ልጥፎች

ከጁን 5, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ቃሬዛ ላይ ነው። (የወግ ገበታ 05.06.2019)

ምስል

በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  በ መሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።   ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱“ ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie 05.06.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። በ መሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። ውስጥህን እዬበወዘ ውስጥነት ሰጠሁኽ ምን አልባት ገና ፅንስ ላይ በእናታቸው ማህጸን ላሉት ላይገለጥ ይችል ይሆናል። ሰ ው ለሆነ ሁሉ ግን ይህ የአለመኖር ዕጣ ፈንታ ወይንም እያሉ ቀፎ ለመሆን መፍቀድ ከጽንስነት የማይሻል ተፈጥሮ ነው ላርባ ላይ ለላ ቢገልጹት መሃንዲሶቹ መልካም ነው። የ ሚገርመው እነሱ የሚያስቡት ኢትዮጵያዊ ዜጋን እንደ ፑፓ ነው። ድፍረት ነው ይህ በራሱ። በግርዶሽ ትዕይንት እያዛሉ የልባቸውን ይከውናሉ። ለ ሰው ልጅ አንገት ነው ወይንስ ሃብል ነው የሚያስፈልገው? ይህን ጥያቄ መመለስ ያለበት ሁሉም መሆን አለበት። 100ሚሊዮን ህዝን ላርባ ነህ ማቹሪቲ ይጎድልሃል የማለትም ያህል ነው ዴሞግራፊ ለእኔ። ዴሞግራፊ ፍልስፍና እያራመድክ በምርጫ ተወዳድረህ ታሸንፋለህ ብሎ ነገር ከቧልትም ያለፈ ሃጢያትም ነው። ዛ ሬ የማከብራትን ብዙም ፈተና የተቀበልኩባትን የክብርት ወ/ት ዳኛ ብርቱካን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩት። ቃለ ምልልሱ ራሱ የተደረገበት ቦታ   የኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ነው። የ ጠ/ሚሩ ቢሮ በሚሰጠው አመራር የሚሰጥ ሁለተኛ የከፍተኛ ዜጎች ቃለ ምልልስ መሆኑ ነው። ይህ የቤተመንግሥት ደረጃ ለOBN መሰጠቱንም በይበልጥ ያረጋገጥኩበት አመክንዮ