ልጥፎች

ከጁላይ 9, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የቃሉ ጌታ አሜኑ እንዲህ ነው!

ምስል
እልልታው በስልክ ናፈቀኝ! ከሥርጉተ ሥላሴ 09.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዚና።) „እንሆ ይህን ሁሉ ዓይኔ አዬች፤" ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለች።“ (መዝሙር ምእራፍ ፲፫ ቁጥር ፩) ·         አ ዲስ ዜና ለቅኖች … ይሄውና የእኛ የአሮን በትር በዬሄደበት ሁሉ ለምለም ነው። በዚህች ቅጽፈት የሰልክ አገልግሎት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አበሠረ። ቃል ብቻውን ምንም አይሠራም ሲሉ የነበሩት ሁሉ እንጥሽት ውሃቸው ፍስስ ይላል አሁን። ኢትዮጵያ ውስጥ ከብርሃን የቀደሙ ተግባራት በታምራዊ ምትሃት በሚመሰል አኳሆን እዬተከወነ ነው። ተመስገን የዚህ ዘመን ታዳሚ ፈጣሪዬ ስላደረከኝ። አሹልከህም ሪሞርኬው ስላለደረከኝ።  ውዶቼ ቅኖቹ ... እንዴት በሞባይል እና በቤት ስልክ እንደሚገባ ደግሞ ምርኩዙን ተከትሎ የበለጠ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል … ·       ም ርኩዝ።   https://www.youtube.com/watch?v=1kXNrttrCSA Ethiopia: [ ሰበር ዜና ] ከኢትዮጵያ ኤርትራ በቀጥታ ስልክ መደወል ተፈቀደ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ዓራት ዓይማናው መንገዳችን ነው! ቅኖቹ የኔውቹ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ። 

ሽኝት በቅኔ እትብታዊነት ነባቢታዊነት!

ምስል
የእናት እና የልጅ መለያዬትን ያህል የነበረው ተመስጧዊ ሽኝት በጥሞና! ሃሌ ሉያ። "ነፍሴ ሆይ እግዚአብሄርን አመስግኚ።" (መዝሙር ምዕራፍ ፩፵፭ ቊጥር ፩) ከሥርጉተ ሥላሴ 09.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ·        መነ ሻ። https://www.youtube.com/watch?v=8sbjgAy5t1s&feature=share „Ethiopia: የጠ / ሚ አብይ የደመቀ የሽኝት ፕሮግራም ከአስመራ“ ድመቀቱ አይደለም እኔን የመሰጠኝ፤ መለዬት እንዲህ መፈራቱ። ሽብርቅ ለሆኑ ዲኳዊ ጉዳዮች እንብዛም ነኝ። አብሶ ይህ የሚሊዮኖች የነፍስ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ጥሞናም፤ ተመሰጦም ያስፈልገዋል። እንዲያውም አቅም ያላቸው ይህን ስመጥር ቅኒያዊ ትልም በጸሎት ቢደግፉት ጥሩ ነው። እንዲያውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና የኤርትራው የወል የ7 ቀን የሱባኤ ሁኔታ ቢኖራቸው፤ እስልምናም፤ ካቶሊክም፤ ፕሮቴስታንም በወል ይህን የሰላም ጥረት በጸሎት፤ በሰጊድ፤ በሱባኤ፤ በድዋ አጥር ቅጥር ቢሆኑለት ምኞቴ ነው። ቢያንስ በግል ሁላችንም ማድረግ እንችላልን። የባከነው የትውልድ ዘመን ማክተም አለበት። ይበቃናል። ለእኔ የመንፈሴ ጉዳይ መለያየቱ እንዲህ ጭንቅ መሆኑ ነው። እያንዳንዷ ሰከንድ የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ መንፈስ ዕዝነ ህሊናቸው ከኢትዮጵያ አዬር መንገድ ላይ ተተክሎ ነበር በተመስጦ እና በጥሞና። ያ ነው እኔን መንፈሴን ሁለመናዬን የገዛው። ቅንነት ነጥሮ የወጣበት፤ ንጽህና እና አሳቢነት ፈልቆ የታዬበት ድንቅ ገጠመኝ። ያዝልቀው እንጂ አያያዙ የእናት እና የልጅ ያህል የጠራ የፍቅር ጥሪኝ አለበት። ተመስገን! ·    ...

መቼነው ወደ እኛ የምትመጪው እትጌ ትግራይ?

ምስል
ይብላኝልሽ ትግራይ። „አቤቱ በአንተ ታመኛለሁና ጠብቀኝ።“ (መዝመሩ ዳዊት ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩ ) ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ  09.07.2018 (ከጭምቷ ሲወዘርላንድ) ·         መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=6yww4Az7IdY&t=0s&list=LLNUkM6s0cFeCBEsZNkZIp0g&index=4 Must Watch !!! Amazing Story on JTV Min Addis ·         ጠ ብታ አሁን እርሰ ጉዳይ ትግራይ ስትሆን የሚከፋችሁ ልትኖሩ ትችላላችሁ፤ ግን የግድ ነው። እኔም ፈልጌው፤ ወድጄው አይደለም። ለነገሩ እነሱም  በአንድም በሌላም የትግራይ ህዝብ ማለት የኛ ድርጅት ማለት ነው ይላሉ። አመክንዮውም የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሠረቱም የትግራይ ልጆች ነው። ያገዟቸው፤ ያበረታቶቸው እርሱ ህዝቡ ነው። ስንቅና ትጥቅ የሆናቸው እነሱው ናቸው። ሌሎች ተፎካካሪ ነን ባዮችም በትግራይ ሥም የተደራጁትም ያው የትግራይ ልጆች ናቸው።  ስለዚህ ከዚህ ዕውነት ውጪ ሊሆን አይቻልም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብለህ ከትግራይ ውጪ ሰማይ ላይ የተነሳፈፈ መንፈስ ነው ማለት አይቻልም። እኔ እንዲያውም አጋጣሚው ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ጀምሮ ትግራይን የመርሳት ሁኔታ ይፈጠራል ስል ጭራሽ የተባባሩት ድምጽ ሆነው ነው ያረፉት ተፎካካሪ ነን የሚሉትም መደመሩ ከጭካኔ እና ከአረመኔያዊነት ጋር ሆኗል። ያም መብት ስለሆነ ምንም ባልልም ትግራይን አታንሱ ስለሚለው ግን መነሻውም መድረሻውም መናህሪያውም ይሄው መሬት ስለሆነ ...