ተመክሮ ለመከረው ክብር ይገባዋል!

ብስለት።
ተመክሮ ለመከረው
ክብር ይገባዋል!
„ቀን የሚያመጣው ምን እንደ ሆነ
አታውቅምና ነገ በሚሆነው አትመካ።“
 መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ
ከሥርጉተ©ሥላሴ
27.11.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


ሊሂቃኑ የኢትዮጵያን የምሥራች ቀን ተገኝች ክብርት ትናፍቅሽ ሲባል አስከዛው ድረስ ነው እያሉ በሚመጻድቁበት ማግስት ትናንት አቶ ሌንጮ ለታ አንድ ቁም ነገር ላይ እርገት አድርገዋል። 

ከዚህ ቀደመም የሸግግር መንግሥት አያስፈልግም ብለው ፊት ለፊት ወጥተው የሞገቱ ነበሩ፤ የዶር መራራ ጉዲና ህሊና የተጽዕኖ ፈጣሪዎችን የአንድነት መንግሥትን አዲስ ሽል ይዞ ብቅ ሲል፤ ሌላውም የሽግግር መንግሥት አሁኑኑ በማለት መለከቱን ሲነፋ አሳቸው ግን ግን አያስፈልግም ብለው ነበር አቋም የያዙት። ወደ አገር ሲገቡም 
አጀብም፤ ጭብጨባም፤ ስልፍም አላስፈለጋቸውም እዩን እዩን 
አላሉም እንደ ማለት።

በዛው ሰሞናት ደግሞ ከአህዱ ራዲዮ ጋር ውይይት ሲያደርጉ ስለምን
ያን ያህል ወጣት በባዶ እጁ ሲረግፍ ያልነበረ ድረጅት አሁን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ግርም ብሏቸው የት ነበር የዳውድ ኢብሳ ሠራዊት 
ያን ጊዜ ወጣቶቹ ሲያልቁ በጥይት ሲቆሉ ሲሉ ተደምጠዋል። 

በአህዱ ራዲዮ ቃለ ምልልስም ምርጫው በተያዘለት ገደብ ይከውን ብለው ግን መከወኑ አሁን ያለው ለውጥ ህጋዊ እውቅናውን ለማስገኝት ቢሆን የሚል ዕድምታ ነበረው እሳቤያቸው በቅጡ ከተፈተሸ። ትናንት ደግሞ ልብ ያለው ነገር ገልጸዋል፤ ራሳችን በ እርጋታ እሰክናደራጅ ድረስ እኛ በመጪው ምርጫ አንሳተፍም ለውጡ መሠረት እንዲይዝ እንተጋለን ብለዋል። ደፋር እርምጃ ነው። 

ደፋር እርምጃ ነው እምለው በምርጫው አለመሳተፋቸውን አይደለም። ምርጫ ለመሳተፍ የተመዘገቡት ፈሪዎች ናቸው ለማለትም አይደለም። ማንም ሰው ሲደራጅ በፖለቲካ ድርጅት በምርጫ ተወዳዳሮ ለማሸነፍ እና ለመሸነፍ ስለሆነ ለወዳደር የሚወስኑት ሙሉ መብታቸው ነው። እናም የተጋገባ ነው። 

ባይሆን መሳናዷቸው ነው አነጋጋሪው ጉዳይ እንጂ። እራሱ የሁለተኛ ጊዜው የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከተነሳ በሆዋላ እንኳን ተግባር ላይ ቢገኙ በተለይ አገር የነበሩት መልካም ነበር የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጉዞ አቃቂር አውጪ ዘጋቢ ከሚሆኑ። አገር የገቡትም እንዲህ መሰል አቋም የሌላች ትንሽ መነቃሰቀስ ቢሞክሩ መልካም ነበር ሃኒ ሙኑን ከሚያሳድዱ። ቀድመው የገቡት በውነቱ 6 ወር እንዲሁ በዋል ፈሰስ አቃጥለውታል። ቢያንስ በሚቻልበት ቦታ ትንሽ መንቀሳቀስ ያስፈልጋቸው ነበር። 6 ወር ቀላል አልነበረም። 

የሆነ ሆኖ እኔ የአቶ ሌንጮ ለታን የሳቸውን የዚህን ውሳኔ ቃና ሳስበው እየተነሱ እዬወደቁ ያሉ መንፈሶች፤ ያሉ ያልሰከኖ ቅብጥብጥ ነፍሶች በተደሞ መርምረው፤ በተደሞ የወሰኑበት ጉዳይ ነው ብዬ አሰባለሁኝ። ራሱ የኦሮሞ ድርጅቶች አንድን ህዝብ ከ6 በላይ ከፍ ያለ ነው።

ይህን የአንድ ህዝብን ከ6 በላይ መንፈሱን በሽንሸና አውኮ አቅምን ከማባክን የተራጀንበት ዓለማ የሚያስፈጽም ኦዴፓ ከኖረ፤ እሱ እኛ የምንፈልገውን ከፈጸመው እኛ ተደራቢ ሆነን አቅሙን ለመበትን፤ አትኩሮቱን ለማወክ አንተጋም ነው። የኛን ፓርቲ ለማደረጃት አንጣደፍም። ዘመን አናጋሪ ብልህነት ነው፤ ተነባቢ ብልህነት ነው፤ ተመክሮ እንዲህ ሲያሰብል ማዬት ለትውልዱም ተቋም ነው። መቼም ክልፍልፉን ክልላችን ነው እያለ የሚያውከውን መንፈስ ሁሉ አከርካሪዊን እንኩት ነው ያደረጉት። ይባረኩ!

አቅምን ለመበትን ያለው ትጋት፤ አቅምን አቅጣጫ ለማስቀዬር ያለው ግብግብ አብሶ ለኦሮሞ እናት ዳግም እንባ ያለው መሰናዶ እና ውርክብ እንደ ዜጋ እጅግ የሚያርመጠምጥ ጉዳይ ነው። ይህን ልብ ያላለው የአቶ በቀለ ገርባ፤ የአቶ ጃዋር መሃመድ፤ የአቶ ዳውድ ኢብሳ መንፈስ ሌት እና ቀን ይባትላል ለመተርትር ድሉን አሳልፎ ለበላሃሰብ ለማሰጠት ከወያኔ ሃርነት ትግራይ በላይ አጀንዳው አድርጎ የ ኦህዴድን አቅም ሲበትን ሲሰነጥቅ ውሎ ያድራል።

ፉክክሩ ሩጫው ኦህዴድን አቅመ ቢስ አድርጎ፤ ከጫዋታ ውጪ አድርጎ የሌላ ሲሳይ ድካሙን ለማድረግ ነው። መቼም በጥርስ የተዬዘው የአብይ ካቢኔ ከምድረ ገጽ ቢጣፋ ምኞታቸው ነውና።

ይህን ነው በተደሞ ዘለግ አድርገው አቶ ሌንጮ ለታ የገመገሙት። ትልቁ የአላዛሯ ኢትዮጵያ ችግርም አቅምን እንዴት መያዝ፤ አቅምን እንዴት መምራት፤ አቅምን እንዴት ማስተዳደር፤ አቅምን እንዴት መንከባከብ አለማወቅ ነው። ለእነ አቶ ሌንጮ ፓርቲ ገበርዲን ከርባት ወንበር ዝና በውነቱ በዚህ አገላለጻቸው ፋይዳ ቢስ ስለመሆኑ ነው ያመሳጠሩልን። የኦህዴድ ልጆችም የእኛው ናቸው ባይ ናቸው። የተገኘውን ለውጥ እንዳይቀለበስ ወታደር ሆነውታል። ትልቅ የህሊና በረከትም አበርክተዋል። ገብቷቸዋል። 

                               ፎቶ ከኢትዮ ሪጅሰተር የተወሰደ።

አቶ ሌንጮ ለታ የሚሉት የለውጡን ሐዋርያት ልንደግፋቸው፤ ልናግዛቸው፤ ልናበረታታቸው እንጂ አቅማቸውን ልነፈታተነው፤ ልንፎካከረው፤ መቅኖ ልናሳጣው አይገባ ባይ ናቸው። በዛ ላይ አኩርተውናልም አለበት። ሥልጡን ዕሳቤ ነው። ረቂቅ ነው እንጂ 
ብዙ ድካምም ያቀላል። ለኦህዴድ አንድ ሸክም ተቃሎለታል።
ለውጡ እንዲቀጥል ለምንፈልግ ቅኖች ደግሞ ልዩ ሥጦታ ነው። መንፈሱን የትርምሱን አስኳል አግኝተውታል። ብዙ ነገርን ታዝበው የደረሱበት መደምደሚያ የልቤ የሚያስብል ነው። 

ሌላው አክብሮታቸው ድንቅ ነው። በተጠሩበት የሰብሰባ ቦታ ሁሉ ራሳቸው ይገኛሉ። ቀድሞ ከእነ ሳጅን በረከት ቅርፊት መፍትሄ ይገኛል ብለው በዬተጠሩበት የሚገኙት አሁን አይገኙም። ስለምን መታበይ አወቅኩሽ ናቅኩሽ ስለሆነ። ለነገሩ ራሱን ያላከበረ ነው ሌላውን ሊያከብር የማይችለው። 

ለነገሩ ራሱን ጠ/ሚር አድርጎ ለሾመም መንፈስም እንዲሁ መከራ ነው ከሥር ቁጭ ብሎ ለመታደም፤ እጁን አውጥቶም ጥያቄም ሆነ አስተያዬት ለመስጠት። ሁልጊዜ ቁብ ተለምዶል እንዴት ተወዴት። መምራት ነው እንጂ ለመመራት ፈቃዱ ከዬት ይመጣል። ተመክሮው ሁሉ እውሃ የበላው ቅል ሲሆን ነው በዬፌርሜታው የሚታዬው።

አቶ ሌንጮ ለታ ግን በተጠሩበት ቦታ ሁሉ ይገኛሉ፤ ቃለ ምልልስ ይስጡ በታበሉበት ቦታ ሁሉ ተገኝተው ይሳጣሉ፤ የፕሮቶኮል የሲናሪዮ የክብር ጉዳይ ጉዳያቸው አይደለም። ስለዚህ አንዱን ትልቁን የመሪነት መርሆ እዬተገበሩት ነው ባይ ነኝ። አሁን አሁን እማዬው መታበይ በሌሎቹ ላይ እጅግ ይገርመኛል። አሁን የአቶ በቀለ ገርባ መታበይ ልኩን ያለፈ ነው። እሳቸውን የተረጎምንበት እና አሳቸው ሆነው የተገኙት ለራሳቸው የሰጡት የተንጠራራ፤ በእጅጉም ልኩን ያለፈ ሁኔታ ግርም ይለኛል። አሁን አቶ ሌንጮ ለታ ይህን በዝምታ ውስጥ እዬቀጣቀጡት፤  እያቀጨጩትም እዬፈለሱትም ነው።

አቶ ሌንጮ ለታ የራሳቸው የሆነ ሃሳብ እና መንገድ ቢኖራቸውም አገር ከገቡ ጀምሮ የማዬው አብዛኛውን ጉዳይ ግን አዎንታዊ ነው - ለእኔ።  በእርግጥም ለግል ኢጎ ሳይሆን ለነጻነት መታገልን ዘመን እና ሂደት እንዳስተማራቸው፤ ተለምዷቸው ተዛነፉን ፍላጎት ቆንጥጦ አብነታዊ መስመር እንደኪተሉ እንዳደረጋቸው አስተውላለሁኝ። በሌላ በኩል በማዬት ውስጥ ያለው ማስተዋላቸውም ሚዘኑን የጠበቀ ውሳኔ እንዲወስኑ ረድቷቸዋል ብዬ አስባለሁኝ።

በጠ/ሚር አብይ አህመድ ያለው ብቃት እና ልቀትም ከውስጣቸው የእኔ ብለው ተቀብለውታል ብዬ አስባለሁኝ። እንዲህ ዓይነት ሊሂቃን ሲገኙ ደግሞ ተስፋ ይበረታል፤ ተስፋ አቅም ያገኛል፤ ትውልዱም አብነት ያገኛል። ግልጽነታቸው ድንብልብ ሽብልል አለመሆኑ ደግሞ መልካም ነው። አያደክሙንም። አላደከሙንም። የሚያስቀድሙትን ያስቀድማሉ የሚያስከትሉትን ያስከትላሉ። እንደ ሌሎቹ የኦሮሞ ሊሂቃን የተከደነ እና የተሰወረ ዕሳቤ የላቸውም። 

የማይመችም ቢሆን የሆነውን፤ ውስጥ የሚያስበውን ነገር ሆድ ይፍጀው ብሎ ጊዜ መግደል እና አጋጣሚ ሲያገኙ እያፈራረቁ የነበረውን  የመንፈስ ጥሪት፤ ታዕማኝነት ከማባከን በብዙ የሚሻለው የአቶ ሌንጮ ለታ መንገድ ነው።

 ስለ ውሸት እንኳን እሳቸው ግልጥ አድርገው ነው የሚናገሩት። 
በወቅቱ መሆን ስላለበት ፓለቲካ እንዲህ እና እንዲያ ስለሆነ ይላሉ በተረፈ ባለክንፍ መላዕክ ስላልሆኑ በሁሉም ነገር መስማማት አይጠበቅባቸውም። መሳሳታቸውም ሰውኛ ነው። ቁም ነገሩ የልብን ሲያገኙ ልብን ለመሸለም መሰናዳት መቁረጥ መወሰን በዛም ለመኖር ማሰብ ግን ትልቅንት ነው። ቅንነት ነው። 

የጹሑፌ መነሻ ነው ሊንኩ ከሥር ለጥፌወለሁ ተያያዡንም።  … እኔ እንደምለው እሳቸውም ሙሉዕ ሥነ - ምግባሩን የፓርቲ ያሟላ የፖለቲካ ፓርቲ እንደሌለም በአጽህኖት ገልጸዋል። በዚህም የልቤን ነው የገለጹልን። ፓርቲ እንዲህ የተረብ ድርጅት አይደለምና። የገበያ ውሎ ነበር እኔ ስል የነበርኩት። በወጀብ የሚመራ፤ በንፋስ ሃይል የሚታዘዝ ነው ስል የነበረው። ደንብ በፓርቲ ህይወት ውስጥ የነፍስ ያህል ሰነድ መሆኑ እራሱ የፓርቲው መሰረታዊ ሰነድ መሆኑን የማያውቅ አባል የፓርቲ አባል ለማለት መሬት ክብ አይደለችም የማለት የ አምክንዮ ግድፈት ነበር እኔ ሳዬው የነበረው። ላጥ ያለም ገደል ነው።

የፓርቲ ደጋፊ እና የፓርቲ አባል መኖር በፍጹም የማይገናኙ ፖለቲካው ፍልስፍናዎች ናቸው። የሆነ ሆኖ በዚህ ሊንክ ውስጥ ከ2.40 እስከ ለ3.59 የኦሮሞ ዴሞክራሲ ግንባር ሊሂቃኑ ለውጡ እንዲቀጥል ማገዝ ላይ እንደሚሠሩ በኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ለውጥ ታይቶ አይታዋቅም ባይ መሆነቸውን ይነግረናል። ግንባራቸውን በሥርዓት ወደ ተደራጀ ፓርቲነት ለመለወጥ ደግሞ ሂደት እንጂ ጥድፊያም ችኮላም እንደማያስፈልግ ነው በአጽህኖት የገለጹት።

አዎን የፖለቲካ ድርጅት ፓርቲ ስንቅ እና ትጥቁ ዲስፕሊን ነው ያን አምጦ ወልዶ የቆረጠ አባላት ያሉት ጠንካራ ፓርቲ ለመፍጠር እንደ ጓድ ገ/መድህን በርጋ ዓይነት ልባም ሰው፤ ልምዱ ተመክሮው እርጋታው ያለው ያስፈልጋል። ፓርቲ የሰከነ ደልዳ ሙርጥን ይፈልጋል፤ ረጅም ጊዜ መቀመጥ፤ ረጅም ጊዜ ማሰብ ያስፈልጋል። ሰውን በህሊና የማበጀት ተግባር ነውና። የእኔ አለቆች እኔንም ጨምረው ቢሮ ነበር የምናድረው። በፓርቲ ህይወት ውስጥ አለቀ የሚባል ሥራ የለም። እርማቱ ራሱ ጭንቅላት ነው የሚበጠብጠው።

ፓርቲ የመንፈስ አደብን ይሻል፤ ፓርቲ ስልቹዎችን ወይንም ሰነፎች ወይንም አቋራጭ መንገድ ፈላጊዎችን ሳይሆን ቀልቡን የሚገዛው ሰርተው የማይደክሙ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ አቅም ያላቸውን የረጉ፤ ውስጣቸው የተደራጀውን፤ አካበቢያቸው የሥራ ቦታቸው ዝርክረክ ያለሆኑትን፤ የማስተዋል አውራዎችን ይሻል። 

አንድ ጠንካራ ፓርቲ የግርግርግ የገብያ ውሎ አይደለም። ፓርቲ የህሊና ስክነት በበቃ የሃሳብ ልቅና አቅም የሚገናባ ጽኑ ድርጅት ነው። አዳኝም!አለን ማለት ሳይሆን አለን ብሎ ለማሰብ ራሱ የጊዜ አቅምን ይጠይቃል።

ለዚህ ነው እኔ ሸግግር መንግሥት አስፈላጊነትን እማላምንበት፤ ለዚህ
 ነው እኔ የተጽዕኖ ፈጣሪ አንድነት መንግሥትን ሽል እማላምንበት። አቅሙ የለም። ለመሸመትም ፈቃዱ የለም። የነበረው ስህተት ከተደገመ ለመማርም ፈቃዱ የለም ማለት ነው። ለመማር ፈቃዱ ከሌላ መሪነት ተወዴት ይገኛል? መና ከሰማይ ካለወረደ በስተቀር።

 የሆነ ሆኖ እዮር የሚመሰገነው የለማው መንፈስ በቆረጣ ገብተው ብሎሆቹ በቃ አዬር ላይ ተንሳፈን የንፋስ ሰረገላ ባለሟሎች ሆነን ባክነን እንዳንቀር ህልም እልም እደረገውታል። እኛም ተመስገንን አዘውትረናል። ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ስለገለማን። የተቆረ የኩሬ ውሃ ድግምትም ስለሰለቸን። 

#EBC ኢቲቪ 57 ምሽት 1 ሰዓት አማርኛ ዜና. . . ህዳር 17 ቀን 2011 .

 

በምለስት ይህም ቢቃኝ አይከፋም ባይም ነኝ።

http://www.tzta.ca/2017/10/25/%E1%88%8C%E1%8A%95%E1%8C%AE-%E1%88%88%E1%89%B3

ሌንጮ ለታ ከዶ/ ዲማ ነገዎ ጋር ካርቱም ለምን እንደሄዱ ተናገሩ | / ብርሃኑ ነጋ የኦሮሞ ቄሮዎችን ትግል አደነቁ

ህወሃት ሞራላዊ ልዕልናን አዳክሟል፤ መልሰን መገንባት እና ማምጣት አለብንብርሃኑ ነጋየኢትዮጵያ ሁኔታ ስጋቴ ነውሊንጮ ለታ

ሌንጮ ለታ አስጠነቀቁ


ውዶቼ ክብረቶቼ የጹሑፌ ታዳሚዎች እነኝህ ልምዶች ቀላል ተቋም አልነበሩም። ውስጥ ለውስጥ መገማገምን፤ ውስጥ ለውስጥ መተያዬትን፤ ውስጥ ለውስጥ አቅምን መተዋወቅን ዕድል የሰጡ ይመስለኛል። 


ለዚህም ነው አሁን ለተገኘው ለውጥ ኦዴግ የተለዬ አክብሮት እና የተለዬ ዕውቅና ለመስጠት ሲጀመር ጀምሮ ድፍረት የኖረው ብዬ አስባለሁኝ። 


ዕውነት ለመናገር በዚህ ውስጥ ያዬሁት አቅም ተመክሮን፤ ልምድን ምን ያህል ሥራ ላይ ለማዋል እንደተቻለ ነው። መኢሶንም እንዲህ ዓይነት ጸዓዳ ቅን መንፈስ ነው ያለው። ጥርት ያለ አቋም እና ውሳኔም ነው ያለው ለዚህ አዲስ የለውጥ መባቻ መሰንበቻነት - መ ኢሶን እንደ ኦዴግ።

  


ተመክሮ ለመከረው ክብር ይገባዋል!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።