ልጥፎች

ከሜይ 1, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ሙት ዓመት መታሰቢያ።

ምስል
የቅኔው ንጉሥ ፈላስፋ – የትውልድ ግሥ፤   የኑሮ ስዋሰዋዊ – ምዕት፤   ( የሎሬት ጸጋዬ ገ / መድህን ሙት ዓመት መታሰቢያ ) ከሥርጉተ   © ሥላሴ ( Sergute © Sselassie ) 25.02.2013  (ከደመግቧ  ሲወዘርላንድ – ዙሪክ ) („ ጥበብ ቤቷን ሠራች፣ ሰባቱን ምሰሶ አቆመች። ምሳሌ፤ ምዕራፍ 9 ቁጥር 1“) ተግቶ ንጋትን ሠራት። በቀንበጥነት በዝግጁነት ሰማያዊ ጥሪን ታጥቆ ተቀበለ – ጀግና። የማያልቅ ሙቅ ሥነ – ጥበባዊ ስሜትን በተስፋ ስንቅነት ቀመረ፣ አንጥሮ በቅንነት ለገሰ፣ አንቆጠቆጠም። በስብዕናዎቹ ውስጥ ማንነቱን ሰንደቁ ያደረገ ጉልቶ የሚታይ የትውልድ ጌጠኛ ዓውራ። ተግባሩ ዋጋቸው ለዘመናት ሳይቀንስ እዬፈኩ – እዬደመቁ ከሩቅም ከቅርብ በቋሚነት የሚጠሩ ዘላቂ ማገሮች ናቸው። ሃብትነቱ – ሁለመና ሁለአቀፋዊ ሞዴል መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዳኝነቱ ጥልቅ ሥልጡን ውስጠ አዋቂ – መርማሪዎች ናቸው። የአፍሪካ ዋርካ፤ የፓን አፍሪካኒስትነት ጠበቃ፤ የሰብዕዊነት ዕጬጌ ነው የቅኔው ዐፄ ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ! ሥጦታ ! ምርቃት ! ቅኔው – ተዘረፈ እቶኑም – አጠና … ቅኔውም አፈራ፤ አብነት – ተጉዞ ረጅም – ተመዞ ቅኝተ – መዘዞ፤ ሀቅን – ጎዘጎዘ ሚስጥርን አፈሰ። ፈልነን – አፍልቶ ትናንትን – ፈወሰ። ዛሬን – አነገሠ … ሥጦታ – አቀሰሰ። ግሡ – ተገሰሰ፤ ዜማ ተንተራሰ ጥበብ – ገሰገሰ። መምህሩ ነገሠ፤ ድንቅነት – ለበሰ። በዐለም አንደበት ሎሬት – ተወደሰ ! ብዕርህ ወተት ናት፤ — ዕልፍን የፈጠረች መንፈስህ