#ነገን መሥራት ይቻላል
ለትውልድ እያንዳንዱ ሰከንድ ዕሴት አለው። #ዕሴቱ እንዳይባክን ትውልድ #ጊዜውን ማደራጀት ይኖርበታል። ጊዜ ማደራጀት ከተቻለ ሕይወትን በዕቅድ መምራት ይቻላል። ሕይወትን በእቅድ መምራት ከተቻለ በዛሬ ውስጥ #ነገን መሥራት ይቻላል። በነገ #መሠራት ውስጥም ከነገ ወዲያ #መሠረቱ ይጣላል። ዬትውልድ ተከታታይነት ቁምነገር የሚገነባው በራስ ውስጥ በሚሰራ የተደራጀ ተግባር ነው። በራስ ውስጥ የተደራጀ ተግባር ከኖረ ራስን #ለማድመጥ በቂ ጊዜ ይኖራል። ያ በቂ ጊዜ ሩቅ ይታሰብበታል። ታስቦም ይተገበርበታል። ያ ተግባር ሲዋህድ የማህበረሰብ ይሆናል። ሁሉም እራሱን #ያጥና እያልኩ ነው። ትውልድ የቅልቅሎሽ ድራማ አይደለምና። ሥርጉትሻ28/06/024
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ