"ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?"

 

ከአቶ ዋስ ያገኜሁት ትምህርት ነው። ይጠቅማል ትርጉም ማወቅ። " ማዕዶት" የሚል በጸጋየ ድህረ ገጽ አንድ መምሪያ ነበረኝ። እኔ በአማርኛ እርባታውን ተጠቅሜ ነበር ማዕዶት ያልኩት። ማዕድ የሚለውን ሥረ ቃል መነሻ አድርጌ የጥበብ ምግብ እንደማለት ነበር የተጠቀምኩት። በአማርኛ ፍሰት እኔ ተ ፊደልን ስለምወደው ሁልጊዜ ቃላትን ሳራባ ተን እጨምራለሁኝ። ሥርጉተ ወዘተ ነው ። የሆነ ሆኖ በግእዝ "መሻገሪያ" ማለት እንደሆነ ትርጉሙ ይገልፃል። አባ በጸሃ የሚባሉ የቄስ ትምህርት አስተማሪየ የቅኔም መምህር አንዱ መፃህፌ ላይ ግጥም ጽፌላቸዋለሁኝ። ትርጉሙን ዛሬ አገኜሁት "ደረሰ" ማለት ነበር ለካ።
 
"ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?"
 May be an image of candle holder and text
 
"1 ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው
2 ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው።
3 ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው
4 ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው።
5 ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው።
6 ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት
7 ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው።
8 ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው።
9 አስካል፦ፍሬ ማለት ነው።
10 በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው።
11 መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው።
12 መንክር፦ልዩ ማለት ነው።
13 ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው።
14 ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው።
15 ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው።
16 ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው።ቅዱስ ለወንድ ነው።
17 ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው።
18 ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው
19 ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው።
20 ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው።
21 ጸገየ፦አበበ ማለት ነው
22 ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው።
23 ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው።
24 ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው።
25 ሰናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።
26 ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው።
27 መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው።
28 መራሒ፦መሪ ማለት ነው።
29 ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው።
30 ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው።
31 ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው።
32 ብሩህ፦የበራ ማለት ነው።
33 ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው።
34 ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው።
35 አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው።
36 ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው።
37 ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው።
38 ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው።
39 ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው።
40 ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው።
41 አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
42 ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
43 ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
44 ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
45 ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
46 ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
47 ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
48 ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
49 በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
50 መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
51 ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
52 ትንሳኤ፦መነሳት ማለት ነው።
53 ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
54 ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
55 ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
56 ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
57 ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
58 ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
59 ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
60 መርአዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርአዊት ለሴት ነው።
61 ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
62 ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
63 ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
64 ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
65 ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
66 ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
67 ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
68 ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
69 ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
70 ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
71 ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
72 መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
73 ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
74 ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
75 ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
76 ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
77 አማን፦እውነት ማለት ነው።
78 አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
79 ሰዋስው፦ድልድይ ማለት ነው።
80 ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።"
......... ከአቶ ዋስ ያገኜሁት ነው። ትምህርት ስለሆነ ነው ሼር ያደረግሁት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።