶ እጁ ሲረግፍ ያልነበረ ድረጅት አሁን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ግርም ብሏቸው የት ነበር የዳውድ ኢብሳ ሠራዊት ያን ጊዜ ወጣቶቹ ሲያልቁ በጥይት ሲቆሉ ሲሉ ተደምጠዋል። በአህዱ ራዲዮ ቃለ ምልልስም ምርጫው በተያዘለት ገደብ ይከውን ብለው ግን መከወኑ አሁን ያለው ለውጥ ህጋዊ እውቅናውን ለማስገኝት ቢሆን የሚል ዕድምታ ነበረው እሳቤያቸው በቅጡ ከተፈተሸ። ትናንት ደግሞ ልብ ያለው ነገር ገልጸዋል፤ ራሳችን በ እርጋታ እሰክናደራጅ ድረስ እኛ በመጪው ምርጫ አንሳተፍም ለውጡ መሠረት እንዲይዝ እንተጋለን ብለዋል። ደፋር እርምጃ ነው ። ደፋር እርምጃ ነው እምለው በምርጫው አለመሳተፋቸውን ...