ኃራም መኖር ላይበር።
ኃራም መኖር ላይበር።
ከሥርጉተ©ሥላሴ (Sergute©Sselassie)
21.03.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
21.03.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
„የሕልሙን ፍቺ አንዲሰጡኝ የባቢሎንን ጠቢባን ሁሉ ወደ እኔ ይገቡ ዘንድ አዘዝሁ።“
(ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ
፬ ከቁጥር ፮ እስከ ፯)
በመሆን ውስጥ ሳይኖር
በሳይኖር ውስጥ ሲኖር፣
በሲኖር ውስጥ ሳይኖር
በውስጥ ሳይኖር ሲኖር፤
ሳይኖር መኖር በማኖር
መኖር ሳይኖር ሲኖር?
በነፍስ መኖር ሲ‘ር
ብትን አፈር ሲመር፣
መኖር ሳይኖር ሲተረተር
ሲበረበር … ሲፈረፈር … ሲመረመር … ሲሸረሸር
…
መኖር ሲታሰር በጭስ ግብር፣
የመኖር ቅበር ቀንበር
ሲሰረስር ሳይፈጠር?
እኮ! ምን ፍጠር?
ሲሰባበር በድርድር፣
ባርባር ባርባር …
ኃራም መኖር ላይበር።
· መኖሩ ለተሰረዘ ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ይሁንልኝ
(21.03.2018.)
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ