ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 26, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዴሞክራሲ ለምላስ ጣፋጭ ነው፤ ከማርም ይበልጣል።

ምስል
ምን እንሁን? እንዴትስ እንሁን? የትስ እንቁም? „የእግዚአብሄር አምላክ እንዲህ ይላል፣ ---- መንገዳችሁንና እና ሥራችሁን አሳምሩ፤“ ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ  ፯ ቁጥር ፫ በዚህም ሥፍራ አሳድራችሁ አለሁ“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 26.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·       እ ፍታ። ትናንት የጨለማ ቀን ነበር ለእኔ። ሌላው ወገኔ ምን ዓይነት ቀን እንዳሳለፈ አላውቅም። የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች አንደ ሥርጉተ የአቋም መግለጫ ከምለው የውሳኔ ሃሳብ ውህደት ብለው ይሻለኛል በንባብ አቅርበዋል። ከመንግሥት ሚዲያ OBN አለበት። ውሳኔ እንዳልለው የኦሮሞ ህዝብ ተወያይቶ ማጽደቅ ስላለበት ነው። አሁን እኔ በመንፈስ ኢትዮጵያም የማውቃቸውን ክ/ አገራትን ሳስብ አብሶ ነገረ ጢቾ ይመጣብኛል። ጤቾ ሥርጉተ ሥላሴ ተዛወረች ብለው ሳምንት ሙሉ ከመደበኛ ሥራቸው የቀሩት የኦሮሞ እህቶቼ ሽው ይሉኛል።  በእኔ ኦሮምኛ ጅማሮ ከትከት ብለው ይሰቁ የነበሩበትን ጉዳይ ሳስበው ውስጤ ይፈወሳል።  በዬከተሞች ስሄድ እሚያቅፉኝ ወገኖቼን ጠረን አስታውሳለሁኝ። ጢቾን ስለቅ መኪናው ሲንቀሳቀስ ያስቆሙት ይመስል ከመኪናው ጋር አብረው የሮጡ እነዛ ብርቅ ወገኖቼ ይመጡበኛል።  መዛወሬን ስነግራቸው ቢሮ ውስጥ ድብልቅልቅ ያለ ጩኸት ማሰማታቸውን ዛሬም አስበዋለሁኝ። ሰው የተረዱ እስኪመስል ድርስ ነበር የጮኽቱ። የሚገርመው ብክን ብለው እንደዛም እንደሆኑ ጥለውኝ ወደ ቤታቸው እንዴት እየከነፉ እንደሄዱ ይታዬኛል።  ስለዚህም ሁልጊዜ ወደ ጢቾ ያለትኬት እጓዛለሁኝ። ዛሬ በሃሳብ ለመጓዝ ይከብደኛል። ይፈቀድልኝ አይፈቀደልኝ አላውቅም። ልብሱም ያለውን ፎቶ ልጠቀምበት አልጠቀመብት እንዲሁ? ኤርትራ እና ኢትዮጵያ መለያዬታቸው ምን ያህል