ሰውነት ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ እንጂ ባዕዷ አይደለም።
ሰውነት ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ እንጂ ባዕዷ አይደለም። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከቅንነት ጋር ተዋውቆ አያውቅም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰውኛም አይደለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተፈጥሯዊም አይደለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጭካኔን መርሁ ያደረገ ነው። ስለዚህ ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ #ተፈጥሯዊነት ነው። ተፈጥሯዊነቷ ትርታዋ ነው። ኢትዮጵያን እያመሳት ያለ ፖለቲካዋ ነው። እግዚአብሄር አምላክ ተፈጥሯዋን ዕውቅና የሚሰጥ፤ አክብሮ ሊያስከብራት የሚችል መንፈስ በምድሯ ይፍጠር። አሜን። ለእሱ የሚሳነው የለም እና። ጀርመን አንደኛውንም፤ ሁለተኛውንም የዓለም ጦርነት ተሳትፎው የጎላ ነበር። ዛሬ ግን በምድሩም በሰማዩም ሥልጣኔ አንቱ ነው። ፈጣን እና ታታሪ ህዝቧ መሪ ስላገኜ። ጀርመን ዛሬ ከኃያሉ ጎን ተሰልፋል። ይህ የሆነው #በመሪወች #አቅም እና #ትጋት ነው። ከልዩነት አንድነትን የመረጠው ጠንካራው ህዝቧ እና የመሪወቿ #ጥበብ ለሰው ተርፎ ማደር ችለዋል። በጀርመን #ጥበብ እና #ጥበበኛ #አይታሠርም ። ብልህ ሰው ከአለበት ተፈልጎ ልምዱን፦ ተመክሮውን እንዲያጋራ ይደረጋል። #ይሸለማል ። ዕውቅና ያገኛል። ታታሪው ህዝቡ ጀርመን ይቅደም ነው። እግር ኳስ #ጨዋታ ብቻ አይምሰላችሁ። ታላቅ ብሄራዊ የትውልድ መገንቢያ ልዩ መንፈስ ነው ለጀርመኖች። ትርታቸው ነው።በእያንዳንዱ የተጫዋቾቻቸው ንቅናቄ አትኩሮታቸው #የድርሳን ያህል ነው። ይጥራሉ ያሳካሉ። ብርታታቸው ከጥረታቸው ጋር የተዋህደ ነው። በሁሉም ዘርፍ ንቁ እና ብቁ። ቀልጣፋ እና ስኬታማ። ሥልጡን እና መኖርን የተጠ...