የቃሉ ጌታ አሜኑ እንዲህ ነው!
እልልታው በስልክ ናፈቀኝ!
ከሥርጉተ ሥላሴ
09.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዚና።)
„እንሆ ይህን ሁሉ ዓይኔ አዬች፤"
ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለች።“
(መዝሙር ምእራፍ ፲፫ ቁጥር ፩)
- · አዲስ ዜና ለቅኖች …
ይሄውና የእኛ የአሮን በትር በዬሄደበት ሁሉ ለምለም ነው።
በዚህች ቅጽፈት የሰልክ አገልግሎት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መጀመሩን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አበሠረ።
ቃል ብቻውን ምንም አይሠራም ሲሉ የነበሩት ሁሉ እንጥሽት ውሃቸው ፍስስ ይላል አሁን።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከብርሃን የቀደሙ ተግባራት በታምራዊ ምትሃት በሚመሰል አኳሆን እዬተከወነ ነው። ተመስገን
የዚህ ዘመን ታዳሚ ፈጣሪዬ ስላደረከኝ። አሹልከህም ሪሞርኬው ስላለደረከኝ።
ውዶቼ ቅኖቹ ... እንዴት በሞባይል እና በቤት ስልክ እንደሚገባ ደግሞ
ምርኩዙን ተከትሎ የበለጠ ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል …
- · ምርኩዝ።
Ethiopia: [ሰበር ዜና ]ከኢትዮጵያ ኤርትራ በቀጥታ ስልክ መደወል ተፈቀደ
„ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ዓራት ዓይማናው መንገዳችን ነው!
ቅኖቹ የኔውቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ