#ጊዜን የማድመጥ አቅም፣ ሊደመጥ ይገባል።
#ጊዜን የማድመጥ አቅም፣ ሊደመጥ ይገባል። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም።" #ክፍል ፲፱። https://www.youtube.com/watch?v=8NoAvavswVk ኢትዮጵያ ቦታዋ አሁን ያለችበት አይደለም | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ETV | EBC | EBCDOTSTREAM https://www.youtube.com/watch?v=sN2roWE6dAs ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ ሼር ባደረኩት ሊንክ ያዳመጥኩት ሲሆን፣ በጉዳይ ላይ ሦስት ጉልህ አመክንዮችን አስተውያለሁኝ። እና ሂደቱን በአራተኛ ደረጃ ላነሳ እሻለሁኝ። 1) ስለ ፕሮፌሰር ዶር. ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስተሩ የተነሳው በጎ ጉዳይ ነው። ገፊ ኃይሉ፣ ስለምን ጎልቶ እንደ ተነገረ ዛሬ ላይ ለእኔ ግልጽ ነው። ባለፈው በሰፊው ጽፌበታለሁ። 2) ስለ የጥበብ ቤተኞች የተሰጠው ማብራሪያ ነበር። "ዓዋቂወች ግን ……… " ጉዳዩን ባለቤቶቹ ይሂዱበት። እኔ በዚህ አገላለጽ የምሻውን ብቻ እገልፃለሁኝ። 3) ስለ " #የሠፈር ' ዕሳቤ በተነሳው ጉዳይ ምልከታዬን አቀርባለሁ። 4) የፕረዘንቴሽኑ #ቶን ፣ ጀስቸር እንዲሁ ብቃኜው ብያለሁኝ። #አንከር ጉዳዮቼ። ቁጥር 1) ስለ ፕሮፌሰር ከዚህ ቀደም ስለፃፍኩበት ሊንኩን አስቀምጣለሁኝ። ከእኔ ዕሳቤ ጋር አቻ የሆነ ዕይታ መራመዱን ወይንም አለመራመዱን የእናንተ ህሊና ይመዝነው ዘንድ እተወዋለሁኝ። ቁጥር 2) የጥበብ ቤተኞችን የህሊና አቅም ጎልቶ፣ የማህበራዊ ኑሮ ዘይቤያቸው ላይ ስስነት ተወስቷል። እራሳቸው ባለቤቶቹ ስላሉ እሱን ለእነሱ እሰጣለሁኝ። ተመቸ...