#የተረሱት። ለምርጫ

 

#የተረሱት። ለምርጫ ማስፈራሪያ ከምርጫው በፊት ሰበብ ተፈልጎ ቀድም ብለው የታሠሩ ምንዱባን።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 3 people
 
እንዴት አደራችሁ? ከእኛ ይዘንባል፤ ይዳምናል። የአዬር ፀባዩ ባህሬው ወርኃ #ሚያዚያን ሆኗል። ሚያዚያ እንደልቡ ነው። መዝነቡ ግን ፀጋ ነውና እቀበለዋለሁ። ተመስግን። ምን አልባት ለገበሬወች አዝመራንካልጎዳ።
 
እነኝህ የምታዮዋቸው የአርቲስት ሃጫሉ ግድያን ተከትሎ ሻሸመኔ፤ አርሲ ነገሌ፤ ዝዋይ፤ ሽዋ ሮቢት #አማራወች የገነቧቸው ተቋማት፤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች #ዞግ #ሳይለይ ያደሯቾቸው ተቋማት ሲነዱ፤ በግፍ ንፁኃን በጅምላ በተዘጋጄ ኃይል ሲረሸን አዲስ አበባም ታቅዶለት ነበር። ይህን በአንድም በሌላም አድምጠናል። ዒላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን በማንደድ #ለመበቀል የታሰበ ነበር። ብጥብጡ ሲነሳም ከፍ ያለ #ቀውስ ታቅዶም ነበር። 
 
ዕቅዱን በጥዋቱ #ያከሸፋት አዲስ አበቤ አሁንም እስር ላይ ናቸው። #ማገዶ። ሃሳቡ #ምርጫውን #ፀጥ ባለ ሁኔታ #በፍርኃት #ጫና ማሳካት ነበር። ፈፅመውታል።
ያን ጊዜ የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ በማሳበብ ፖለቲከኞችን ግርግሩን ተጠቅመው አሰሩ።
 
 የተዋህዶ ልጆችን በገፍ ለካቴና ሰጡ። ፖለቲከኞች ተፈተዋል፦ በዚህ ምክንያት የታሠሩት። እነዚህ ምስኪኖች ግን #ተጽዕኖ #ፈጣሪም አይደሉም። #ተዕዕኖ #ፈጣሪ #ቤተሰብም የላቸውም። #በሥም አናውቃቸውም። ከሦስት ዓመት በላይ እስር ቤት ይገኛሉ። ምን አልባት የታመሙም ሊኖሩ ይችላሉ። 
 
ቤተሰቦቻቸው በምን ሁኔታ እንደሚገኙም አናውቅም። ጠበቃ ይኑራቸው // አይኑራቸው አይታወቅም። #አዲስ #አበባን #ከጥፋት #ክሮ የታደጓት አስተዋሽ ያጡ። ዘለግ ሲልም #የተረሱ
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
26/06/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።