ልጥፎች
ከጁን 8, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ
“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው” {ከጸሐፊ እና ከተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ}
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
“እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎ በሰላም መጡልኝ።” “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው” ከጸሐፊ እና ከተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ እስከ 1966 ዓ / ም መጨረሻ ድረስ የመሯትና የህዝቧም እረኛ ሆነው ፥ እንደ ቀስተ ደመና ቀለማት ህብር ውበት ሁሉ፣ የተለያየ ባህል ባለቤትና ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቧን በአንድ መሶብ አሰባስበው፣ መተሳሰብ መዋለድ ህብረትና ሀገራዊ ማንነት ተዋህደውና አምረው እንዲሰርፅና እንዲኖር ያስቻሉት እኒያ መሪዎቿ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረባቸው ነበሩ። የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶችም ለእምነቱ ህግጋት ተገዢ ፈጣሪያቸውንና አማንያንን አገልጋይ ነበሩ። ፈጣሪም ከእነርሱ ጋር ነበረ። የቀደሙት የኢትዮጵያ መሪዎች በፈሪሃ እግዚአብሄር እየተመሩ የህዝባቸው መልካም እረኛ ሆነውና በሀይማኖቶችም አከባብረውና አስማምተው ህዝባቸውን አኖሩ። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር አቆሙ። ከጠላት ጠበቁ። የኢትዮጵያ ህዝብም ልበ ቅን፣ በራሱ ላይ ሊያደርጉበት የማይፈልገውን በጎረቤቱና በሌሎች ወገኖቹ ላይ የማያደርግ፣ ፈሪሃ እግዚአብሄር ያደረበት ሆኖ ተባብሮና ተሰባስቦ ኖረ። ለዘመናት የተገነባው ይህ ሀገራዊ / ኢትዮጵያዊ እሴት በዘመነ ደርግ ፈተና ገጠመው። ፈተናው ፖለቲካዊና መንፈሳዊ ነበር እንጂ ዘርን ተገን አድርጎ ሀገራዊና ኢትዮጵያዊ ማንነትን የዳጠ፣ የጨፈለቀ፣ ያዋረደና ኢትዮጵያዊነትን ...