ጦርነት ህግ የለውም፤ ጦርነት ርህርሄ ያልፈጠረለት የክስረት ክስተት ነው።
ጦርነት ህግአልቦሽ ነው! „የማላዬውን ነገር አንተ አስተምረኝ፤“ መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፴፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.01.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። „ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ የሚል የአቶ ዳውድ ኢብሳ “ መግለጫን አዳመጥኩት - ከልቤ ሆኜ። በኦዴፓ እና በኦነግ መሃል ያለው ጋብቻም ይሁን ፍቺ በውነቱ ይ ኼ ነው፤ ያ ኛው ነው ለማለት ይቸግራል። ለሰሚውም ለፈራጁም ግራ ነው ። ግራ የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን መሰከረም 5 እና ጦሱን፤ ቡራዩንና እና ሰቀቀኑን ስላዳመጥን ከባድ ነው ይህን ይኼነው ለማለት። ማን ምን እንደሆነ አሁንም መወ ሰ ንም መወ ገ ንም ይከብዳል። ሰርገኛ ጤፍ የሆነ ነገር ነው ። ማን የዬትኛው ድርጅት ደጋፊ እንደሆን በቅጡ አይ ታ ወቅም። የትኛው ኦዴፓ የትኛው ኦነጋውያን እንደሆነ አንጥሮ ማውጣት መቼውንም የሚቻል አይደለም። ለውጡ እና ተጠቃሚው የኦሮሞ ማህበረስብ ገና ልብ ለልብ አልተገናኙምና። የሆነ ሆኖ ከሆነ፤ የሆነውን በሆነው ነገር በትክክል መንግሥት መግለጽ ይጠ በ ቅበታል። አድሮ የሚገኝ ነገር። የፈለገ ይሆን የሆነውን እንቅጩን መናገር የተገባ ነው። አብሶ ለመንግሥት ታማኝነት ወሳኝ ስለሆነ። አድርገዋል የሚባለው ነገር አለ። መንግሥት ደግሞ አላደረኩም እያለ ነው። ቆይቶ ዕውነቱ ከተገኜ አብሶ መንግሥት አላደርኩም ባለው ላይ አድርጎ ከተገኜ ጥሩ አይሁንም። መታመንን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሊሂቃኑ ት/ቤት ገብተው መማር ያለባቸው ይመስለኛል። ስለምን? የወል ችግራቸው ስለሆነ። በመንፈስ አቅም ማፍራት እኮ ከመታደል በላይ ...