በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር።
እንኳን ደህና መጡልኝ
በመሆን ውስጥ
የሌለ ተስፋ ባይፈጠር
ይሻለው ነበር።
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤
እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።
ምሳሌ
፲፮ ቁጥር ፱“
ከሥርጉተ ሥላሴ
Sergute Selassie
05.06.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።
በመሆን ውስጥ የሌለ ተስፋ ባይፈጠር ይሻለው ነበር። ውስጥህን እዬበወዘ ውስጥነት ሰጠሁኽ ምን አልባት ገና ፅንስ ላይ በእናታቸው ማህጸን ላሉት ላይገለጥ ይችል ይሆናል።
ሰው ለሆነ ሁሉ ግን ይህ የአለመኖር ዕጣ ፈንታ ወይንም እያሉ ቀፎ ለመሆን መፍቀድ ከጽንስነት የማይሻል ተፈጥሮ ነው ላርባ ላይ ለላ ቢገልጹት መሃንዲሶቹ መልካም ነው።
የሚገርመው እነሱ የሚያስቡት ኢትዮጵያዊ ዜጋን እንደ ፑፓ
ነው። ድፍረት ነው ይህ በራሱ። በግርዶሽ ትዕይንት እያዛሉ የልባቸውን ይከውናሉ።
ለሰው ልጅ አንገት ነው ወይንስ ሃብል ነው የሚያስፈልገው? ይህን ጥያቄ መመለስ ያለበት ሁሉም መሆን አለበት።
100ሚሊዮን ህዝን ላርባ ነህ ማቹሪቲ ይጎድልሃል የማለትም
ያህል ነው ዴሞግራፊ ለእኔ። ዴሞግራፊ ፍልስፍና እያራመድክ በምርጫ ተወዳድረህ ታሸንፋለህ ብሎ ነገር ከቧልትም ያለፈ ሃጢያትም ነው።
ዛሬ የማከብራትን ብዙም ፈተና የተቀበልኩባትን የክብርት ወ/ት ዳኛ ብርቱካን ቃለ
ምልልስ አዳመጥኩት። ቃለ ምልልሱ ራሱ የተደረገበት ቦታ የኦሮሞ
ሚዲያ ኔት ወርክ ነው።
የጠ/ሚሩ ቢሮ በሚሰጠው አመራር የሚሰጥ ሁለተኛ የከፍተኛ ዜጎች ቃለ ምልልስ መሆኑ
ነው። ይህ የቤተመንግሥት ደረጃ ለOBN መሰጠቱንም በይበልጥ ያረጋገጥኩበት አመክንዮ ነበር።
ሃላፊነቱ የልተወሰነው ኦዴፓ እንዲህ በቀዶ ጥገና ሙያ ተክኖበታል። ይህ በራሱ ሌላው
የዴሞግራፊ ፍልስፍና ማሳያ ምልክት ነው። ዘመናትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ተድጦ ነው ይህ እዬተከወነ ያለው።
የሥነ - ልቦና የበላይነትም አብሮ እዬተሠራበት ያለ ጉዳይ ነው። የቤተመንግሥት ቃለ
ምልስ አድራጊ በደም ከሆነ ያው ዋልታ ላይ ሆኖ ሊከውነው ይችል ነበር። የተፈለገው ግን ይህ አይደለም።
Ethiopia
: ስለ መጪው ምርጫ 2012 ውዝግቦች በአንጀት አርስ ጥያቄዎች አፋጠጣት | ከብርቱካን ሚደቅሳ ጋር ቃለ ምልልስ | Birtukan Mideksa |
ወደ ቀደመው ስመለስ ዴሞግራፊ ሰውን ውስጡን አውልቆ እንደ ገና አዲስ ሰብዕና መሞላት ነው ቻርጅ ማድረግ። ወደ ሌላ ሰብዕና ትራንስፈር ማድረግ
ነው።
መጀመሪያ በዚህ ፍልስፍና አራማጆች እና ሰው ሆነ በተፈጠረው ኢትዮጵያዊ ዜጋ አማካይነት አደብ የገዛ ይፋዊ ውይይት ያስፈልጋል።
እንዲህ በለብ ለብ፤ እንዲህ በግጥምጥሞሽ የሚሆን አይደለም። ድፈረት እና ጀግንነት ይጠይቃል። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም
በዚህ ጉዳይ ግልጥ አቋም ሊይዝ የሚችልበት ሁኔታ መታቀድም ይኖርበታል።
ከዚህ ነው ማንኛውም ችግር የሚፈጠረው፤ በቀጣይም ቧ
ብሎ
የተከፈተው
የኢትዮጵያውያን ዜጎች ህብራዊነት ዕጣ ፈንታ ተስፋ ለቀብር የተሰናዳ ስለመሆኑ ማሰብ በጥልቀት ይጠይቃል።
ኢትዮጵያዊው ዜጋው ሲፈጠር በፈጣሪ /በአላህ / ፈቃድ ነው። ይህ ለመቀዬር የተነሳ ህጋዊ እውቅና ያለው የመንግሥት አካል እያለ ስሌላ መኖር ማሰብ መቼም ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ ዕብንነት ይመሰለኛል። ለዛውም
ስለምርጫ?
ሌሎች ጉዳዮች ማባጨያ እና ግርዶሽ ለመፍጠር የታለሙ ገደሎች ናቸው። ስለዚህ በዕውነት ላይ ሆኖ ሰብዕናን ሊቀማ፣ ሰው ሆኖ መፈጠርን በልቶ አዲስ ፑፓ አድርጎ ለመስራት የታቀደው ስትራቴጅ ንጹህ መድሎ (pure Discrimination) ላይ የጠራ አቋም ይኑር።
በስርክራኪው፤ በንፋሱ፤ በቀጨር መጨሩ ከመታመሳችን በፊት። ሰውነትህ እዬውለቀ እንደገና ልትበጅ ታቅዶ እዬተከወነ ባለው ጉዳይ ላይ ከልብ የገባ መነቃቃት ሊኖር ይገባል።
ይህን ዕሳቤ ባነሰ ግምት በ5 ዓመት ውስጥ ምን ያህል ይህ ሰይጣናዊ ትልም ወደ ተግባር ተሻግሮ አዲስ የማንነት ቅዬራ
ናሙና ኢትዮጵያ ልትሆን እንደምትችል ማሰብ ይገባል።
የዓለም ጦርነት መንስኤና ውድመት መሰረታዊ ቅዠትም ይህ ነበር። ስለሆነም ይህን ለማስቆም መትጋት ይገባል። ምልክት
አይደለም እዬታዬ ያለው። ወፍራም ድርጊት ነው። ተግባር ነው እዬታዬ ያለው።
ውቡን ቅይጡን Heterogeneous የማንነት ውበትን ወደ ወጥ Homogeneous ማንነት ለመቀዬር ነው ተጋድሎ እዬተደረገ ያለው።
ይህ በመንግሥት በቂ ድጋፍ እዬተሠራበት በሌላ በኩል ደግሞ አህዳዊ መንግሥት ሊያመጡብን ነው ጩኽቱም እዛው ቤት ነው
ያለው።
እነሱ እዬተገበሩት ያለውን ግን ያስተዋለው የለም። ለዚህ አዲስ አበባ፤ ኬሚሴን፤ እና ጌዲዮን መሰረታዊ የምርምር
ማዕከሎች ናቸው። በተለያዩ ሁኔታዎች እርምጃዎች እዬተወሰዱ በምስቅልቅል የፖለቲካ ሁኔታ ላለችው ኢትዮጵያ
በሌላ በኩል ደግሞ ስለ ዴሞክራሲ እና አሳታፊ ምርጫ ሲወጋ ይደመጣል።
መጀመሪያ የዲሞግራፊ ንድፍ ላይ አውራው ፓርቲ ኦዴፓ የጀመረውን ሰውን አፍርሶ የመስራት ቅዠት ማስቆም ይጠበቅብናል። ስለ ሰው፤ ስለተፈጥሮ፤ ስለ ሃይማኖት ግድ የሚለው ሁሉ።
በዚህ ዙሪያ ነው ለሰብዕዊ መብት የሚተጋው
ሁሉ መሞገት ያለበት። ሚዲያው ሁሉ መሥራት ያለበትም በዚህ መሰረታዊ ሰውን አፍርሶ ለመስራት በታቀደው ብቻ ሳይሆን ድርጊት ላይ
እዬዋለ ባለው ኢ - ሰብዕዊ ኢ - ተፈጥሯዊ ጉዳይ ላይ ከልብ የመሆነ ተጋድሎ ማድረግ ይጠበቅብናል።
ኦዴፓ አልፈን ኦፌኮን ስናይም ሌላ
ዘንዶ ደግሞ አለ። በዚህ ዙሪያ ብዙውን ነገር በቅኔ ሲዎርፉ
የሚታዩት ፕ/ መራራ ጉዲና በራሳቸው ድርጅት ውስጥ በበቀለው አዲስ የነቀርሳ
ሽል ዘፍጥረትን ለመደመስስ፤ የባቢሎን ግንብ ቀያሹን በምክትላቸው የተነደፈው ስልትን ሲያውግዙ ወይንም ያላቸውን የድርጅታቸውን
አቋም ሲገልጡ አይታዩም። ስለምን „የቡዳው ፖለቲካ“ ማህበርተኛ
እሳቸውም ስለሆኑ።
ዕውነት ፈላጊ ሰው እውነት ካለበት
ቦታ ነው መቆም ያለበት። እውነት ለዬዘመኑ መራ እንድትኖር የሚያደርገውም ይህ እውነት ላይ መቆም ስለሚሳነው ነው የኢትዮጵያ እፉኝቱ
ፖለቲካ።
ሌላው ቀርቶ ፕ/ መራራ ጉዲና ስለ
ብሄራዊነት የሚጨንቀቸው ቢሆን ኖሮ በዴሞግራፊ ፍልስፍና የተከወነውን
አውግዘው ቀድመው መነሳት የነበረባቸው እሳቸው ነበሩ ቋንቋው የአፍ መፍቻ ስለሆነ። ግን አልሆነም።
ስለዚህ አላዛሯ ኢትዮጵያ ሰው ፈርሶ
መሰራት ብቻ ሳይሆን ፈርሶ ከሚሰራውም ጋር ጋብቻ ንግድ ማህበራዊ ኑሮ በታገደበት ትልም ላይ ተቁሞ ተስፋን መጠበቅ ጸሐይ ተለውጣ
ጨርቃ ትሆናለች የማለት ያህል ነው ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት፤ ፈተናን
አሸንፎ፤
የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይስደዳል።
ፍቅርም ሲያልቅ ትእግስት ይሰደዳል።
ኑሩልኝ የኔዎቹ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ