የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)

በአማራ ምሁራን የተቋቋመው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በባህርዳር የፓርቲውን መመስረቻ ጉባኤ ማድረግ ጀመረ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች | 
(-ሐበሻ) በአማራ ምሁራን የተመሰረተውና  የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በሚል የሚጠራው አዲሱ ፓርቲ በባህርዳር ከተማ የመመስረቻ ጉባኤውን እያደረገ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የተላከው መረጃ ጠቁሟል::
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ; የአማራን ሕዝብ በሁሉም መልኩ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥና በተለያዩ አካባቢዎች ክልሉ ህዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን የመከላከል ዓላማ በመያዝ መቋቋሙን በባህርዳሩ መመስረቻ ጉባኤ ላይ ተነግሯል::
በባህርዳር ሙሉዓለም አዳራሽ ዛሬ የተጀመረው ጉባኤ በነገው ዕለት እሁድ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል:: በጉባኤም ድርጅቱን የሚመሩ የአመራርና የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምርጫ እንደሚደረግ ይጠበቃል:: በነገው ዕለትም ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል::

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን የመሰረቱት  19 ሰዎች በህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ ሂደ ድጋፍ በሚያሰባስቡበት ወቅት በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸውና መለቀቃቸው አይዘነጋም::
  • ምንጭ ዘሃበሻ ዘገባ።

https://www.zehabesha.com/amharic/archives/91865#respond

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።