«በሞኝ ክንድ ጉድጓድ አይለካበትም።» "የውክልና ጦርነት" አይኖርም አሉ።
«በሞኝ ክንድ ጉድጓድ አይለካበትም።» ብዙ ጊዜ ሃሳባቸውን ሲለዋውጡ ስለማያቸው ልብ የሚያስጥል ባይሆንም፣ አሁን ላለው የቀንዱ ውጥረት ግን ጠቃሚ ውሳኔ ነው። በትክክል ገብቷቸው ይህን አቋም አጽንተው ከቀጠሉበት " በሞኝ ክንድ ጉድጓድ አይለካበትም? ኢትዮጵያዊው ብሂል ዘመን ሰጠው ማለት እችላለሁኝ። አንድ የአገር መሪ፣ ወይንም የአንድ ንቅናቄ መሪ በዓቱን ከጦር ሜዳነት መከላከል ብልህነት ነው። ይህ ዜና ከጸና ለኢትዮጵያ የምሥራች፣ ለግብጽ ግን መርዶ ይመስለኛል። የግብጽ የፖለቲካ ሊቃናት ኮተት እያሉ የሚድሁበት መንጠላጠያ ፍላጎታቸው አንኳሩ ኢትዮጵያን መፎካከር፣ የአፍሪካ መሪ ሆኖ ለመውጣት ማለም ነው። አባይ ምክንያታዊ የመንፈስ ማረፊያቸው ቢሆንም ፋንታዚያቸው ግን የአፍሪካ አንከር መሆን ነው። የእኔ መረዳት እንዲህ ነው። ሥርጉትሻ 2025/09/24 ዝርዝሩን BBC አማርኛው ዘግቦታል። https://www.bbc.com/amharic/articles/c62ld9dy4v2o «የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአገራቸው ውስጥ እንዲዋጉ እንደማይፈቅዱ ተናገሩ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በአገራቸው በሰላም ማስከበር ላይ የሚሰማሩ የኢትዮጵያ እና የግብፅ ወታደሮች ወደ ግጭት ሊገቡ የሚችሉበት ምክንያት እንደሌለ በመግለጽ "የውክልና ጦርነት" አይኖርም አሉ። ፐሬዝዳንቱ ከቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ ላይ እንደተናገሩት በሁለቱ አገራት መካከል "በሶማሊያ ምድር" የሚካሄድ ጦርነት እንደማይኖር እና ሶማሊያም ይህንን እንደማትፈቅድ አሳውቀዋል። የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ በዚሁ ቃለ ምልልሳቸው ላይ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በሶማሊያ ውስጥ ግ...