ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 3, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

ምስል
  እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጣችሁልኝ። „አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኽኝ? እኔን ከማዳን ከጩኽቴ ቃል ሩቅ ነህ። አምላኬ በቀን ወደ አንተ እጣራለሁ አልመለስህልኝም፤ በሌሊት እንኳን እረፍት የለኝም።“ (መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 21 ከቁጥር 1 እስከ 3) ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 03.02.2021 · የ እኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?   አላዛሯ ኢትዮጵያ እና ልጆቿ እንዴት እዬሆኑ ይሆን አዋዋሉ አስተዳደሩ?? እንደምን እዬሆንሽ ነው እማ! የእኔ ልዕልተይ! እናንተስ ማህበረ ንጹኃና ቅኖቹ የብራናዬ ታዳሜዎች እንዴት ናችሁ? ስለጤንነታችሁ፤ ስለሰላማችሁ አስባለሁኝ። እናንተ ለእኔ የህሊናዬ ቤተ - መቅደሶች ናችሁ እና። ይህን ስላችሁ ከንቱ ውዳሴ ይመስላችሁ ይሆናል። እመኑኝ ብዬ አልሞግትም። ጥሞና ላለው ሰብዕና እኔን እኔ አድርገው የሚመሩኝ የህይወት መርሆቼን አቤቱ ጉግል፤ ፊታውራሪ ዩቱብ ቢጠዬቅ ይመልስዋል። ዛሬ መስካሪ አለን። ትናንት ምን ዛሬ ምን እንደሆን። በልጅነት የሚያውቁኝም በዛው ልክ ስለመሆኔ ያውቃሉ። እራሴን አታልዬ ለመኖር አልተፈጠርኩበትም። እምጽፈው እራሴ የሆንኩትን ነው። እኔ እኔን መሆን ከተሳነው እኔ ለእኔ በተሰጠው የነፃነት ልክ መቆም ካልቻለ እኔ እኔን ማሰናበት ይኖርበታል። ይህ ደግሞ አይፈቀድለትም። ይህ መርሄ ነው። ·       ው ሃማ ባለቀለሙ ሃሳብ? ሃሳብ ሰላም ይሻል። ሃሳብ ፍቅር ይሻል። ሃሳብ አትኩሮት ይሻል። ሃሳብ እንክብካቤ ይሻል። ሃሳብ ሰው ይሻል። ሙሉሰው። ምራቁን የዋጠ። ስለዚህም ጊዜ መስጠት - ማድመጥ - አክብሮ ማወያዬት - ማሰከን ያስፈልጋል። ማንን? የንጉሶች ንጉሥን አጤ ሃሳብን። ሃሳብ አ...