ሰውነት ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ እንጂ ባዕዷ አይደለም።
ሰውነት ለኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ እንጂ ባዕዷ አይደለም።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከቅንነት ጋር ተዋውቆ አያውቅም።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰውኛም አይደለም።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ተፈጥሯዊም አይደለም።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጭካኔን መርሁ ያደረገ ነው። ስለዚህ ዘላቂ መፍትሄ ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ ተፈጥሯዋ #ተፈጥሯዊነት ነው። ተፈጥሯዊነቷ ትርታዋ ነው። ኢትዮጵያን እያመሳት ያለ ፖለቲካዋ ነው። እግዚአብሄር አምላክ ተፈጥሯዋን ዕውቅና የሚሰጥ፤ አክብሮ ሊያስከብራት የሚችል መንፈስ በምድሯ ይፍጠር። አሜን።
ለእሱ የሚሳነው የለም እና። ጀርመን አንደኛውንም፤ ሁለተኛውንም የዓለም ጦርነት ተሳትፎው የጎላ ነበር። ዛሬ ግን በምድሩም በሰማዩም ሥልጣኔ አንቱ ነው። ፈጣን እና ታታሪ ህዝቧ መሪ ስላገኜ።
ጀርመን ዛሬ ከኃያሉ ጎን ተሰልፋል። ይህ የሆነው #በመሪወች #አቅም እና #ትጋት ነው። ከልዩነት አንድነትን የመረጠው ጠንካራው ህዝቧ እና የመሪወቿ #ጥበብ ለሰው ተርፎ ማደር ችለዋል። በጀርመን #ጥበብ እና #ጥበበኛ #አይታሠርም።
ብልህ ሰው ከአለበት ተፈልጎ ልምዱን፦ ተመክሮውን እንዲያጋራ ይደረጋል። #ይሸለማል። ዕውቅና ያገኛል። ታታሪው ህዝቡ ጀርመን ይቅደም ነው። እግር ኳስ #ጨዋታ ብቻ አይምሰላችሁ።
ታላቅ ብሄራዊ የትውልድ መገንቢያ ልዩ መንፈስ ነው ለጀርመኖች። ትርታቸው ነው።በእያንዳንዱ የተጫዋቾቻቸው ንቅናቄ አትኩሮታቸው #የድርሳን ያህል ነው። ይጥራሉ ያሳካሉ። ብርታታቸው ከጥረታቸው ጋር የተዋህደ ነው።
በሁሉም ዘርፍ ንቁ እና ብቁ። ቀልጣፋ እና ስኬታማ። ሥልጡን እና መኖርን የተጠበቡ።
ኢትዮጵያ ደግ ህዝብ ሰጥቷታል። ሁሉን ቻይ። ግን ከዘመን ዘመን ለበቂ ህክምና፤ ለበቂ መጠለያ፤ ለበቂ ምግብ ያልበቃ ህዝብ ይዘው ፖለቲከኞች በዬዘመኑ #ሲፈርሱ // #ሲሰሩ ኖረዋል። ሙሉ 60 ዓመት በሶሻሊስት ርዕዮት ኢትዮጵያ ታመሰች።
ለሶሻሊዝም መሪ ያስፈልጋል። ቻይና የት ደርሳለች። መሪ ስላላት። ለዛም የሚበቃ መሪነት ይጠይቃል። #የለም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሪወች ከሊቅ እስከ ደቂቅ ራሳቸውን ገምግመው እራሳቸውን ፈቅደው #ቢያገሉ ኢትዮጵያም ትውልዱም እንዴት ባተረፋ ነበር።
ኢትዮጵያ ተፈጥሮዋ ያልሆነውን #ሶሻሊዝምን ተሸከሚ ተብላ ነው አሳሯን የምታዬው። ቀይረነዋል ቢሉም ከዛ መንፈስ ፈቅ ያለ የለም። ቂም እና በቀል የመከነበት፤ ግድያ እና እስር የማይኖርበት። ሴራ እና ተንኮል የሚደርቅበት በሆነ ነበር።
የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አይደለነም ቢሉ እንኳን ድርጊታቸው ግን እዛው ከሶሻሊዝም #ኢንትሪግ ፈቅ አይልም። በግል ህይወታቸው ኢንትሪግ የመኖራቸው አጋር የሚያደርጉ ሁሉ አሉ።
በዛ ተጠምቀዋል። "ያልታደለ" ይለዋል ጋሼ ፀጋዬ
መደጋገፍ፤ መረዳዳት፤ መደማመጥ ጣሪያ የሆነው ለዚህም ነው። ስለሆነም የእኔ ዕይታ የአደራም፤ የሽግግርም፤ የአገናኝም የሚለው መስመር ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅት ለኢትዮጵያ ልኳ ስላልሆነ፤ የማንነት ቀውስ የሌለባቸው #ወላጅ #አባትም፤ ወላጅ እናትም ያላቸው፦ በህይወት ከሌሉም ከሚታወቅ ቤተሰብ የተፈጠረ ሊሆን ይገባል። የኑሮ ደረጃ ማለቴ አይደለም።
የኢትዮጵያ ቁልፍ ፖለቲከኞች ጠቅላይ ሚኒስተሮች ሳይቀር አባታቸውን የማያውቁ፤ ሥማቸውን የቀዬሩ ስለመሆናቸው በዝርዝር አንድ ሚዲያ ላይ አዳምጬ በውነት አዘንኩላት።
የማንነት ቀውሱ ነው በበቀል እንዲህና እንዲህ የሚያደርገው።
ሌላው ቲሙ #ከዬትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ደጋፊም፤ አባልም ያልነበሩ #አጽናኝ // #አይዟችሁ ባይ ቲም ተፈጥሮ ኢትዮጵያ ለዘላለም #በተፈጥሯዊነት ቲም እንድትመራ ነው ምኞቴ።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት ታሪክ እኔ ያዬሁት የዕለት ዘጋቢነት እና የሚዲያ የፖለቲካ ተንታኝነት ነው። የሚዲያ ጌጦች ዘውዶች ናቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች።
ውዶች አይደሉም። ጊዜ ስለተረፋቸው በኢቬንት ትይንት ተዋናይነት የሥራ ዘመናቸው ይጠናቀቃል። ፖለቲካ እኮ ቁጭታ ይፈልጋል። ቁጭ ብሎ መሥራትን።
የጫጉላ ሽርሽር የካሜራ ሙሽርነት ሳይሆን የቢሮ መደበኛ ሠራተኝነትን ይጠይቃል። ቀን ብቻ አይደለም። ማትራስ ላይ እዛው እያደሩ መትጋትን ይጠይቃል። ለአንድ ቁልፍ የፖለቲካ መሪ እረፍት ምኑ ነው?
በቃት ዕንባ።
በቃት መከራ።
በቃት ዋይታ።
በቃት አንገት መድፋት።
ጠቅላላ የኢትዮጵያን የፖለቲካ አዬር የሚቀይር ሁኔታ ነው ሊፈጠር የሚገባው። ኢትዮጵያኒዚም ሞደርን ፍልስፍና ነው። ይህ በቂ ነው።
አገር በቀል ፖሊሲ በኢትዮጵንያዚም ፍልስፍና፤ አገር በቀል ዕቅድ በኢትዮጵንያዚም ፍልስፍና መንደፍ። የኢትዮጵያ ህዝብ ትጉህ ስለሆነ ተረዳድቶ በ20 ዓመት ውስጥ ኢትዮጵያን የተሻለች ማድረግ ይችላል። አቅም አለን።
ይህ ተይዞ ነው የገበርዲን፤ የከረባት፤ የሞድ፤ የግብረ ሰላም፤ የሽርሽር፤ የፓርክ፤ የሪዞልት ምረቃ አገር ምድሩን ያካለለው። ሌላውም ሰው ቢይዘው ያው ነው። ምክንያት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውቅር ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ #የኢንትሪግ #ኮንቴይነር ስለሆነ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
24/06/024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ