ልጥፎች

ከጁን 9, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአብን መሥራች ጉባኤ ልዩ የምሥራች ነው - ለእኔ።

ምስል
            የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ                   መሥራች ጉባኤ                   ታላቅ           የምሥራች ነው።                                           ከሥርጉተ ሥላሴ ሲዊዘርላንድ 09.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)                                    „ሁሉ በሥላሴ ፈቃድ ተፈጥሯልና፣ ይህ ለምንድን ነው ያ ለምንድን ነው የሚል የለም።“                                                              (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፬ ቁጥር ፳፩) ብሥራት አባተ። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ መሥራች ጉባኤ በባህርዳር እዬተካሄደ ስለመሆኑ ዛሬ ግንቦት 09.06.2018 ከሚሊዮኖች ድምጽ ከጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሽፈራው እና ከዘሃበሻ ደ...

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)

ምስል
በአማራ ምሁራን የተቋቋመው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን ) በባህርዳር የፓርቲውን መመስረቻ ጉባኤ ማድረግ ጀመረ June 9, 2018 |  Filed under:  News Feature , የዕለቱ ዜናዎች  |  Posted by:  Zehabesha ( ዘ - ሐበሻ ) በአማራ ምሁራን የተመሰረተውና    የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ( አብን ) በሚል የሚጠራው አዲሱ ፓርቲ በባህርዳር ከተማ የመመስረቻ ጉባኤውን እያደረገ መሆኑን ለዘ - ሐበሻ የተላከው መረጃ ጠቁሟል :: የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ; የአማራን ሕዝብ በሁሉም መልኩ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥና በተለያዩ አካባቢዎች ክልሉ ህዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን የመከላከል ዓላማ በመያዝ መቋቋሙን በባህርዳሩ መመስረቻ ጉባኤ ላይ ተነግሯል :: በባህርዳር ሙሉዓለም አዳራሽ ዛሬ የተጀመረው ጉባኤ በነገው ዕለት እሁድ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል :: በጉባኤም ድርጅቱን የሚመሩ የአመራርና የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምርጫ እንደሚደረግ ይጠበቃል :: በነገው ዕለትም ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል :: የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን የመሰረቱት    19 ሰዎች በህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ ሂደ ድጋፍ በሚያሰባስቡበት ወቅት በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸውና መለቀቃቸው አይዘነጋም :: ምንጭ ዘሃበሻ ዘገባ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/91865#respond

አዲሱን የአማራ ፓርቲ ማን ወለደው?

ምስል
አዲሱን የአማራ ፓርቲ ማን ወለደው ?     ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው June 9, 2018 | Filed under: የዕለቱ ዜናዎች | Posted by: ዘ - ሐበሻ ዛሬ ሰኔ 2/2010 ዓም በባህርዳር አዲስ የአማራ ፓርቲ ምስረታ ጉባኤ ተጀምሯል። በምስረታው ላይ ሁለት አይነት “ የሕዝብ ” ስሜት ይብፀባረቃል። አንደኛው ደስታ ነው። ሁለተኛው በጥቅሉ ትችት ይመስላል። በዘር ተደራጁ የሚል። ደስታው ሕዝብ ወኪል ከማጣቱ የመጣ ነው። የሕዝብን ብሶት የሚያሰማ አካል በመጥፋቱ አማራጭ ተገኘ ከሚል ነው። የትችቱ ስሜት የሚመጣው አማራ እነ መለስ በተለሙት የዘር ቀመር መደራጀት የለበትም ከሚል የቅንነት የሚመስል ሙግት፣ የአማራው ሕዝብ በማንነቱ ከተደራጀ ቦታ አናገኝም ከሚሉ ቡድኖች ስጋት ይመስለኛል። በዚህ ወቅት የአማራ ሕዝብ አይደራጅ ለማለት ይህን ህዝብ የሚታደግ ሌላ አማራጭ ያስፈልጋል። ሁለት አማራጮች አሉ ሊባል ይችል ይሆናል። ·          አንደኛው የትህነግ / ህወሓት ተላላኪ ሆኖ የአማራን ሕዝብ ሲያስገዛ፣ ሲያስገድል፣ ሲያስዘርፍ የኖረው ብአዴን የሚሉት ቡድን ነው። ይህ ቡድን የትህነግ / ህወሓት ወኪል ሆኖ የአማራን ሕዝብ ላይ በደል ሲፈፅም የኖረ እንጅ ለህዝብ የሚሰራ አይደለም። ·          ሁለተኛው አማራጭ አንድነት ሀይሉ ነው። ብአዴን የአማራውን ስም እየጠራ አማራን ...