ልጥፎች

ከጁን 8, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የባድመ ዕድምታ በሥርጉታ ዕይታ ።

ምስል
                         አይዋ አደብ ብትገኝስ ምን ይመስልሃል?                                        ከሥርጉተ ሥላሴ 07.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)                                „ልጄ ሆይ የእግዚአብሄርን ተግሣጽ አትናቅ፣ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር።“                                                     (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፩) ·          ጥገናዊ ለ ውጥ እና ፈተናው። አደብ ሲታደሉት ብቻ የሚገኝ ተፈጥሮ ነው። መልካም ስብዕና። የሆነ ለውጥ ነገር ፈልገህ የለውጥ ፍንጮች እና አቅጣጫዎች የሚያመጣቸውን ነገሮች ፈርተህ አይሆንም። አንድ ትወስዳለህ ሌላ ትሰጣለህ። አንድ ትሰጣለህ ሌላ ትቀበላለህ። አንድ ትጥላለህ ሌላ ታነሳለህ፤ በጥገናዊ ለውጥ ውስጥ ሁሉም ተጠቃሚ ሁሉም ተጎጂ አይሆንም። ተጎጂውም ተጠቃሚውም እኩል በኩል ነው። መስዋዕትነቱም እኩል ነው። ጥገናዊ ለውጥ ቡፌ አይደለም። የምትፈልገውን የምታነሳበት፤ የማትፈልገውን የምትተውበት። ከምትፈልገውም/ ከማትፈለግውም መታደም ግድ ይላል። ዴሞክራሲ የሚባለውም እኮ በድምጽ ለተወሰነው ውሳኔ ተሸናፊው የግድ ተገዢ ይሆናል። ሳያኮርፍ ደስ ብሎት ሥልጣኔው ካለ።  ለዚህ ደግሞ ተፈጥሯዊ አደብ ሲኖር ነው - ከተገኜ። ድምጽ ላልሰጠህበት፤ ሽንጥህን ገትርህ ለተሟገትክበት ሃሳብ ተሸናፊ ከሆነ ላሸነፈው መገዛት፤ በዛ ሃሳብ መመራት የግድ ይላል። በለውጥ ውስጥ መራራ ሃሞት በማር በጥብጦ መጠጣት ማለት ነው። ኮሶ በሽታ የያዘው ሰው „አሳንጋላ // እንቆቆ“ የሚባል ባህላዊ መዳህኒት ሲወስድ እያንገሸገሸው ነው። ግን ከሚያወርደው የኮሶ ትል ለመገላገል ነው ያ መራራ