ልጥፎች

ከማርች 20, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአቶ ነአምን ዘለቀ ከግንቦት 7 ራስን ማግለል ዕድምታ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የራስነገር። „አንተ ፈጣሪያችን ግን ቸር ነህ ይቅር ባይ ነህ፤ የምትታገሥ ነህ፤ ከሀሊነትህን እያወቅን ብንበድልም ባንበድልም፤ ያንተ ወገኖች   ነንና በቸርነትህ ሁሉን ትሠራለህ። ነገር ግን ያንተ ወገኖች   እንደ ሆንን እናውቃለን።“ መጽሐፈ ጥበብ ፲፭ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        ከውስጥ ስለማዬት። የእኛ ነገር እንዲህ ነው ተሰበሰበ ሲባል መበተን፤ ተበተነ ሲባል መሰብሰብ። ተቃና ሲባል መጉበጥ፤ ጎበጠ ሲባል ደግሞ መቃናት፤ ፈሰስ ሲባል መ ለ ቀም፤ ተለቀመ ሲባል መፍሰስ እኛ እንዲህ ነን። በቀለ ሲባል መድረቅ፤ ደረቀ ሲባል ማጨብጨብ፤ ሞላ ሲባል መጉደል ጎደለ ሲባል መሙላት፤ ሞላ ሲባል መፍሰስ፤ ፈሰሰ ሲባል ክው ብሎ መድረቅ ዕጣ ፈንታችን ይኸው ነው። ሰሞኑን አንድ ዜና አዳመጥኩኝ። ሳዳምጠውም ደነገጥኩኝ። ጋደም ብዬ ስለነበር ቀና አልኩኝ እና በማስተዋል ዜናውንም ሀተታውን አዳመጥኩኝ አቅራቢው ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማዬሁ ነበር። የሰማሁት ከዘሃበሻ ኦፊሻል ድህረ ገጽ ላይ ነበር። በምልሰት ደግሜ አዳመጥኩት። ድንጋጤዬ አብሮኝ ቆዬ። በዚህ ወቅት ይህ ይሆናል ብዬ አልገመትኩም ነበር። የእውነት። አቶ ነዓምን ዘለቀ ከግንቦት 7 ራሳቸውን ማግለላቸው ነበር ዜናው። ዜናው ከዘሃበሻ ስለገኘሁት አልተጠራጠርኩትም። ግን በጹሑፍ የሰፈረ አግኝቼ እስክመረምረው ተግ አልኩኝ። ትናንት ሚዲያዎች ላይ ጎልቶ የወጣ የውይይት አጀንዳ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። አብሶ በደከሙለት ሚዲያ በኢሳት ከዜና በስተቀር እንደ አቶ ዛዲግ አብርሐ ያህል እንኳን ቁብ አልተሰጠውም ወይንም ክብር አልተሰጠውም

ኢትዮጵያስ እራሷስ እዬተፈናቀለች አይደል

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ኢትዮጵያስ እራሷስ እዬተፈናቀለች አይደል። "ይገባቸዋልና ስለዚህ ነገር ጣዖቶቻቸውን በሚመስሉ አጋንንት ጠፉ፤  በብዙ የሚሆኑ ትንኞች ክፉ የሚሆኑ እንዚህ ተጨነቁ።"  መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 20.03.2019 ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ? አላዛሯ ኢትዮጵያ ታማለች። በሁለመናዋ እዬተጎሳቆለች ነው። እሷ እራሷ እተፈናቀለች ነው። በመንፈስ፤ በሥነ - ልቡና በሁለመናዋ ነቀላ እዬተካሄደባት ነው። የዚህ ምንጩ ማነው? መሠረቱስ ምንድን ነው? ·        ጋኔል። ለዚህ ሁሉ ምንጩ እና መሰረቱ የሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጋኔል ማንፌስቶ ነው። የ አቶ ሌንጮ ለታ እና የሄሮድ መለስ ዜናዊ መግለጫም ነው ህገ መንግሥት የተባለው። ሲቀመም በሻብያ ውሃ ልክ ነው። ይህ ማንፌስቶ በኖረበት አራት አስር ዓመታት ሁሉ በእያንዳንዱ ሰከንድ ማለት ይቻላል፤ ጣሊያን ወረስ የሆነውን ኢትዮጵያን ጨርሶ የማፍለስ ፍልስፍ ዶክተሪን ነው የተከተለው።   ለጋኔሉ ሰነድ እውን ለማድረግ አጥፊ አረም ሲተክል ነው የኖረው የሄሮድስወሌንጮ የሚባትት ክፉ መንፈስ።  አሁን ነው እኔ እዬታዬኝ ያለው ያ ሙት መንፈስ አሁንም እያመሰ ስለመሆኑ። ያ ሰይጣናዊ መንፈስ አሁንም የዘራውን እያጨደ ሳይሆን እኛኑ ቀጥቅጦ ገዝቶ ደግሞ አሁንም አስደግድጎ እያሳጨደን ይገኛል። የሁለቱ የሙት መንፈስ አንዱ በአካል ሌላው በደመንፈስ እንሆ ኢትዮጵያን እያፈናቀላት ነው ከባዕቷ። ኢትዮጵያዊነት ማለትም መሆንም በአደባባይ በአዋጅ እዬተራደ እዬተቃጠለ እዬወደመ ነው የ