ልጥፎች

ከኦክቶበር 7, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ከ2010 – 2024 አይቆጠርም። ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱስ? • #ቦነሷ ዝቀሽ በሆነባት አገር አገረ ኢትዮጵያ።

  #ከ2010 – 2024 አይቆጠርም። ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱስ? • #ቦነሷ ዝቀሽ በሆነባት አገር አገረ ኢትዮጵያ።    https://www.youtube.com/watch?v=TVDR-fNoBks «በኃይል ሳይሆን በሃሳብ የበላይነት በምክክር የምትጸና ኢትዮጵያ ETV | EBC | EBCDOTSTREAM» https://www.youtube.com/watch?v=7jR-X1Psqdg «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አዲሱ የመደመር መንግሥት በይፋ ሲመሰረት ያስተላለፉት መልእክት» | Pm Abiy Ahmed   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።"   #ምዕራፍ ፳።   ፩ኛ።   የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ መክፈቻ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ፤ በዛ በቀድሞው የኬኒያ መሪ አስደማሚ ንግግር በተደረገበት የምክክሩ የመዝጊያ ሥርዓት ላይ አልተገኙም። ጥፍት ብለው ነበር።    እኔ በጥሩ ጎኑ ነው ያዬሁት። የጥሞና ጊዜ ከነበራቸው። ከሰሞኑ የራሳቸውን መንፈስ ለራሳቸው ርክክብ ሊፈጽሙ የአጀንዳ የውሳኔ ሃሳብ፤ ያሰቡት ሳይሳካ በቀረው በኢትዮጵያ፤ በአፍሪካ፤ በዓለም የዲፕሎማሲ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባን የኦሮምያ የማድረግ ህልማቸው በአሰቡት መስመር ከስሟል። የልጆች የዕቃ ዕቃ ጨዋታ በሚመስል በሚያስገምትም ሁኔታ ተለጣፊ ፈጥረው አንገዋለውታት ፋክት ዕውነት የ4000 ታዳሚን መንፈስም።    ይህ ሃሳብ በምንያህል #እርቀት "ለታላቅ አገር ለታላቅ ህዝብ ለታላቅ ራዕይ" ለሚባለው የሚዲያ ሞቶ #እሩቅቅ በጣም እሩቅ እንደሆነ ላስታውሳቸው እፈልጋለሁ በትህትና እና በአክብሮት። እራሷ አዲስ አበባ በፌድራል ሥር ትሁን የተባለበት ምክንያት የንስኃ አባቷ መሆን ስለተፈለገ እንጂ ለራስ ገዝነት የማታንስ...

#መለሲዝም ዕድለኛ ነው። ድምጡን አጥፍቶ ሥራውን ይሠራል። #ሌጋሲው ቀጥሏል። 2) ዝምታ #ከጩኽት ይከብዳል።

  1) #መለሲዝም ዕድለኛ ነው። ድምጡን አጥፍቶ ሥራውን ይሠራል። #ሌጋሲው ቀጥሏል። 2) ዝምታ #ከጩኽት ይከብዳል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።"    አቶ አህመድ ሸዴ የፓርላማ አፈ ጉባኤ። ወሮ ሙፍያት ካሚል የፌድሬሽን ምቤት አፈጉባኤ   #ምዕራፍ ፳።   ሁለት እርዕሶችን በአንድ ላይ አጣምሬ እስቲ ልሂድበት።   ከትናንት በፊት የሲዳማ የክልል ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን ወደ #ፌድሬሽን #ምክርቤት አፈጉባኤ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ጽፌ ነበር። የግምቴ አቅጣጫ ትክክል ነበር ማለት ነው።   "የአዲስ መንግሥት ምሥረታ።" መንግሥት በሌላት አገር የተፈጠሩ የአገር መሪወች? የሚገርሙ እኮ ናቸው። ኢትዮጵያ እኮ ከቀደምት መንግሥት ከመሠረቱ አገራት ተርታ የተመደበች አገር ናት።    አየር ላይ ተተክሎ፤ በቅሎ እንደ ጸደቀ፤ እንደ አፈራም ሰብል ኢትዮጵያን #አብይዝም ሠራሽ አድርገው ባያቀርቧት ጥሩ ነው። ለነገሩ ኢህአዴግ ነፍሱ እንዳለ የሚያሳይ የምደባ ኩነት ተስተውሏል።   በሌላ በኩል #ስብጥሩንም በማስተዋል መመርመር ይገባል። ብልሁ ጉዳይ ያ ይመስለኛል። አዲስ ነገር ግን #አላየሁም ። ሳሎን የነበረውን ወደ ጓዳ፤ ጓዳ የነበረውን ወደ በረንዳ፤ ከበረንዳ የነበረውን መኜታ ክፍል ሽግሽግ ነው።    ለውጥ ለዛውም " #አዲስ " የት ላይ ይሆን ያለው። ይልቅ በቃላት፤ በሞቶ፤ በሥንኝ ውበት ከመጽናናት የተረሳው ቢሮክራሲ፤ ከፖለቲካ #ውክልና #ውጭ የሆነችውን #ቅድስት #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶን ማሰብ። ምንም አያደርግም ተብሎ የተናቀውን ዝምተኛውን የማህበረሰብ ክፍል ሊያሳምን የሚችል የቁም ነገር ትጋትን አቅዶ መተግበር በእጅጉ ይገባል።   ...

#የከበደ ምስክርነት ለባለቤቱም ለተመስጋኙ ለአመስጋኙም።

  #የከበደ ምስክርነት ለባለቤቱም ለተመስጋኙ ለአመስጋኙም።   "ልጄ ሆይ በክፋ ሰወች አትቅና፣ ከእነርሱ ጋርም መሆንን አትውደድ፣ ልባቸው ግፍን ታስባለችና፣ ከንፈራቸውም ሽንገላን ትናገራለችና።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ከ፩ - ፪)   #ምዕራፍ ፳።   "ጭምት ናቸው" ሲባል እሰማለሁኝ። ለትዳራቸውም ታማኝ ናቸው" ሲሉ እሰማለሁኝ። ምክትል ጠቅላይ ሚር አቶ ተመስገን ጥሩነህ። እኔ አየር ላይ ያዬኋቸው፣ ሥራ ላይ እንደነበሩ ያወቅሁት የአማራ ክልል ሊቃናት #ሰማዕታት ሲሆኑ ያን ጊዜ የአማራ ክልል መስተዳድር ፕሬዚዳንትነት ለአንድ ዓመት #በተመላላሽነት ሲሰሩ ነው ገፃቸውን ያዬሁት።    አወንታዊ የሆነ ዕይታዋን የሰጠች የማከብራት አንስት ብዕረኛም ነበረች፣ ከእኔ ከእሩቋ ይልቅ እሷ ቅርብ ናት። በጸረ ህወሃት የትግል ዘመን አላውቃቸውም ነበር። የሆነ ሆኖ በብልፄው ጉባኤ ላይ "ብልጽግናን መምረጥ ነገን መምረጥ" ነው ሲሉ ሙግት ቢጤ ጥፌ ነበር። ዕውነት ለመናገር ጽፌባቸውም፣ ሞግቻቸው አላውቅም።   ዛሬም #ልሞግታቸው አይደለም። ህዝብ የሚዬው የዕውነት - ዕውቀት አለና ለህዝብ የህሊና ዳኝነት ዕድሉን መስጠት ይገባል። እንደ እኔ ግን የሚከብድ ይመስለኛል ለቀጣይ ህይወታዊ ህሊናዊ ጉዳይ።    በዚህ #የአዲስ #ፕላኔት ይሁን ሐዋርያ የአቶ ተመስገን ጥሩነህ ፍለጋ እና #ግኝት ውስጥ እንዴት የመንፈስ ቁመናቸው እራሱን ችሎ በጤነኝነት እንደሚቀጥል አላውቅም። ዶር አብይም አንገታቸውን ደፍተው አቀርቅረው ነው ያዬኋቸው።    በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብ #የትግዕስቱ መጠነ ሰፊነት #ቁሞ አስተምሮኛል። ንግግሩን ለማዳመጥ ልዩ የመቻል፣ #የመታገስ አቅም ይጠይቃል። ለ2...

ማን ነው #የጠበቀው? #ዳታ ሠርታችሁልን?

  ማን ነው #የጠበቀው ? #ዳታ ሠርታችሁልን?   "እግዚአብሄርን መፍራት ወደ ህይወት ያመራል።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፱ ቁጥር ፳፫።)   #ምዕራፍ ፳።   "የመንግስት ምስረታው ለምን ተጠባቂ ሆነ?"    ሁሉንም አካቶ #እንደ እራስ #ወጥ ፍላጎት ውስጥ አድርጎ ማየት አይገባም። በተለይ ሚዲያ። የራስን ሃሳብ ይሁን ፍላጎት ይሁን ምኞት ይሁን ራዕይ በፈለጉት ቃል መግለጽ ይቻላል።   ግን #ጥናት ሳይሠራ እንዲህ ጠቅልሎ አንድ አጀንዳ ውስጥ ሁሉንም በአንድ መሥመር ውስጥ ማስገባት #አልጫ ነው የሚሆነው።   ቢያንስ አገር ውስጥ ያሉ ዕውነተኛ ሞጋች ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችን ማሰብ ይገባ ነበር።     #የሰላማዊ ታጋዮች እነሱ ተወዳድረው ውጤት ያላገኙበትን የምርጫ መቋጫ #ጓጉተው ወይንም #ናፍቀው ይጠብቃሉ ተብሎ ይህን ከመሰለ ማጠቃለያ  መድረስ የተገባ አይደለም። #የታሠሩም አሉ እኮ።   ሌላው በጣም ሌላው የኢትዮጵያም ሚዲያ ይሁን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #ጭምቱ ማህበረሰብን (sillent majority)ምልከታ፤ አቋም ማወቅ አይቻልም።    ይህ ባለ ልዩ መክሊት የማህበረሰብ ክፍል የልቡን ሲያገኝ ብቻ ነው ግብረ መልስ የሚሰጠው። ይህንን ጠቅላይ ሚር አብይ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፤ #የቴዲ "ዳስ ጣል" ላይ ታይቷል። ፖለቲከኞችን ወደ #ዘፈን የሳበ ሞገድ እኮ ይሄው የጭምቱ ማህበረሰብ ልዩ የአቅም ክህሎት ነው።   አብዛህኛው የኢትዮጵያ ህዝብ መደቡ #ዝምታ ላይ ያለ ነው። #የጨመተ - ስኩን አቅም ያለው (sillent majority) ከዛ ከማይታወስ፤ ከተረሳ #ዝምተኛ ማህበረሰብ ውስጥ ነው። " እናስተውል" እንደማለት። ...